ፈልግ

የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የደቡባዊ ሊባኖስ መንደር በሆነችው አይን ባአል  የደረሰ ውድመት የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የደቡባዊ ሊባኖስ መንደር በሆነችው አይን ባአል የደረሰ ውድመት  (AFP or licensors)

በሊባኖስ ድንበር ተሻጋሪ ጥቃቱ በድጋሚ መቀስቀሱን ተከትሎ እስራኤል የሊባኖስን በርካታ አካባቢዎችን ማጥቃቷ ተነገረ

የእስራኤል ጦር ለደቡብ ሊባኖስ ነዋሪዎች እና ለቤካ ሸለቆ ነዋሪዎች አዲስ የመልቀቂያ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተከትሎ ሃገሪቷ የሂዝቦላህ መገኛዎች ናቸው ያለቻቸውን ቦታዎች ኢላማ በማድረግ በሊባኖስ ላይ አዲስ የአየር ድብደባ መፈጸሟ ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የእስራኤል ጦር ለደቡብ ሊባኖስ እና ለቤካ ሸለቆ ነዋሪዎች አዲስ የመልቀቂያ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን መገኛ ናቸው ተብለው በሚታመኑ ቦታዎች ላይ ያነጣጠረ አዲስ የአየር ድብደባ መፈጸሙ ተነግሯል።

ቀደም ሲል በተደረጉ ጥቃቶች የዜላያ ማዘጋጃ ቤት ኃላፊ አሊ ቃሴም አህመድ እና ሶስት የቤተሰቡ አባላትን ጨምሮ ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን፥ ይህ ጥቃት በምዕራብ ቤካ በምትገኘው ዜላያ መንደር በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ላይ መፈጸሙን እና በጥቃቱ ሌሎች ሶስት ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።

የእስራኤል ጦር በሊባኖስ የተለያዩ ስፍራዎች ከሰኞ ማለዳ ጀምሮ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ወደ 25 የሚጠጉ ቦታዎችን መደብደቡን እና እነዚህ ስፍራዎች ሂዝቦላ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው መዋቅሮች እንደሆኑም ጭምር ገልጿል።

ረቡዕ ማለዳ ላይ ሂዝቦላህ የሚፈነዳ ሰው አልባ አውሮፕላኑን ወደ እስራኤል ማስወንጨፉን እና በድንበር አካባቢ ወድቆ መፈንዳቱን የእስራኤል ጦር ያስታወቀ ሲሆን፥ ቡድኑ በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሮኬቶችን አስወንጭፎ ሁለት የእስራኤል ወታደሮችን ማቁሰሉን እና ሄዝቦላህ ጥቃቶቹን የፈጸመው ባለፈው ወር ተግባራዊ የሆነውን ደካማውን የተኩስ አቁም ስምምነትን እስራኤል በመጣስዋ ምክንያት የበቀል እርምጃ እንደሆነ ገልጿል።

በሌላ ዜና የሶሪያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠረ ትልቅ የአሸባሪዎች ሴራ ማክሸፉን እና ከሂዝቦላ ጋር ግንኙነት አለው የተባለውን ሴል ማፍረሱን የገለጸ ሲሆን፥ ሚኒስቴሩ በደማስቆ፣ አሌፖ፣ ሆምስ፣ ታርቱስ እና ላታኪያ ላይ በአንድ ጊዜ በተደረገ ዘመቻ በርካታ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

08 May 2026, 14:58