የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እሁድ ይጀምራል
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በሁለቱም በእስራኤል እና በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም ስምምነት መደረጉን የሚገልጽ ዜና ከተሰማ በኋላ በሁለቱም ወገን በሚገኙ ሕዝቦች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ደስታ ፍጥሯል። ስምምነቱ የተደረሰው በዶሃ ከፍተኛ ድርድር ከተደረገ በኋላ ነው።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
እስራኤል እና ሃማስ በኳታር፣ በግብፅ እና በዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የሽምግልና ጥረት ካደረጉ በኋላ የጋዛን የተኩስ አቁም ስምምነት እውን እንዲሆን ተስማምተዋል።
የስምምነቱ ትግበራ እሁድ ጥር 11 ይጀምራል።
በስምምነቱ መሰረት ሃማስ በመጀመርያ ምዕራፍ 33 የእስራኤል ታጋቾችን እንደሚፈታ የገተገለጸ ሲሆን በሚቀጥሉት ስድስት ሳምንታት ውስጥ ደግሞ እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን ለመልቀቅ ተስማምታለች። ይሁን እንጂ ሐሙስ እለት ጥር 07/2017 ዓ.ም እስራኤል ሃማስን ከስምምነቱ ወደኋላ በማፈግፈግ ወነጀለች፣ ስምምነቱ እንዲዘገይ ታቅዶ የነበረው የካቢኔ ድምፅ ዘግይቷል።
ቀጣይነት ያለው ሰብአዊ ቀውስ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አቶ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ስምምነቱን በደስታ ቢቀበሉትም በጋዛ የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ ተደራሽነትን ማረጋገጥ እንዳለበት አሳስበዋል።
ዩኒሴፍ ስምምነቱን ወቅታዊ ብሎ በመጥቀስ በጋዛ ህጻናት ላይ ያለውን ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ አጉልቶ አሳይቷል።
በተመሳሳይ የተባበሩት መንግስታት UNRWA ኃላፊ ፊሊፕ ላዛሪኒ በጋዛ የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ ለማግኘት "ፈጣን እና ያልተደናቀፈ" ጥሪ አቅርበዋል ።
አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ ያለውን ፍላጎት አፅንዖት ሰጥቶ ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የተኩስ አቁም ስምምነት ከታወጀ በኋላ በጋዛ ቢያንስ 32 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል ሲሉ የነፍስ አድን ሰራተኞች ገልጸዋል።
የጋዛ ሲቪል መከላከያ ብዙ ቤቶች ያሉት አንድ አፓርትመንት በቦምብ ተመቷል ሲል ገልጿል።