ፈልግ

Cookie Policy
The portal Vatican News uses technical or similar cookies to make navigation easier and guarantee the use of the services. Furthermore, technical and analysis cookies from third parties may be used. If you want to know more click here. By closing this banner you consent to the use of cookies.
I AGREE
የእምነት እና የስነምግባር ማህበረሰቦች የአፍሪካ እና የዲያስፖራ ስብሰባ በአዲስ አበባ የእምነት እና የስነምግባር ማህበረሰቦች የአፍሪካ እና የዲያስፖራ ስብሰባ በአዲስ አበባ  (SECAM)

የእምነት ማህበረሰቦች አዲስ አበባ ከተሰበሰቡ በኋላ በአፍሪካ ፍትህ እንዲሰፍን እርምጃ ሊወስዱ ነው።

በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የተጠናቀቀውን የእምነት እና የስነ-ምግባር ማህበረሰብ አውደ ጥናት ተከትሎ ከአፍሪካ እና ከዲያስፖራ የተውጣጡ የእምነት እና የስነ-ምግባር ማህበረሰቦች የአቋም መግለጫ ተፈራርመው ለአህጉሪቱ ፍትሃዊ የጉዳት ካሳ እንዲደረግላት እና ፍትህ እንዲሰፍን በመምከር የውይይቶቹን ውጤት ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸው ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ከአፍሪካ እና ከዲያስፖራ የተውጣጡ እምነት እና ስነ-ምግባር ያላቸው ማህበረሰቦች በቅርቡ በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የተካሄደውን ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ ለአፍሪካ ሀገራት እና ለአፍሪካ ተወላጅ ህዝቦች ፍትሃዊ የጉዳት ካሳ እንዲደረግ በምያሳስብ ጭብጥ ላይ ያተኮረ ጉባኤ መሆኑን ተከትሎ ተጨባጭ እርምጃዎችን ወስደዋል።

የጉባኤው አባል የሆኑት አባ ስቴፈን ኦኬሎ እንዳሉት ከሆነ ልዑካኑ ለትግበራ እና ለአለም አቀፍ እርምጃ የምወስድበት ጊዜው አሁን ነው ብለዋል ።

መግለጫው በከፊል “ጉባዔው ሲጠናቀቅ፣ የአዲስ አበባው የፍትሃዊው ካሳ ጥያቄ መግለጫ መጽደቁ ገና ጅምር መሆኑን ተናጋሪዎች አጽንኦት ሰጥተው የገለጹ ሲሆን የውሳኔ ሃሳቦችን ወደ ተግባር ለመተርጎም ከአፍሪካ ህብረት፣ ከዩኔስኮ (ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት)፣ ከጋና መንግስት፣ ከክልላዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች (RECs)፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ አለምአቀፍ ተቋማት እና መሰረታዊ ንቅናቄዎች ጋር ለመቀጠል ቁርጠኛ የሆኑ አስተባባሪ አካላት እንደ ተዋቀሩም ተገልጿል።

ከፍተኛ ባለስልጣናትን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ ምሁራንን እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨምሮ ወደ 100 የሚጠጉ ተሳታፊዎችን ባሰባሰበው ጉባኤው እምነትን መሰረት ያደረጉ ተቋማት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍትህን የሚያበረታቱ የካሳ እና የፖሊሲ ማሻሻያዎችን የመምከር የሞራል ግዴታ ላይ አጽንኦት ሰጥተው ተወያይተዋል።  ተሳታፊዎቹ በጽናት ለመቀጠል እና ለአፍሪካውያን እና ለአፍሪካውያን ተወላጆች ፍትህ ለአለም አቀፍ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ለማረጋገጥ በትብብር ለመስራት ቆርጠዋል።

ከየካቲት 20-21/2017 በአዲስ አበባ በኩሪፍቱ ሪዞርት አፍሪካ መንደር እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የተካሄደው የሁለት ቀናት ስብሰባ “የእምነት ማህበረሰቦች እና የስነ-ምግባር ድርጅቶች ሚና ለአፍሪካውያን እና የአፍሪካ ተወላጆች ፍትሃዊነትን በማካካስ” በሚል መሪ ቃል ነበር የተከናወነው።

ማካካሻ ከሙዋለ ነዋ ማካካሻ ባሻገር ነው

ማካካሻ ከገንዘብ ማካካሻ ባሻገር ሰፋ ያሉ ጥረቶችን ያጠቃልላል። በአዲስ አበባው ኮንፈረንስ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች እንዳሉት “የገንዘብ ማካካሻ ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ እውነቶችን መቀበል፣ ዕርቅን መፍጠር እና ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መረዳጃ መንገዶችን መፍጠር ነው” ብለዋል።

ክርክሩ እየተፋፋመ በሄደ ቁጥር ተሳታፊዎቹ እንዳሉት፣ ዓለም እነዚህ የፍትህ ጥሪዎች ትርጉም ያለው እርምጃ ይወሰድ እንደሆነ ለማየት ይከታተላል።

የአዲስ አበባ መግለጫ መፈረም

ለሁለት ቀናት ከተካሄደው ስብሰባ ዋና ዋና ውጤቶች መካከል አንዱ የአዲስ አበባን የካሳ መጠየቂያ መግለጫ መፈረም ሲሆን ይህም ለአፍሪካውያን ትልቅ ርምጃ ሲሆን ይህም ለታሪካዊ ኢፍትሃዊነት፣ ፍትህን ለመፈለግ መደበኛ ቁርጠኝነትን የሚያመለክት ሲሆን በአትላንቲክ፣ ትራንስ-አትላንቲክ የባሪያ ንግድ፣ ባርነት፣ ቅኝ ግዛት እና በአፍሪካ አህጉር እድገት ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ያለው ስርአታዊ ኢፍትሃዊነት ነው ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።

መግለጫው የእምነት ማህበረሰቦች ሰላምን፣ እርቅን እና እውነተኛ ፍትህን በማስፈን፣ ከአፍሪካ አጀንዳ 2063 ለበለፀገ እና ለተባበረ አህጉር ጋር በማስማማት ያላቸውን ሚና አፅንዖት ሰጥቷል።

ከተፈረመበት መግለጫ በኋላ ተሳታፊዎቹ የአፍሪካ ህብረት የመልሶ ማቋቋም የፍትህ ስርዓትን ለማጎልበት የአፍሪካ ህብረት የባለሙያዎች ኮሚቴ ለማቋቋም በጉጉት ይጠባበቃሉ። በአለም አቀፍ ደረጃ የአፍሪካ እና የዲያስፖራ ካሳን ለመደገፍ የአፍሪካ ህብረት ልዩ ልዑካን ለመሾም መንገድ ከፍቷል።

በተጨማሪም ታሪካዊ ኢፍትሃዊነትን ለመቅረፍ መደበኛ እና የጋራ ቁርጠኝነት “የሥነ-ምህዳር ዕዳን እንደ ማካካሻ የንግግሩ አካል እውቅና መስጠቱን ፣ በቅኝ ግዛት ዘመን ብዝበዛ ያስከተለውን የአካባቢ ጉዳት አምኖ እና የአፍሪካ ህብረት ለዚህ ዓላማ ቀጣይነት ያለው የአስር አመት ካሳ ማወጅ እንዲያስብበት የቀረበ ሀሳብ ነው ።

አውደ ጥናቱ የተካሄደው የአፍሪካ እና የማዳጋስካር ኤጲስ ቆጶስ ጉባኤዎች ሸንጎ (በሴካም) ፣ በአፍሪካ ኅብረት የካቶሊክ ምዕመናን ሐዋርያዊ እንክብካቤ ሰጪ ተቋም፣ የሰማያዊ ባህል ፣ የዓለም ሰላም ፣ የብርሃን መልሶ ማቋቋም (HWPL) ፣ በስነ-ምግባር እና በስነ-ሕይወት ሥነ-ምግባር የፓን አፍሪካ ጉባኤ፣ (COPAB) ፣ የሰላም እና ልማት የሃይማኖት ተቋማት ሕብረት ማህበር (IAPD-አፍሪካ) ፣ የተባበሩት ሃይማኖቶች ተነሳሽነት (URI) እና ሌሎች የአፍሪካ ቁልፍ አጋሮች ከዜጎች እና ዲያስፖራ ህብረት ዳይሬክተር ጋር በመተባበር ነው።

 

06 Mar 2025, 15:30
Prev
March 2025
SuMoTuWeThFrSa
      1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031     
Next
April 2025
SuMoTuWeThFrSa
  12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930