“የጦር መሣሪያ ትጥቅ መፍታት እና ማስፈታት፡- ሰላም ስጦታ ነው” በሚል አርዕስት በቅርቡ ይፋ ስለሆነው መጽሐፍ “የጦር መሣሪያ ትጥቅ መፍታት እና ማስፈታት፡- ሰላም ስጦታ ነው” በሚል አርዕስት በቅርቡ ይፋ ስለሆነው መጽሐፍ  

ር.ሊ.ጳ ሊዮ ሰላም የተገነባው በኑክሌር ጦር መሳሪያዎች ሳይሆን የጦር መሣሪያ ትጥቅ በመፍታት ነው አሉ!

የቫቲካን ማተሚያ ቤት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የተጻፈ አዲስ መጽሐፍ ይፋ ድርጓል፣ “የጦር መሣሪያ ትጥቅ መፍታት እና ማስፈታት፣ ሰላም ስጦታ ነው” የአቶ አሌሳንድሮ ባንፊ የአርቶት ሥራ የተካተተበት ጥራዝ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እ.አ.አ ግንቦት 8 ቀን 2025 ዓ.ም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 267ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ሰላም የሰጡትን ንግግሮች እና አስተያየቶችን አንድ ላይ ያገናኛል።

“ሰላም ለእናንተ ይሁን” የተሰኙ ቃላት ከሙታን የተነሣው ኢየሱስ ለሐዋርያቱ የሰጠው የመጀመሪያ ሰላምታ ነበር (ዮሐ. 20:19)። ይህ ደግሞ ከሙታን የተነሣው ክርስቶስ ለሐዋርያቶቹ እና ለመላው ዓለም የሰጠው የመጀመሪያው ስጦታ ነበር፣ ሰላም! ያ ስጦታ ግን “በርካሽ” ዋጋ አልመጣም፤ የናዝሬቱ ጌታ ክቡር አካሉን የህማማቱን ቁስል አሳይቷል። ጥላቻን፣ ዓመፅን፣ የዓለምን መስቀል ተቋቁሟል፣ ተጋፍጧል። ትጥቅ አስፈትቶና ትጥቅ ለማስፈታት ኢየሱስ ክርስቶስ ኢፍትሃዊነትን ተቋቁሞ ተነስቷል። የወንጌል አዋጅ በታሪክ ውስጥ ገብቷልና ራሱን አስገብቷል። ዛሬም ከ2,000 ዓመታት በፊት እንደነበረው ማለት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ

ሰላም የብዙ ሰዎችን ልብ የሚያነቃቃ ታላቅ ፍላጎት ነው፣ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ስጋት ላይ ይወድቃል፣ ይረገጣል እና ይሳለቁበታል። ዛሬ፣ በምድር ላይ በሚደረግ ጦርነት ውስጥ 103 አገሮች በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ በሆነ መንገድ ተሳትፈውበታል። በዩክሬን፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በሱዳን፣ በምያንማር፣ በየመን፣ በኮንጎ እና በሌሎች በርካታ ሁኔታዎች የጦር መሳሪያዎች እየጨመሩና የሰውን ልጅ እየገደሉ ነው። በእርሳቸው ዘመን የቀድሞ እና ተወዳጁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የሦስተኛው የዓለም ጦርነት በከፊል ተጀምሯል” የሚለውን አገላለጽ የፈጠሩት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ ያለ ቅድመ ሁኔታ ሰፊ የግጭት ሁኔታ ለመግለጽ አስበው ነው። በዚህ ርዕስ ላይ ያቀረብኳቸውን ንግግሮችን ስመለከት፣ አሁን በዚህ የቅኔና የሌሎች ጽሑፎች አስተሳሰቦች ውስጥ የተጠናቀረ፣ ለልቤ ቅርብ የሆኑ አንዳንድ ገጽታዎችን ማጉላት እፈልጋለሁ።



ከሁሉም በላይ ሰላም ኃላፊነት ነው። ችግር ሲያጋጥመን፣ ውጥረት ሲገጥመን ወይም ሲስድቡን የመጀመሪያ ስሜታችን በሌሎች ላይ መፍረድ፣ መክሰስና ማውገዝ ከሆነ፣ ከዚያም፣ የማይቀር፣ መጀመሪያ ግድየለሽነት ከዚያም ጥላቻ በዙሪያችን መብቀል ይጀምራል። የሚያጠፋና የማይገነባ እውነታን የመመልከት መንገድ አለ። በምትኩ ሰላም የሚጀምረው ከእኔ ነው። በእኛ ነው። ቅዱስ አውጎስጢኖስ እንዲህ ብሏል፣ “‘ጊዜው ተቸግሯል፣ ጊዜው ከባድ ነው፣ ጊዜውም ክፉ ነው።’ ጥሩ ሕይወት ኑር፣ እናም ጊዜውን በመልካም ሕይወት በመኖር ትለውጣለህ፤ ጊዜውን መለወጥ ትችላለህ፣ ከዚያም የምታጉረመርምበት ምንም ነገር አይኖርህም" ይለናል። በዕለት ተዕለት ግንኙነታችን፣ በቤተሰባችን፣ በቤታችን፣ በከተሞቻችን፣ በሥራ ቦታ፣ በራሳችን መኖር ካልጀመርን በዓለም ላይ ያሉ ኃያላን ሰዎችን ሰላም መጠየቅ አንችልም። ሰላም የሚገነባው በትንሽ የዕለት ተዕለት ምልክቶች ነው፡ የፈገግታ ስጦታ፣ የጥፋተኝነት ስሜት ሲኖር ይቅርታ በማድረግ፣ የደግነት ቃል በመናገር።

ከዚህም በላይ ሰላም የሚገነባው በእውነት ነው። ጦርነትን “በሰላም ስም” እንደሚያደርጉ የሚናገሩ እንኳን። ማንም ሰው ለጦርነት ሲል ጦርነት እንደሚፈልጉ ለመናገር አይደፍርም፤ የምድር ኃያላን እንኳን እያንዳንዱ ሰው ፍትህን እንደሚመኝ እና በሰላም ለመኖር እንደሚፈልግ ያውቃሉ። በተለይም የሂሮሺማ እና የናጋሳኪ ክስተቶች አስከፊ መዘዝ ከተከሰተ በኋላ፣ ወደ ጦርነት የሚያመራው መንገድ “ምንም መመለሻ የሌለው ጀብዱ” ነው፣ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዳስጠነቀቁት ከሆነ። ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ያቀረቡትን ልባዊ ጥሪ ከአንድ ጊዜ በላይ ደግሜ ደጋግሜ ተናግርያለው። ሰዎችን አንድ የሚያደርገው፣ የተከበሩት የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንደገለጹት፣ “የዓለምን የወደፊት ታሪክ ሊለውጥ በሚገባው መሐላ የታተመ ቃል ኪዳን ነው፡ በፍጹም እንደገና ጦርነት እንዳይፈጠር፣ በፍጹም እንደገና ጦርነት እንዳይፈጠር! የሰው ልጅን ሁሉ ዕጣ ፈንታ የሚመራው በሰላም እና በሰላም ነው”! ከሁሉም በላይ በአቶሚክ የጦር መሳሪያ ዘመን፣ የእውነት ማረጋገጫ ማለፍ አለበት፡ ሰላም የሚመነጨው በአቶሚክ የጦር መሣሪያዎች ሳይሆን የጦር መሳሪያ በመፍታት እና በማስፈታት ነው። ይህ እውነት፣ ባለፉት አስርት ዓመታት የኑክሌር የጦር መሣሪያ ማሽቆልቆልን ስናይ ግልጽ ሆኖ የታየው፣ ዛሬ በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ የጦር መሳሪያ ውድድር ተሸፍኗል። ዘፋኝ እና የዘፈን ግጥም ጸኃፊ ቦብ ዲላን፣ በአቶሚክ ቦምብ ላይ በምሳሌያዊ አነጋገር እንደጻፈው፣ በአንድ የግጥም ቅንብሮቹ ውስጥ፡- “ሰው ሰራሽና በሰው የሚዘወር ስለሆነ እጠላሃለሁ” በማለት መጽፉ ይታወሳል። ዛሬ፣ ቤተክርስቲያኗ በትህትና ለሁሉም ሰው ትኩረት ጥያቄ ታቀርባለች፡- የሰው ዘር በምድር ላይ መኖር መቀጠል አለበት? የሳይበር ጎራ እና የዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ውድድር አንድ ሰው ይህንን ጥያቄ በቁም ነገር እንዲጠይቅ ያነሳሳዋል።

ሰላም ምስክሮችን ይፈልጋል። የግጥም ታሪክ የቅኔና የሌሎችም ጽሑፎች ስብስብ ይህንን በብዙ ፊቶች ጥንካሬ ይጠቁመናል። የተጠቀሱት አሃዞች፣ ብፁዕ ፍሎሪበርት ብዋና ቹይ፣ እና የእግዚአብሔር አገልጋዮች ጆርጂዮ ላ ፒራ እና ዶርቲ ዴይ፣ የሙስና ፈተናን በማሸነፍ፣ ድሆችን በመርዳት፣ ዲፕሎማሲን በመደገፍ፣ በመጀመሪያ ደረጃ ሰላምን ያበረታቱ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ምሳሌዎች ናቸው። ከታዋቂ ወንዶችና ሴቶች ጋር፣ ሰላም የራሳቸውን ሕሊና የተከተሉ “ብዙም የማይታወቁ ዋና ዋና ገጸ-ባህሪያት” የተዋቀረ ነው።

ታሪክ ወደ ኑክሌር አደጋ እየተቃረብን እንደሆነ እያሳየን ይገኛል። መዛግብት እንደሚያሳዩት የአንድ ሰው የሶቪየት ባለስልጣን ስታኒስላቭ ፔትሮቭ ውሳኔ ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ጦርነትን ለማስወገድ አስተዋጽኦ አድርጓል። እ.አ.አ መስከረም 26 ቀን 1983 ዓ.ም. ነበር። ፔትሮቭ በተረኛነት ላይ በነበረበት በሞስኮ አቅራቢያ የሚገኘው የመከላከያ ምሽግ ራዳር ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ሶቪየት ህብረት በርካታ አህር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳኤሎች መተኮሳቸውን አመልክቷል። ሆኖም ግን፣ የሶቪየት የሳተላይት ማወቂያ ስርዓት ስህተት ነበር። ፔትሮቭ ትዕዛዞችን ባለመተግበሩ እና የተገመተውን ጥቃት ላለመዘገብ መርጧል። ይህ ቀላል እርምጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሞት ሊያስከትል እንደሚችል የሚያውቅ ሰው ሕሊና ወስኖ የተደረገ ውሳኔ ነበር። ምንም እንኳን ከእኛ የተራቀቁ እና ፈጣን ቢሆኑም፣ መከላከያ የሌላቸውን ሰዎች ቦምብ ለማፈንዳት የሚወስኑ ማሽኖች ያሉት ዓለም በእውነት አስፈሪ ይሆናል። የአንድ ሰው ሕሊና ለመላው ዓለም ዋጋ ሊኖረው ይችላል።

በመጨረሻም፣ ሰላም ተስፋን ይፈልጋል። ቤተክርስቲያን ለሁሉም ወንዶችና ሴቶች ስለፍቅር መስበኳን ትቀጥላለች። ዓለም ዛሬ የምትፈልገው አንድ ነገር ካለ፣ ለወደፊቱ የሰላም መልእክት እንደሆነ አምናለሁ። የኢየሱስ መልእክት ብቸኛው ምንጭ አድርገን ካገኘነው በኋላ የወደፊቱን በተስፋ እንመልከተው። ምክንያቱም የክርስቶስ ትምህርት ፍሬ ነገር ይህ ነው፡- ፍቅር፣ ልግስና እና ለሌሎች ሞትን እንዲያሸንፉ ሕይወትን መስጠት፣ ማግለልን፣ ዓመፅን ማሸነፍ፡- “እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ" (ዮሐ. 10፡10)።

በዓለም ላይ ከሚደረጉ ብዙ ጦርነቶች ፊት ለፊት ተስፋ ለመቁረጥ ፈተና ውስጥ ለሚወድቁ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒየስ 11ኛ ለመላው ቤተክርስቲያን ያቀረቡትን ግብዣ አቀርባለሁ፡- “በአሁኑ ጊዜ ባሉ ችግሮች መካከል እንድንኖር ስላደረገን እግዚአብሔርን እናመስግን። ከእንግዲህ ማንም ተራ እንዲሆን አይፈቀድለትም።” እግዚአብሔር ዓመፅ በሌለባቸው ጎዳናዎች ላይ ይምራን። አማኞችና መልካም ፈቃድ ያላቸው ሰዎች የሰላም ገንቢዎች ሆነው መሥራታቸውን አያቆሙም። እያንዳንዱ ሰው ሰላምን በሕይወቱ ዓላማ ያድርገው።

ከቫቲካን፣ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም.

 

22 Jul 2026, 16:11