የጳጳሱ የሰላም መጽሐፍ፣ የጳጳሱ የሞራል እንቅስቃሴን ሊያነሳሳ ይችላል መባሉ ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ እ.አ.አ በግንቦት 8/2025 ዓ.ም 267ኛው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ሲመረጡ፣ ለዓለም የተናገሩት የመጀመሪያ ቃላቶች ሰላም በሰዎች ልብ፣ በቤተሰቦቻቸው እና በአገራት ውስጥ ይሰፍን ዘንድ በተናገሩት ቃላት እና ባላቸው ፍላጎት ላይ ያተኮሩ ነበሩ።
ይህ ምኞት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሊቀ ጳጳሱ ንግግሮች፣ ስብከቶች እና ሰላምታዎች ውስጥ የማያቋርጥ ጭብጥ ሆኖ ቆይቷል፣ ምክንያቱም በዓለም ዙሪያ ያሉ ብዙ አገሮች በግጭቶች እና በውጥረት ውስጥ በአሁኑ ወቅት ተጠምደው እንደሚገኙ ይታወቃል።
አሁን የቫቲካን ማተሚያ ቤት ስለ ሰላም ሁሉንም ቃላቶቻቸውን እና ሀሳቦቻቸውን የሚሰበስብ አዲስ መጽሐፍ አውጥቷል፣ ይህም ስለ ሰላም ሁሉንም ቃላቶቻቸውን እና ሀሳባቸውን አሰባስቦ የያዘ “የጦር መሣሪያ ትጥቅ መፍታት እና ማስፈታት፡- ሰላም ስጦታ ነው” በሚል ርዕስ መጽሐፍ አስትሟል። ጥራዙ በጣሊያንኛ ቋንቋ ቢሆንም፣ በቅርቡ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ የሚተረጎም ሲሆን ቀደም ሲል በሊቀ ጳጳሱ የተጻፈውን መቅድም ወይም መግቢያ ጽሑፍ አካቶ ይዟል።
ቫቲካን ሬዲዮ ለመጽሐፉ ዝግጅት ኃላፊነቱን የወሰደውን ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ እና የቴሌቪዥን ዘጋቢ የሆነው አቶ አሌሳንድሮ ባንፊን አነጋግሯል። የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ መልእክት ኃይል በወንጌል ውስጥ እንዴት እንደሚገኝ እና ክርስቲያኖች ለተለዋዋጭ ዓለም ተስፋን እንዴት ማምጣት እንደሚችሉ አጉልተው ገልጸዋል።
“የዚህ መጽሐፍ ዓላማ ሁሉም ሰው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ስለ ሰላም ያስተማሯቸውን ትምህርቶች ግንዛቤ እንዲያገኙ እድል መስጠት ነው” ሲል አብራርቷል። መጽሐፉ በዚህ ጭብጥ ላይ የሊቀ ጳጳሱን ቁልፍ መልእክቶች በመጽሐፉ ጭብጥ ውስጥ በማደራጀት እና “በቅድስት መንበር እውቅና ከተሰጣቸው ተቋማዊ አካላት ወይም ለአለም የሰላም ቀን መልእክቱ፣ እስከ ደብር ጉብኝቶች ወይም በኢዮቤልዩ አመት ወቅት ከወጣቶች ጋር ባደረጉት ውይይት” ላይ ያሉትን ሁሉንም ንግግሮች በማካተት እንዴት ማቅረብ እንደሚፈልግ አጉልቶ አሳይቷል።
መጽሐፉ “የዚህን ጭብጥ ማዕከላዊነት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሊዮ አስተንትኖዎች ውስጥ ያጎላል። የተለያዩ ሁኔታዎች፣ የተለያዩ አፅንዖቶች፣ ግን አንድ አሳሳቢ ጉዳይ፡ ውይይትን መገንባት ወይም ማሳደግ፣ ከወዳጅ-ጠላት ማዕቀፍ በመላቀቅ ድልድዮችን መገንባት” ሲሉ አቶ ባንፊ ስለመጽሐፉ ውስጣዊ ይዘት አጥብቆ ተናግሯል።
የወንጌል ጥንካሬ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሊያነሳሳቸው የሚችለው እንቅስቃሴ
የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ቃላትና ሀሳቦች ለአለማችን በጣም አስፈላጊ ውሳኔዎችን ለሚወስኑ ሰዎች እንዴት ሊደርሱ እንደሚችሉ ሲጠየቁ፣ አቶ ባንፊ ይህ “አስቸጋሪ ጥያቄ” መሆኑን አምነዋል።
“የሶቪየት አምባገነን የነበሩት ጆሴፍ ስታሊን በአንድ ወቅት ‘ጳጳሱ ስንት ወታደራዊ ክፍሎች አሉት?’ በማለት በፌዝ መጠየቁን ያስታወሱት አቶ ባንፊ፤ ዛሬም መልሱ አንድ ነው፡ የለም” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
“ቫቲካን ትልቅ የዲፕሎማሲ ቡድን እንዳላት እና ቤተክርስቲያን በዓለም ዙሪያ ሚስዮናውያን እንዳሏት፣ ነገር ግን በጦር መሣሪያ የታጀበ ኃይል እንደሌላት" አስተውለዋል።
“የጳጳሱ መልእክት እና የአለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ኃይል በወንጌል ውስጥ እንዳለ” አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩት አቶ ባንፊ “የጦር መሣሪያ ትጥቅ የፈታ እና የሚፈታ ኃይል ነው፣ በዓመፅ እና በጦርነት ፊት ለመሸነፍ የታለመ ይመስላል። ሆኖም የዚህ ዓለም ኃያላን የክርስቶስ ተወካይ አገልጋይ ምን ዓይነት የሞራል ማነሳሳት ሊያነሳሳ እንደሚችል በሚገባ ያውቃሉ፣ እናም በዚህ ምክንያት የእሱን ፍርድ ይፈራሉ” ሲሉ ተናግረዋል።
የአንድ ሰው ሕሊና ለመላው ዓለም ዋጋ ሊኖረው ይችላል።
በዚህ ረገድ፣ በመግቢያ ጹሑፋቸው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሰላም የግለሰብ ኃላፊነት እንዴት እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተው ለእያንዳንዳችን በመናገር ይጀምራሉ።
አንድ የሶቪየት ባለስልጣን ስታኒላቭ ፔትሮቭ እ.አ.አ በ1983 ዓ.ም ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ሶቪየት ህብረት በርካታ አህጉር አቋራጭ ባሌስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሱን የሚያመለክቱ የሩሲያ ራዳሮችን ምላሽ ባለመስጠት የኑክሌር አደጋን ለማስወገድ አስተዋጽኦ ያደረገበትን ታሪካዊ ክስተት ጠቅሰዋል። ስርዓቱ በእርግጥም ችግር አጋጥሞታል፣ እና ምንም ሚሳኤሎች አልተተኮሱም ነበር ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ ክፍል “የአንድ ሰው ሕሊና ለመላው ዓለም ዋጋ ሊኖረው እንደሚችል” ያሳያል ብለዋል፣ እና አቶ ባንፊ በትክክል “ተስፋ የሚሰጠን ይህ ግንዛቤ” መሆኑን ገልጸዋል።
“የሰላምን የወደፊት ሕይወት ለመገመት ትክክለኛውን አመለካከት የሚሰጠን በሰው ልብ እና አእምሮ ውስጥ ያለው ይህ እምነት ነው። የጦርነት፣ የጥላቻ እና የዓመፅ ፍጻሜ የሚጀምረው በእኔ፣ በቤቴ፣ በባልደረቦቼ እና በጎረቤቶቼ መካከል ነው” ብለዋል አቶ ባንፊ።
ስለ ተስፋ ስንናገር፣ ለአቶ ባንፊ ክርስቲያኖችን ከሌሎች የሚለየው ይህ ነው፣ በእግዚአብሔር ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው ነው።
በዚህ ረገድ የቅዱስ አውጎስጢኖስን መጽሐፍ በላቲን ቋንቋ "ዴ ቺቪታቴ ዴይ" (“የእግዚአብሔር ከተማ”) ጠቅሶ እነዚህ ሁለት ቦታዎች እርስ በርስ እንዴት እንደሚተሳሰሩ ገልጿል።
“አንድ ላይ ያድጋሉ፣ ነገር ግን ልዩነቱ ሙሉ በሙሉ በተስፋ ላይ የተመሰረተ ነው። የምድራዊቷ ከተማ ሰዎች፣ ቅዱስ አውጎስጢኖስ እንደሚለው፣ በነገሮች ባለቤትነት ደስታን ይፈልጋሉ። የእግዚአብሔር ከተማ ሰዎች ደስታን የሚያገኙት በላቲን ቋንቋ “spei dei” በሚለው ቃል ሲሆን ትርጉሙም የእግዚአብሔር ተስፋ፣ እግዚአብሔር ድንቅ ማለት ነው።
የቅዱስ አውጎስጢኖስ ተጽዕኖ
አቶ ባንፊ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጽሑፎችን በማጣራት ሂደት ውስጥ “የቅዱስ አውጎስጢኖስ ታሪክ እና የፖለቲካ ኃይል አመለካከት ባለው ተጽእኖ” በጣም እንደተደነቁ ተናግረዋል።
“ከአስደሳቹ ንግግሮች አንዱ እ.አ.አ በጥር 9/2026 ዓ.ም በቅድስት መንበር እውቅና ለተሰጣቸው የዲፕሎማቲክ ልዑክ ቡድን አባላት ያደረጉት ንግግር መግለጽ ይቻላል። በዚህ ንግግር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በላቲን ቋንቋ "ዴ ቺቪታቴ ዴይ"ን (የእግዚአብሔር ከተማ) በሰፊው ጠቅሰው ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ የእግዚአብሔር ከተማ የፖለቲካ ችግር እንደማታመጣ ተናግረዋል” ሲሉ አቶ ባንፊ አስረድተዋል።
“ይልቁንስ፣ በሕዝቦች መካከል የበለጠ ፍትሃዊ እና ሰላማዊ አብሮ የመኖር ፍላጎትን የመሳሰሉ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሕይወት ላይ ባሉ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ነጸብራቅ ይሰጣል” ሲሉ ተናግረዋል።
“ይህ ጥቅስ ለእኔ የቅዱስ አውጎስጢኖስን ራዕይ እና በምንኖርባቸው ማህበረሰቦች ውስጥ የካቶሊኮችን ኃላፊነት ያብራራል” ካሉ በኋላ አቶ ባንፊ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።
