ፈልግ

የእስራኤል ወታደራዊ ቡልዶዘሮች በዌስት ባንክ በሚገኘው የኑር ሻምስ የፍልስጤም የስደተኞች ካምፕ አቅራቢያ ሲነዱ የእስራኤል ወታደራዊ ቡልዶዘሮች በዌስት ባንክ በሚገኘው የኑር ሻምስ የፍልስጤም የስደተኞች ካምፕ አቅራቢያ ሲነዱ  (AFP or licensors)

በዌስት ባንክ በሠፋሪዎች ላይ የሚፈጽም ጥቃት በ25% መጨመሩ ተገለጸ

የእስራኤል የመከላከያ ኃይል ሪፖርት ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ ዓመት 2025 ዓ. ም. በዌስት ባንክ ነዋሪዎች ላይ የተፈጸመ ጥቃት ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

 በጋዛ ሰርጥ የሲቪሎች ሞት የቀጠለ ሲሆን ሰኞ ዕለት የእስራኤል ድሮኖች በካን ዩኒስ በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ሁለት ሕጻናት በብርድ ተሰቃይተው መሞታቸው ታውቋል። በተመሳሳይም በዌስት ባንክ ሠፋሪዎች ላይ በሚሰነዘር ጥቃት ምክንያት ውጥረት እያየለ መምጣቱ ታውቋል።

እስራኤላውያን በፍልስጤማውያን ላይ የሚፈጽሟቸው ብሔረተኛ ወንጀሎች ቁጥር እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከጥቅምት 7/2023 ዓ. ም. ጀምሮ ያለማቋረጥ የጨመረ ሲሆን በጊዜው የተመዘገበው ጠቅላላ ቁጥር 1,720 መድረሱ ተገልጿል።

እነዚህ አሃዞች በእስራኤል የመከላከያ ኃይሎች (IDF) የወጡ ሲሆን የእስራኤል ጋዜጣ ሃሬትዝ መዘገቡም ታውቋል።

እንደ የዜና ማሰራጫው ዘገባ ከሆነ አዝማሚያው የአካባቢውን ደህንነት እና መረጋጋት እያበላሸው እንደሆነ እና ፖሊስ ችግሩን ለመፍታት በቂ ጥረት እያደረገ እንዳልሆነ ተገልጿል።

እስራኤል የጦር ወታደሮቿን ለመላክ እያሰበች ነው

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2025 ዓ. ም. ሠፋሪዎች 200 ሰዎችን በማቁሰል አራት ሰዎችን ገድለዋል በሚል 845 ብሔረተኛ ወንጀሎች መፈጸማቸው ተዘግቧል።

ይህ በ2024 (እ.አ.አ) ከተፈጸሙ 675 ጥቃቶች ጋር ሲነጻጸር በ25% ገደማ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በጥቃቶቹ 149 ፍልስጤማውያን መቁሰላቸው እና ስድስት መገደላቸው ታውቋል።

እንደ ተንታኞች ከሆነ የክስተቶቹ መጨመር ከፍተኛ የጦር አዛዦች ፖሊስ ሁኔታውን ለመቆጣጠር ባለው አቅም ጥርጣሬን ሊያሳድር እንደሚችል አስረድተዋል።

ጥቃቶቹ ከቀጠሉ ሠራዊቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን መደበኛ እና ተጠባባቂ ወታደሮች ቡድን ወደ ክልሉ መላክ ሊያስፈልገው ይችላል።

በጋዛ የሰላም እቅድ በደረጃ 2 ላይ የተጠቀሰ የመደራደሪያ ነጥብ መሠረት የሃማስ ልዑክ የተኩስ አቁም ስምምነት አፈፃፀም ላይ ለመምከር በግብፅ እንደሚገኝ እና እንዲሁም ክህሎት ያለው ነጻ የፍልስጤም የቴክኒክ ኮሚቴን ለመመሥረት ይወያያሉ።

የሰላም ምክር ቤቱ ሂደቱን በበላይነት እየመራ ሲሆን ውሳኔውን መጭው ማክሰኞ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተጨማሪ የጣሊያን፣ የታላቋ ብሪታንያ፣ የጀርመን፣ የኳታር፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና የግብፅ የክልል ወይም የመንግሥት መሪዎችን ያካትታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩኒሴፍ ቃል አቀባይ ጄምስ ኤልደር ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፥ የተኩስ አቁሙ ስምምነት ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ 100 ሕጻናት በእስራኤል ወረራ መገደላቸውን አስታውቀዋል።

 

15 Jan 2026, 13:25