ፈልግ

በቶልኪን ድርሰት ውስጥ የተጠቀሰው መዝሙር ትህትናን እና ምህረትን እንደሚያስተምር ተገለጸ በቶልኪን ድርሰት ውስጥ የተጠቀሰው መዝሙር ትህትናን እና ምህረትን እንደሚያስተምር ተገለጸ 

በቶልኪን ድርሰት ውስጥ የተጠቀሰው መዝሙር ትህትናን እና ምህረትን እንደሚያስተምር ተገለጸ

የጣሊያኑ ‘ላ ኦዘርቫቶሬ ሮማኖ’ ጋዜጣ ዳይሬክተር ከዛሬ ሰባ ዓመታት በፊት በካቶሊካዊ ደራሲ የተፃፈውን ‘ዘ ሎርድ ኦፍ ዘ ሪንግስ’ የተሰኘውን መጽሃፍ አስመልክቶ እንደተናገሩት ይህ ድርሰት አሁን ላለንበት የፖለቲካ አውድ ጥሩ የመነሳሻ ምንጭ እንደሆነ አመላክተዋል።

አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

እ.አ.አ. ከሰባ ዓመታት በፊት፣ ጥር ወይም የካቲት 1956 ዓ.ም. ላይ ‘ዘ ሎርድ ኦፍ ዘ ሪንግስ’ የተሰኘው መጽሃፍ ደራሲ የሆነው እንግሊዛዊው ጸሐፊ እና የፍልስፍና ሊቅ ቶልኪን ‘ኒው ሪፐብሊክ’ ለተሰኘው መጽሄት ዋና አርታኢ ለሆነው ሚካኤል ስትሬት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ከተወሰኑ ጊዜያት ቀደም ብሎ ከጋዜጣው አዘጋጅ ክፍል የተቀበለው ደብዳቤ “አስፈሪ” ይዘት ያለው መሆኑን የጠቀሰ ሲሆን፥ አዘጋጁ በበኩሉ የሎርድ ኦፍ ዘ ሪንግስ የተሰኘው መጽሃፍ ዋና ገፀ ባህሪ የሆነው ፍሮዶ በድርሰቱ ላይ እንደ ከሃዲ መገደል የነበረበት እንጂ ሊወደስ እንደማይገባው የተከራከረ ሲሆን፥ ቶልኪን ለዚህ ሃሳብ ሲመልስ “የዓለም 'ድነት' እና የፍሮዶ 'ድነት' የሚሳካው በቀድሞው ርህራሄው እና ላደረሰው ጉዳት በሚጠይቀው ይቅርታ” መሆኑን አስረድቷል።

አሁን፣ ከሰባ ዓመታት በኋላ፣ የቅጂ መብት ጊዜው በሚያበቃበት እና የአጥፊዎች ፍርሃት በጠፋበት በአሁኑ ወቅት ስለ ልብ ወለዱ በጣም ዝነኛ ጭብጦችን በነፃነት መናገር እንደሚቻል የገለጸው የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊ የሆነው አንድሪያ፥ ቀለበቱን ‘ማውንት ዶም’ ወደተሰኘው እሳታማ ተራራ የጣለው ክቡር ፍሮዶ ሳይሆን፣ የታሪኩ እጅግ አስፈሪ እና ጎስቋላ ገፀ ባህሪ የሆነው ‘ተንኮለኛው’ ጎለም እንደሆነ በመግለጽ፥ ይህ ክስተት የቶልኪንን ድርሰት ድንቅ ሥራ ከሚያስብሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ማለትም መጋቢት 16 ላይ ስለዚህ ጉዳይ መናገር ትክክል እንደሆነ የጠቀሰው አንድሪያ፥ ይህ ቀን በልብ ወለዱ ውስጥ ቀለበቱ በጎልም ወደ እሳት የተጣለበት ቀን እንደሆነ አስረድቶ፥ ቀለበቱ በሚጠፋበት ወቅት የመካከለኛው ምድር ኃያል እና የጨለማ አምላክ የሆነው የሳሮን ግዛት የሚያበቃበት ጊዜ መሆኑን ጠቅሶ፥ በዚህ ጉልህ በሆነ ቀን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትሑቷ የናዝሬት ሴት የሆነችው ማርያም ለሰማችው የምስራች ቃል ‘ፍቃዷን’ የገለጸችበትና በዚህም ታሪክ እንዲገለበጥ እና ልጇ ክርስቶስ በሰይጣን እና በክፉ ሥራው ላይ ድል እንዲቀዳጅ ያስቻለበት ቀን በመሆኑ ዕለቱን በመታሰቢያነት የምታከብረው መሆኑን ገልጿል።

በቶልኪን ልብ ወለድ አንዱ ክፍል ውስጥ የተጠቀሰውን እና በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ ቁጥር 52 ላይ የተጠቀሰውን “ኃያላንን ከዙፋናቸው አወረደ፣ ትሑታንንም ከፍ ከፍ አደረገ” የሚለውን መዝሙር የዘመረችው የገሊላዋ ትሁት እመቤታች ቅድስት ድንግል ማሪያም መሆኑን ያስታወሰው አንድሪያን፥ በአጠቃላይ ልብ ወለዱ ውስጥ የሰው ልጅን ግማሽ አምሳያ ወክለው የተገለጹት ገጸ ባህሪያት በዚህ የወንጌል ክፍል ታላላቅ ኃይሎች ራሳቸውን አቅመ ቢስ አድርገው እንደሚገልጡ፣ ደካማዎቹ ደግሞ እራሳቸውን እንደ እውነተኛ አሸናፊዎች አድርገው የሚገለጡበትን መልዕክት እንደሚወክሉ አስታውሷል።

ታሪኩን በአዎንታዊ መልኩ የሚፈታው ጉልበት ሳይሆን ቃል በቃል “መታመን” መሆኑን ጠቅሶ፥ በኅብረት የተዋሃዱት ዋና ገፀ-ባህሪያቱ የጦር መሳሪያን በማውረድ እና እጅ ለእጅ በመያያዝ በጣም አጥፊ የሆነውን መሣሪያ እንደሚያስወግዱ፣ እንዲሁም ማለቂያ የሌላቸውን የጦርነቶች ሰንሰለት፣ የኃይል ድግምትና የገዢነት ፍላጎትን እንደሚሰብሩ ገልጿል።

አሸናፊዎች በጣም ጠንካራ ወይም በጣም እብሪተኛ የሆኑ ሰዎች ሳይሆኑ ትሑት የሆኑ ሰዎች መሆናቸውን የገለጸው አንድሪያን፥ በራሳቸው ላይ መቀለድ የሚችሉ እና የራሳቸውን ሃሳብ እና ፍላጎት ሳይሆን የተሻለውን ሃሳብ እና ሙሉ በሙሉ እንኳን የማይረዱትን ተልዕኮ ማገልገል የሚችሉ ሰዎች አሸናፊ እንደሆኑ አስረድቷል።

ይህ ተልዕኮ የሚሳካው በታላላቅ ጀግኖች ስለተፈጸመ ሳይሆን በቆራጥ፣ ግልጽ እና ሁሉን አቀፍ በሆኑ ኩባንያዎች የሚፈጸም በመሆኑ፣ ጨካኝ እና ውጤታማ ወታደሮችን ከመምረጥ ይልቅ ንቁ የሆኑ መንፈሳዊ ነጋዲያንን በመምረጥ እንደሆነ የገለጸው አንድሪያን፤ በሁሉም ረገድ የተለያዩ ጎሳ፣ ተሰጥዖ፣ የዘር ሐረግ፣ ታሪካዊ አመጣጥ እና ከሁሉም በላይ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች አብረው ሲራመዱ እና ሲተባበሩ መሆኑን ገልፆ፥ ልዩነት ሀብት፣ ብዝሃነት ደግሞ ጥበብ መሆኑን እና አሳታፊነት ወደ ድል የሚያደርሰው መንገድ መሆኑን ገልጿል።

ከምናባዊ ልብ ወለድ በላይ የሆነው የቶልኪን ድንቅ ሥራ ከሰባ ዓመታት በላይ የሰው ልጅን እንቅስቃሴ ሁሉ በመዳሰስ የትውልድን አስተሳሰብ ለመቅረጽ እንደረዳ እና ፖለቲካ በቶልኪን የትረካ ኃይል በጤናማ ሁኔታ ተጽዕኖ ማሳደሩ በእርግጥም የሚፈለግ እንደነበር የገለጸው አንድሪያን፥ በአሁኑ ዘመን የፖለቲካ ፋሽን ውስጥ የሚስተዋለውን ስልጣንን በጉልበት የማግኘት አባዜን የሚያስወግደውን የገጸባህሪዎቹን ጥበብ መማር ቢቻል መልካም እንደሆነ አስታውሶ፥ በተመሳሳይ ሁኔታ የተለያዩ ሰዎችን በማሰባሰብ እና መሳሪያዎቻቸውን እንዲያወርዱ በማሳመን፣ እብሪተኛ ከመሆን ይልቅ የትህትናን መንገድ በመከተል የጋንዳልፍን ጥበብ መማር እንደሚገባ መክሯል።

በጽንፈኝነት ምክንያት በተፈጠሩ ግጭቶች በተከፋፈለው እና በተለያየው በዛሬው ዓለማችን እርስ በርስ የሚጋጩ ወገኖችን ለማስታረቅ የሽምግልናን ውበት እና ጥቅም እንደገና ማግኘት እንደሚገባ ያስታወሰው አንድሪያን፥ ከቶልኪን ራዕይ መነሳሳትን ማግኘት እና ቋንቋውንም መቀበል ብንችል መልካም እንደሆነ አስረድቷል

የአመራር ጽንሰ-ሀሳብን እንደገና መለስ ብሎ ማየት ለሚችል ፖለቲካ ትክክለኛው ሃሳብ በጉልበት ከላይ በመሆን መምራት፣ መቆጣጠር እና “ማስገደድ” ሳይሆን፥ በትክክል “በሕዝቡ መካከል” መሆን፣ የተራው ሰው የህይወት ጉዞ አጋር መሆን እና በምሕረት እይታ ማየት እንደሚገባ ያሳሰበው አንድሪያን፥ የዛሬው ዘመን ፖለቲካ ከመቼውም ጊዜ በላይ የቶልኪን እና የታላላቅ ሥራዎቹ ቀናተኛ አንባቢዎች የመሆንን ተነሳሽነት እንደሚፈልግ በመግለጽ አጠቃሏል።

 

 

 

26 Mar 2026, 15:44