የ “Pax Dei” ሽልማት የ “Pax Dei” ሽልማት 

ቅድስት መንበር ሰላምን በመደገፍ ላሳየችው ቁርጠኝነት የ “Pax Dei” ሽልማት እንደምትቀበል ተገለጸ

በ በጣሊያ “ሳንታ ቴክላ ዲ አቺሪያሌ” ነሐሴ 15/2018 ዓ. ም. በሚዘጋጀው 48ኛ ዙር የ “Pax Dei” ሽልማት ዝግጅት ላይ ቅድስት መንበር ሰላምን በመደገፍ ላሳየችው ቁርጠኝነት ለብሔራዊ የጋሪታ ሽልማት መመረጧ ታውቋል። በዕለቱ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን የቪዲዮ መልዕክት የሚያስተላልፉ መሆኑን የሽልማት አዘጋጅ ኮሚቴ በመግለጫው አታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ በጣሊያን ካታኒያ ግዛት ሳንታ ቴክላ ውስጥ የተጀመረው ብሔራዊ የጋሪታ ሽልማት ለ48ኛ ጊዜ መዘጋጀቱ ታውቋል። ዘንድሮ የተመረጠው ርዕሥ “መልካም እና ክፉ” የሚል ሲሆን ይህም በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ዘልቀው የገቡ ሁለት ገጽታዎችን የሚያነጻጽር እንደሆነ ታውቋል።

ከዘንድሮ ሽልማቶች መካከል “Pax Dei” የተሰኘው ለቅድስት መንበር የተዘጋጀ ሲሆን ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን ዝግጅቱን በቪዲዮ ምስል በመካፈል መልዕክት እንደሚስተላልፋሉ ይጠበቃል።

በማንኛውም ወጪ ለበጎ ነገር መጣር

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለቅድስት መንበር የሰላም ቁርጠኝነት እውቅናን ለመስጠት የፈለገው በፈተና ውስጥ በሚገኝበት ወቅት መሆኑን የሽልማት አዘጋጅ ኮሚቴ ዳይሬክተር አቶ አንቶኔሎ ሙስሜቺ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

አቶ አንቶኔሎ በመግለጫቸው “ለሰው ልጅ ብዙ ነገር አስቸጋሪ በሆነበት በዚህ ወቅት በምትችለው ሁሉ መልካምነትን በማራመድ ላይ ለምትገኘው ቅድስት መንበር ሽልማቱን መስጠት ትክክል ሆኖ አግኝተነዋል” ብለዋል። “የቅድስት መንበር ቁርጠኝነት በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እና በብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን አስተዋይ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በኩልም የታየ ተጨባጭ የሰላም ቁርጠኝነት ነው” ሲሉ አክለዋል።

የ 2017 ዓ. ም. ዝግጅት
የ 2017 ዓ. ም. ዝግጅት

ባለፉት ዓመታት ውስጥ የተሰጡት የጋሪታ ሽልማቶች በዋና ዋና ጭብጦች ላይ በመመርኮዝ ሲሆን፥ ሽልማቱ ዳኛ ኒኮላ ግራቴሪን፣ የሥነ-ምግባር፣ የባዮኤቲክስ ፕሮፌሰር እና የ (AI) ባለሙያ አባ ፓውሎ ቤናንቲን እና የቅድስት መንበር መገናኛዎች ጽሕፈት ቤት የቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ፍራንቼስኮ ማሺን ያካትታል። ባለፈው ዓመት “እኔ የምፈልገው ዓለም” በሚል ጭብጥ በጦርነት የተጎዱ የጋዛ ነዋሪዎችን በማስመልከት የተዘጋጀውን ሽልማት የኢየሩሳሌም የላቲን ፓትርያርክ ብጹዕ ካርዲናል ፒርባቲስታ ፒሳባላ መቀበላቸው ይታወሳል።

የመልካም እና የክፉ ልዩነት

“መልካም እና ክፉ” በሚለው የዘንድሮ ጭብጥ ላይ የሽልማት አዘጋጅ ኮሚቴ ዳይሬክተር አቶ አንቶኔሎ፥ ከጅምሩ ከሰው ልጅ ጋር አብሮት የነበረውን “ፍጹም ልዩነት” በማስመልከት ባደረጉት ንግግር፥ “የሰው ልጅ በሚደርስበት ተቃርኖ እና ጭቆና ስብዕናውን ለይቷል፤ ዛሬ ከመልካም መርህ ወደ ክፋት ተመልሰናል፤ ይህም በዘመናዊ የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ ጨለማ ጊዜያት መካከለ አንዱ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ብሔራዊ የጋሪታ ሽልማት
ብሔራዊ የጋሪታ ሽልማት

የማጣቀሻ ነጥብ

አቶ አንቶኔሎ በጣሊያን ሲሲሊ ውስጥ ተመሥርቶ ነገር ግን ባለፉት ዓመታት ውስጥ አገር አቀፍ ጠቀሜታ ያለው የባህል ክስተት እየሆነ ስለመጣው ሽልማት ሲናገሩ፥ “በበረሃ ውስጥ ያለ ካቴድራል” ሲሉ ጠርተውት፥ ከግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ በፊት የተወለደ እና በከፍተኛ ስሜት የማጣቀሻ ነጥብ ለመሆን የበቃ መሆኑን አስረድተዋል።

የ 48ኛ ዙር የጋሪታ ሽልማት ማስታወቂያ
የ 48ኛ ዙር የጋሪታ ሽልማት ማስታወቂያ

የሥነ ጥበብ፣ የመዝናኛ እና የባህል ምሽት

የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ዓርብ ነሐሴ 15/2018 ዓ. ም. በሳንታ ቴክላ አቺሬያሌ በሚገኘው በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አደባባይ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ታውቋል። ይህ 48ኛው የሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት በ “ራይ” የጣሊያን ቴሌቪዥን ዳይሬክተር ፒኖ ሊዮኒ የሚመራ ሲሆን፥ ፕሮግራሙን የሚያስተናግዱት አንቶኔሎ ሙስሜቺ እና የ “TG2” ጋዜጠኛ እና ጸሐፊ አድሪያና ፓኒቴሪ እንደሆኑ ታውቋል። ይህ የኪነጥበብ፣ የመዝናኛ እና የባህል ምሽት በመላ የአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ የሚተላለፍ ሲሆን፥ እንደተለመደው  በከፍተኛ ወቅታዊ ጭብጦች ላይ እንደሚያተኩር ታውቋል።

ብሔራዊ የጋሪታ ሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት

 

20 Aug 2026, 14:19