ፈልግ

በጋዛ የሚኖር ፍልስጤማዊ ክርስቲያን የተገደሉ ልጆቹን በገና በዓል ወቅት ሲያስታውሳቸው በጋዛ የሚኖር ፍልስጤማዊ ክርስቲያን የተገደሉ ልጆቹን በገና በዓል ወቅት ሲያስታውሳቸው 

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለጋዛ ነዋሪዎች የሚያደርሰው ዕርዳታ ሊቋረጥ መቃረቡን አስታወቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሁለቱም ማለትም የእስራኤል ወታደሮች እና የፍልስጤም ዘራፊዎች ሆን ብለው በሚፈጽሙት የማደናቀፍ እና የመበታተን ተግባር ምክንያት በጋዛ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ዕርዳታን የማድረሱ ሥራ እየከፋ እንደሚሄድ አስጠንቅቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሁለቱም ማለትም በእስራኤል ወታደሮች እና በፍልስጤም ወንበዴዎች ሆን ተብሎ በሚፈጸም የማበላሸት እና የመበታተን ተግባር ምክንያት በጋዛ ለሚገኙት ችግረኞች የሚያቀርበው ዕርዳታ ሊቋረጥ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ እና የአደጋ ጊዜ ዕርዳታ አስተባባሪ አቶ ቶም ፍሌቸር፥ በጋዛ ውስጥ ከሞት ለተረፉት ሰዎች ምግብ፣ ውሃ እና መድሐኒት ለማድረስ ቁርጠኝነት ቢኖርም ይህ ሕይወትን ለማዳን የሚያደርገው ጥረት እንቅፋት እያጋጠመው እንደሚገኝ ተናግረዋል። “ትርጉም ያለው ሕዝባዊ ስርዓት የለም” ያሉት ምክትል ዋና ጸሐፊው፥ የእስራኤል ወታደሮች የዕርዳታ ሠራተኞቻቸውን ደህንነት ማረጋገጥ አልቻሉም ወይም አይፈልጉም” ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ጸሐፊው፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የረድኤት ሠራተኞች ወታደራዊ ጥቃት ቢደርስባቸውም የእስራኤል ባለስልጣናት መግለጫዎች ይህን እንደሚያስተባብሉ ገልጸው፥ በሌሎች አጋጣሚዎችም “እስራኤል የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አቶ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የመካከለኛው ምስራቅ መልዕክተኛ እጩነታቸውን አትቀበልም” ብለዋል።

አቶ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የቀድሞውን የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ፔካ ሃቪስቶን በእጩነት ቢያቀርቡም እስራኤል ሹመቱን በመከልከል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሌሎችን እጩዎች ስም ዝርዝር እንዲሰጥ መጠየቋ ታውቋል።

የእስራኤል ሚዲያ በዘገባው፥ ይህ የሆነው አቶ ፔካ ሃቪስቶ ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ባላቸው የጠበቀ ግንኙነት “ሁለት መንግሥታት” የሚለው የመፍትሄ ሃሳብ ተግባራዊ እንዲሆን በመደገፋቸው እና ቀደም ሲል ስለ እስራኤል በሰጡት ወሳኝ መግለጫዎች ምክንያት እንደ ሆነ አስታውቋል።

በሌላ በኩል፥ የፍልስጤም አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 28 በመቶ የቀነሰ ሲሆን፥ የሥራ አጥነት መጠን ባለፈው ዓመት እስከ 51 በመቶ መድረሱ ታውቋል።

በራማላህ የሚገኘው የኢኮኖሚ ሚኒስቴር፥ “በጋዛ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የፍልስጤም ኢኮኖሚ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ አስደንጋጭ ሁኔታ ገጥሞታል” ሲል አስታውቋል።

 

08 January 2025, 15:12