የኢዮቤልዩ ዓመት በጎ ፈቃደኞች ቅዱስ በርን በመሻገር መጨረሻውን ንግደት አደረጉ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
የበጎ ፈቃደኞቹ ሰኞ ታኅሳስ 5/2018 ዓ. ም. ምሽት ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሚወስደው ዋና መንገድ በኩል እያስተነተኑ ዑደት በማድረግ ወደ ባዚሊካው አምርተዋል።
በአረንጓዴ ጃኬቶቻቸው የሚለዩት በጎ ፈቃደኞቹ በቅዱስ ዓመት በቫቲካን የሚገኘውን የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርን ያቋረጡት የሕይወት ልምዶቻቸውን፣ ስጋቶቻቸውን እና ግምቶቻቸውን ይዘው እንደ ነበር ተገልጿል።
ባለፈው የኢዮቤልዩ ዓመት ከዓለም ዙሪያ ወደ ሮም የመጡ ከ33 ሚሊዮን በላይ ነጋድያንን ተቀብለው በማስተናገድ ሥራ ላይ የተሳተፉት 5,000 በጎ ፈቃደኞች ከተለያዩ የማኅበሰብ ክፍሎች የተውጣጡ እንደ ነበሩ ታውቋል።
የበጎ ፈቃደኞቹ በቅድስት መንበር የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ከሆኑት ከሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ ጋር ሰኞ ታኅሳስ 27/2018 ዓ. ም. ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የመጨረሻ ንግደት አድርገዋል።
ለራስ እና ለሌሎች ሽፋን መስጠት
በሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ መሪነት ወደ ባዚሊካው ዑደት ያደረጉት በጎ ፈቃደኞች ለኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀውን የእንጨት መስቀል ከፊት በማስቀደም ሲሆን፥ በመካከላቸው የአንድነት ስሜት የሚታይባቸው በበጎ ፈቃደኞቹ ወደ ፍጻሜው ባደረሱት የአገልግሎት ተሞክሮአቸው ላይም አስተነትነዋል።
ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ በመዝጊያ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ እንደገለጹት፥ በጎ ፈቃደኞቹ በደህንነት እና በወንድማማችነት ሁኔታ ውስጥ አገልግሎት መስጠታቸው የጋራ ግንዛቤን የሚገልጽ እንደ ነበር ተናግረዋል።
በጸጥታ መንፈስ የተደረገ አስተንትኖ
የበጎ ፈቃደኞቹ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የሚወስደውን መንገዱ ተከትለው ዑደት ሲያደርጉ በጸሎት እና በዝማሬ ከመተባበራቸው በተጨማሪ የዓመቱን ትዝታዎችን እና የተግባር ልምዶችን ተለዋውጠዋል።
ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ በር ሲደርሱ፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2033 ዓ. ም. በሚከበረው የቤዛነት ኢዮቤልዩ ዓመት እስከሚከፈት ድረስ በሚዘጉት ቅዱስ በር ፊት ደርሰው በጸጥታ ጸሎታቸውን አድርሰዋል።
በዓመቱ ውስጥ የባዚሊካዎችን ቅዱስ በሮች የሚሻገሩ ምዕመናንን ሲያስተናግዱ የቆዩ በጎ ፈቃደኞቹ፥ በዚህ አጋጣሚ እነርሱም የመስቀል ምልክት በማድረግ እና የግል ጸሎቶችን በማቅረብ ወደ በሩ ደርሰዋል።
“እጅግ ውብ ልምድ ነበር”
የበጎ ፈቃደኞቹ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ በር ያደረጉት ዑደት የተጠናቀቀው ወደ ባዚሊካው ዋና መንበረ ታቦት ሲደርሱ ሲሆን፥ ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወሰኑት መሠረት የ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትን ለማግኘት የተዘጋጀውን ጸሎትን እና የሐዋርያት ጸሎተ ሃይማኖትን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ መርተዋል።
በቅድስት መንበር የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ ለበጎ ፈቃደኞቹ ባደረጉት ንግግር፥ ተሞክሮአቸው ውብ ልምድ ቢሆንም፥
የኢዮቤልዩ ዓመት የተስፋ ጉዞ ስላበቃ ብቻ ተስፋው የሚያሳዝብ ባለመሆኑ በጎ ፈቃደኞቹ የቤተ ክርስቲያናቸው “ሕያው ድንጋዮች” ሆነው እንዲቀጥሉ አበረታቷቸዋል።
የበጎ ፈቃደኞቹ በቅዱስ ዓመት ውስጥ ያደረጉትን ተሳትፎ የሚገልጽ የአገልግሎታቸው ማብቂያ የሆነውን የንግደት ሥነ-ሥርዓት በመፈጸም የኢዮቤልዩ ዓመትን ደምድመዋል