የቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት ወንድማማቾች ማሕበር የቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት ወንድማማቾች ማሕበር   (AFP or licensors) ርዕሰ አንቀጽ

የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት ወንድማማቾች ማሕበር በድጋሚ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንዲለይ ተደረገ

የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት ወንድማማቾች ማሕበር በድጋሚ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንዲለይ ተደረገ

የቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት ወንድማማቾች ማሕበር ከርዕሰ  ሊቃነ ጳጳሳት ፈቃድ እና እውቅና ውጪ ለአራት ጳጳሳት ሲመተ ጵጵስና በመስጠታቸው የተነሳ እንደገና ከሰላሳ ስምንት አመታት በኋላ ከሮም ቤተክርስቲያን በደረሰበት ውግዘት የተነሳ ከቤተክርስቲያን መለየቱ የተገለጸ ሲሆን ይህ ውግዘት የደረሰበት ማሕበሩ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም በፈጸሙ ሕገ-ወጥ የጳጳሳት ሹመት ምክንያት መሆኑ  ተገልጿል፣ ከዚህ ቀደም ከ38 አመታት በፊት በዚህ ተመሳሳይ ማሕበር ላይ እ.አ.አ 1988 ዓ.ም ለስምንት ጳጳሳት በተመሳሳይ መልኩ ሲመተ ጵጵስና ማሕበሩ በመስጠቱ የተነሳ ከደረሰባቸው ውግዘት በኋላ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ያገለገሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጵውሎስ 6ኛ እና በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ  መልካም ፈቃድ እና ልግስና መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት እና ውይይት ውግዘቱ ተነስቶ፣ በቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አማካይነት ወደ ሙሉ ሕጋዊ ክብሩ ማሕበሩ እንዲመለስ ተደርጎ ነበር፣ አሁን ደግሞ ይህ ተመሳሳይ ማሕበር በሕገወጥ መልኩ ሲመተ ጵጵስና በመፈጸሙ የተነሳ በድጋሚ ውግዘት እንደ ደረሰበት ተገልጿ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

 ለጋስ እና ደግ በሆኑ ሙከራዎች፣ በሮች ክፍት ሆነው እና በተሰጡ እድሎች የተመሰከረለት አስቸጋሪ ታሪክ ነው። በሊቀ ጳጳሳት ማርሴል ሌፌብሬ የተመሰረተው የቅዱስ ፒየስ 10 ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር ራሱን ከሊቀ ጳጳሱ እና ከሮም ቤተክርስቲያን ጋር ካለው ኅብረት እንዲለይ ያደረገ ሁለት ከባድ ጥፋቶች ያሉት አሳዛኝ ታሪክ ሲሆን ይህም ያለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣን እና ቤተክርስቲያን ፈቃድ በራሳቸው ፈቃድ ሲመተ ጵጵስና የመስጠት ተግባር በመፈጸም እራሳቸውን ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ከሮም ቤተክርስቲያን ጋር ካላቸው ኅብረት እንዲለዩ አድርጓል።

በሰኔ 24/2018 ዓ.ም የተፈጸመው ስብራት ለቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት ወንድማማቾች ማሕበር ጳጳሳት እና ካህናት ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ምእመናን ከባድ መዘዝ አለው። በእምነት ዶክትሪን ማብራሪያ ማስታወሻ ላይ እንደተገለጸው፣ የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር "በሕገ-ወጥ መንገድ ምስጢራትን ይሰጣሉ፣ የሚያስተዳድሯቸው ምስጢረ ንስሐ እና የሚፈጽሟቸው ምስጢረ ተክሊል ዋጋ የላቸውም ወይም ሕገ ወጥናቸው" ሲል በቫቲካን የቀኖናዊ እና ሐይማኖታዊ ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ይፋ ካደርገው ሰነድ ለመረዳት ተችሏል።

የቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት ወንድማማቾች ማሕበር ውሳኔዎች

ኦፊሴላዊው የማሕበሩ ስም የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት ወንድማማቾች ማሕበር በመባለ የሚታወቅ ሲሆን የዚህ ማሕበር መስራች ሊቀ ጳጳሳት ማርሴል ሌፌብሬ በመሆናቸው የተነሳ የሌፌብሬ ማሕበር በመባልም ይታወቃል። በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወቅት፣ የተደርጉትን የተወሰኑ ማሻሻያዎችን በወቅቱ የተቃወሙት የፈረንሳዩ ሊቀ ጳጳስ ማርሴል ሌፌብሬ እንደ ነበሩ የሚታወቅ ሲሆን ሆኖም ግን፣ በወቅቱ እ.አ.አ 1963 ዓ.ም ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ከደነገጋቸው 16 ኦፊሴላዊ ሰነዶች እና 4 ሐዋርያዊ ሕገ ደንቦች ይፋ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህ ሐዋርያዊ ሕገ ደንቦች መካከል በላቲን ቋንቋ "Sacrosanctum Concilium" የተሰኘው መንፈሳዊ አምልኮን የተመለከተ ሐዋርያዊ ሕገ ደንብ መታወጁ ይታወሳል።

የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በመንፈሳዊ አምልኮ (Sacrosanctum Concilium) እንዲሁም በሐይማኖታዊ ነጻናት ዙሪያ የሚያጠነጥነው ((Dignitatis humanae) የተሰኙ ሁለት ሐይማኖታዊ ሕገ ደንቦች  መድንገጋቸው ይታወሳል። የቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት ወንድማማቾች ማሕበር የመጀመሪያውን አሁንም የሙከራ ሥነ ሥርዓት ማሻሻያዎችን የያዘውን እ.አ.አ የ1965ቱን የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ሥርዓት እንዳከበሩ መታወስ አለበት።

ሊቀ ጳጳሳት ማርሴል ሌፌብቭሬ እ.አ.አ በ1970 ዓ.ም የቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር ከመሠረቱ በኋላ፣ በፍሪቡርግ የስውዘርላንድ ሀገረ ስብከት ውስጥ በኤኮኔ የራሳቸው ዘርዓ ክህነት ወይም ሴሚናሪ እና በሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ፍራንሷ ቻሪየር ፈቃድ ቢከፍቱም፣ በአዲሱ ተሻሽሎ በቀርበው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የመስዋዕተ ቅዳሴ አምልኮ መጽሐፍ መሠረት መስዋዕተ ቅዳሴ ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆኑም፣ እናም እ.አ.አ በ1974 በወቅቱ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያስተዋወቃቸውን ማሻሻያዎች "ቤተ ክርስቲያንን የሚያጠፉ አዳዲስ ነገሮች" ሲሉ ገልጸዋቸው ነበር።

"እንቃወማለን! እናም ሁልጊዜም የሮማውያንን "Neomodernism"  እና "ድህረ-ፕሮቴስታንቲዝም" ዝንባሌ ተከትሎ የሚመጡ ማሻሻያዎችን እንቃወማለን፣ ይህም በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እና ከጉባኤው በኋላ በግልጽ የታየው፣ ከጉባኤው የወጡትን ሁሉንም ማሻሻያዎች እንቃወማለን። እነዚህ ሁሉ ማሻሻያዎች በእርግጥ ለቤተክርስቲያኗ መፍረስ አስተዋጾ አድርገዋል፣ እናም አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል" ሲል ማሕበሩ እ.አ.አ በሕዳር 21 ቀን 1974 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ጽሑፍ ማወጁ ይታወሳል።

ሀገረ ስብከቱ የቅዱስ ጲዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር እውቅና ሰጥተዋል፣ ነገር ግን ቅድስት መንበር ከሊቀ ጳጳሱ ጋር ለመነጋገር በወቅቱ ፈልጋ ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ስጋታቸውን ለመስማት ኮሚሽን አቋቁመው እ.አ.አ በ1975 ዓ.ም ሌፌብቭሬ የኢኮኔ ሴሚናሪን እንዲዘጋ እና ተጨማሪ የክህነት ሹመቶችን እንዳይሰጡ ጠየቁ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ለሊቀ ጳጳሱ ሦስት ጊዜ ጽፈው የማሕበሩን ዋና መሥሪያ ቤት እንዲጎበኙ የሚያምኗቸውን ጳጳሳት ልከዋል።

ከዚያም እንደገና እምቢ ካሉ በኋላ ማርሴል ሌፌብቭሬ በይፋ ታገዱ። ከእዚያን በኋላ መስዋዕተ ቅዳሴ እንዳያሳርጉ ታግደው ነበር። ያም ሆኖ በዚያው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ በአስር ሺህ ምዕመናን እና በአራት መቶ ጋዜጠኞች ፊት እንዳያደርጉ የታገዱትን መስዋዕተ ቅዳሴ መርተው ከፍተኛ የሚዲያ ትኩረትን ስበው ነበር።

እ.አ.አ በመስከረም 1976 ዓ.ም ሊቀ ጳጳስ ሌፌብቭሬ በካስቴል ጋንዶልፎ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ጋር ስብሰባ አድርገው ነበር። ስብሰባው ምንም ውጤት አላስገኘም። እ.አ.አ በመስከረም 1976 ዓ.ም ከፈረንሳዊው ፈላስፋ ዣን ጊተን ጋር ቅዱስነታቸው በአንድ ወቅት ሲነጋገሩ፣ እሱም "መከፋፈልን ለማስወገድ የሚቻለውን ሁሉ እና የማይቻል የሚመስለውን ሁሉ" እንዲያደርጉ ቅዱስነታቸውን ጥይቋቸው ነበር። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ እንዲህ ሲሉ መልስ ሰጥተው ነበር  "እኔም ልክ እንደ አንተ ይሰማኛል። በእርግጥም ስሜቴ ከአንተ እጅግ የላቀ ነው፣ ባለፉት አስራ ሶስት ዓመታት ውስጥ የጵጵስና ሥልጣኔ የመጀመሪያው እውነተኛ መስቀል ነው። ነገር ግን መፍትሄ ለማምጣት  የሚቻለውን ሁሉ እንዳደረግሁ ልነግርህ እችላለሁ" ሲሉ ቅዱስነታቸው መልስ ሰጥተው ነበር።

አክሎም ቅዱስነታቸው "እንዲያውም በጥቂት ወራት ውስጥ አንድ ሰው ይህንን ያለመተባበር፣ ወደ መለያየት እንዴት እንደማይለውጥ ማሰብ አያቅተውም" ብለው ነበር። " እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ አልተከሰተም። ወራት ሳይሆን የጴጥሮስ መንበር ተተኪ ሁልጊዜ ቢኖርም በርካታ ዓመታት ግን ያልፋሉ" ሲሉ አክለው ገለጸዋል።

በሊቀ ጳጳስ ሌፌብቭሬ የተፈረመው የዶክትሪን ስምምነት

ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ 264ኛው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ፣ ሊቀ ጳጳስ ሌፌብቭሬ የቅድስት መንበርን በተለየ መንገድ የሚመለከቱ ይመስላል። እ.አ.አ ህዳር 18 ቀን 1978 ዓ.ም ሊቀ ጳጳስ ሌፌብቭሬ ከቅዱስነታቸው ጋር ተገናኝተው ነበር። እናም እ.አ.አ መጋቢት 8 ቀን 1980 ዓ.ም ለሊቀ ጳጳሱ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ “ስለ ምርጫዎ ትክክለኛነት እና ታማኒነት ምንም እንደማያመንቱ” ገልጸው እና “ከቅድመ-የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ይደረግ የነበረው መስዋዕተ ቅዳሴ በራሱ “ውድቅ ወይም ውግዝ እንደሆነ በጭራሽ አላሳወቁም” ሲሉ ጽፈው ነበር።

ቢያንስ በከፊል አለመግባባቶችን ለመፈወስ እና እገዳውን ለማንሳት ስምምነት ከተደረገ በኋላ፣ እ.አ.አ ሚያዝያ 1988 ዓ.ም ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ  ጋር ከተገናኙ ከአስር ዓመታት በኋላ መታየት ጀመሩ።

በወቅቱ በቫቲካን የቤተክርስቲያን ቀኖና እና የእምነት ዶክትሪን ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ የነበሩት  ካርዲናል ጆሴፍ ራዚንገር፣ ከጽ/ቤቱ ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ አልቤርቶ ቦቮን ጋር፣ ከሊቀ ጳጳስ ሌፌብቭር እና ከብዙ ተባባሪዎቻቸው ጋር ለሦስት ቀናት አስቸጋሪ ድርድር አካሂደው ነበር። በጣም ጉልህ የሆነው ማበረታቻ የመጣው በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ጋር በሚገናኙበት ቀን ዋዜማ ላይ ነበር።

በትዕግስት እና በማስተዋል፣ ካርዲናል ራዚንገር ከባህላዊው ጳጳስ ጋር የጋራ የዶክትሪን ፕሮቶኮል ለመፈረም ተሳክቶላቸው ነበር። ሰነዱ የተጠናቀቀው እ.አ.አ ግንቦት 4 ቀን 1988 በሮም በተካሄደው ስብሰባ ላይ ሲሆን በማግስቱ በካርዲናል ራዚንገር እና በሊቀ ጳጳስ ሌፌብቭር ተፈርሞ ይፋ ሆኖ ነበር።

በዚያ ጽሑፍ፣ ሊቀ ጳጳሱ እና የቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር አባላት "ሁልጊዜም ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ለሮማ ጳጳስ ታማኝ ለመሆን" ቃል ገብተው የነበረ ሲሆን "በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ  በላቲን ቋንቋ "Lumen gentium" (የአሕዛብ ብርሃን) የዶግማዊ ሐዋርያዊ ሕገ ቀኖና ቁጥር 25 ላይ የተካተተውን አስተምህሮ እንደሚቀበሉ አስታውቀዋል፤ ጉባኤው ያስተማራቸውን አንዳንድ ነጥቦች ወይም ከዚያ በኋላ ስለተደረጉት የአምልኮ ሥርዓቶችና የቀኖና ሕግ ማሻሻያዎችን በተመለከተ "ከቅድስት መንበር ጋር አዎንታዊ የመግባቢያ አመለካከትን ለመቀበል ወስነዋል፣ ይህም ለባህላዊ አማኞች "ከቱፊት ጋር ለመታረቅ አስቸጋሪ" የሚመስለውን ነገር ማለት ነው።

በተጨማሪም ፕሮቶኮሉ ወይም ስምምነቱ እንደሚለው በቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ እና በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በተደነገገው ሥርዓት መሠረት "የመስዋዕተ ቅዳሴ እና የቤተክርስቲያኗ ምስጢራት ትክክለኛነት እንገነዘባለን" ይላል።

ስምምነቱ ሌሎች ጉዳዮችንም ይመለከታል፡- የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ የካህናት የወንድማማችነት የሐዋርያዊ ሕይወት ማኅበር መሆን ነበረበት፣ በዚህም ሙሉ ነፃነትን ያገኛል፣ እና "በተግባራዊ እና በስነ-ልቦና ምክንያቶች፣ የካህናት የወንድማማችነት አባል የሆነ ጳጳስ ሲመተ ጵጵስና መስጠት ጠቃሚ እንደሆነ" ይቆጠራል። ሁሉም ነገር መፍትሄ ያገኘ ይመስላል።

የመጀመሪያው የመከፋፈል ድርጊት

ነገር ግን በድንገት፣ እ.አ.አ ግንቦት 6 ቀን 1988 ዓ.ም ጠዋት፣ የፈረንሳዩ ጳጳስ የድርድር ጠረጴዛውን ገለበጡት። ሀሳባቸውን ቀይረው ለካርዲናል ራዚንገር እ.አ.አ በሰኔ 30/1988 ዓ.ም ለአዲስ ጳጳሳት ሲመተ ጵጵስና ለመስጠት  እንዳሰቡ በግል አሳውቀዋል።

የሊቀ ጳጳስ ሌፌብቭሬ ውሳኔ የመነጨው ቅድስት መንበር በቅዱስ ፒዮ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር ቀሳውስት መካከል ተስማሚ የጳጳሳት እጩዎችን እንዳላገኘ በማመናቸው እና አዲሱ ጳጳስ ከየወንድማማችነት ማሕበር ውጭ እንደሚመጣ በመፍራት ነው።

እ.አ.አ በግንቦት 24/1988 የተደረገው ተጨማሪ ስብሰባ ያለ ውጤቱ አብቅቷል፣ እና ሰኔ 2/1988 ሊቀ ጳጳስ ሌፌብቭሬ ለርዕሰ ሊቃነ ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ስለ ድራማዊ ውሳኔያቸው ሲጽፍላቸው፡ እርሳቸው እና ተከታዮቻቸው "ሮም ወደ ባሕሏ የምትመለስበት የበለጠ ምቹ ጊዜ እጠብቃለሁ፣ በዘመናዊነት የተበከለችው የዛሬዋ ሮም እንደገና የካቶሊክ ሮም እንድትሆን ጸልያለሁ" በማለት ጽፈላቸው ነበር። እ.አ.አ ሰኔ 29/1988 ሲመተ ጵጵስናው ያለ ቅድስት መንበር ፈቃድ ከታወጀው ከ24 ሰዓት ቀደም ብሎ፣ ካርዲናል ራዚንገር ለሊቀ ጳጳሱ የቴሌግራም መልእክት ልከው ነበር፡- “ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያኑ ፍቅር፣ ቅዱስ አባታችን፣ አባታዊ ሆኖም ጽኑ በሆነ መንገድ፣ በሰኔ 30 ልትፈጽሙት ያሰባችሁት ሲመተ ጵጵስና ከማከናወናችሁ በፊት ወደ ሮም እንድትመጡ ይጠይቋችኋል” የሚል መልእክት በወቅቱ ልከው እንደ ነበረ ይታወሳል።

ነገር ግን ሊቀ ጳጳስ ሌፌብቭሬ ውሳኔውን ተግባራዊ አድርገዋል። በማግስቱ የካምፖስ ሀገረ ስብከት አዛውንት ብራዚላዊ ቄስ አንቶኒዮ ደ ካስትሮ ማየርን በመታገዝ የቅዱስ ፒዮ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር አባላት የሆኑ አራት ጳጳሳት አድርጎ ሾሙ፤ እነሱም በርናርድ ፌሌይ፣ አልፎንሶ ደ ጋላሬታ፣ ሪቻርድ ዊሊያምሰን እና በርናርድ ቲሲየር ደ ማሌሬይስ ናቸው።

በሐምሌ 1 ቀን ሲመተ ጵጵስና የሰጡት እና ሲመተ ጵጵስናውን የተቀበሉ ሰዎች የመለያየት ድርጊት በመፈጸማቸው ምክንያት በላቲን ቋንቋ " latae sententiae" የተሰኘው ወደ ውግዘት የምያደርስ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተደርጓል።

እ.አ.አ በ1988 ካርዲናል ራዚንገር በሲውዘርላንድ ኤኮኔ ከሚገኙ ባህላዊ እምነት ተከታዮች ጋር የዶክትሪን ስምምነት ፈርመው ነበር፣ ነገር ግን ሁሉም ነገር በመሠረቱ ተግባራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሻር፣ በቀጣዮቹ ዓመታት በተደረጉት ድርድሮች፣ ቅድስት መንበር ከፍተኛውን ውሳኔ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑኗን አሳይቷል፣ ለቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የየወንድማማችነት ማሕበር ደግሞ “የዶክትሪን ግልጽነት” የጎደለው መሆኑን በመግለጽ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ ክፍሎች እና የድህረ-ስምምነት የአስተምህሮ ክፍሎችን እንዲተው ይጠይቃሉ።

የ2000 ዓ.ም መንፈሳዊ ንግደት እና የካርዲናል ቤኔዲክቶስ ስምምነት

ከቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር ጋር የተደረገው እርቅ የማድረግ ሙከራ እ.አ.አ በነሐሴ 2000 እንደገና ቀጠለ። ከቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር አባላት ወደ ሮም የ2000 ዓ.ም ኢዩቤሊዮ መንፈሳዊ ንግደት አድርገው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሥርዓት ተከናውነዋል። ጳጳስ ፌሌይ፣ ከካርዲናል ዳሪዮ ካስትሪሎን ሆዮስ፣ የኤክለሲያ ዴይ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ጋር በመሆን፣ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጋር ለብዙ ደቂቃዎች የቆየ ውይይት አድርገዋል።

ካርዲናል ራዚንገር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ግንኙነቶቹ ቀጠሉ እናም ተጠናክረው መጓዝ የጀመሩ ሲሆን፣ እነሱም በሁለት ዓመታት ልዩነት በተደረጉ ሁለት ውሳኔዎች ለባህላዊ እምነት ተከታዮች ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

እ.አ.አ ሐምሌ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ  የ1962ቱን የሮማ የመስዋዕተ ቅዳሴ ማድረጊያ መጽሐፍ የቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር እንዲጠቀሙ ፈቃድ ሰጥተው የነበረ ሲሆን ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በፊት የነበረውን የላቲን ቤተክርስቲያን የአምልኮ ሥርዓት እንዲቀጥሉ ፈቅደው ነበር።

እ.አ.አ ጥር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ በ1988 ዓ.ም. በሌፌብሬ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ሲመተ ጵጵስና የተሰጣቸውን አራቱን ጳጳሳት ከሥልጣን እንዲባረሩ አደረጉ።

የውግዘት አዋጅን በተናጠል ማንሳት የአንድ ወገን የእርቅ ተግባር ሲሆን፣ አነስተኛ የሆኑ የመከፋፈል አዳጋን ያስቀራል፣ ከቅዱስ ፒየስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር ጋር ለመነጋገር በር ይከፍታል።

ከቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር ጳጳሳት "ከቤተክርስቲያኗ ጋር ሙሉ ህብረት ለማግኘት የሚያስፈልጉትን ተጨማሪ እርምጃዎች ለመውሰድ" ፈጣን ቁርጠኝነት እንደሚኖር ተስፋ አድርገው ነበር። በዚህም እውነተኛ ታማኝነት፣ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ እና የሊቀ ጳጳሱን እና የሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ ስልጣን እውነተኛ እውቅና አሳይተዋል።

የ2011ቱ የዶክትሪን መግቢያ እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ውሳኔ

ዓመታት አለፉ፣ እና እ.አ.አ በመስከረም 2011 ዓ.ም. የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር ጥያቄ በቀረበው ተከታታይ የዶክትሪን ውይይቶች መደምደሚያ ላይ፣ ቅድስት መንበር ማሕበሩ እንዲፈርምበት የሚጠይቅ አጭር ሰነድ አቀረበች።

ጽሑፉ በመሠረቱ ሦስት ነጥቦችን የያዘ ሲሆን፣ የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ከያዘ ማንኛውም ሰው የሚፈለገውን “የእምነት መግለጫ” እንዲቀበል ከሚጠይቀው ጥያቄ ጋር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እና የጳጳሳት ሕብረት ወይም የጳጳሳት ኮሌጅ “እውነተኛውን የዶክትሪን ሥራቸውን ሲያከናውኑ የሚያቀርቡትን” ትምህርቶች “የሃይማኖት ፈቃድ እና የማሰብ ችሎታ” እንዲያረጋግጡ ይጠይቃል፣ እነዚህ ትምህርቶች እንደ አብዛኞቹ የዶክትሪን ሰነዶች ባሉበት ጊዜም እንኳ እነዚህ ትምህርቶች በዶግማዊ መንገድ ባይታወጁም ይህንን አምኖ መቀበል እንደሚገባ ይዘረዝራል።

የቫቲካን ባለሥልጣናት በመግቢያው ላይ መፈረም ማለት “በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሰነዶች ውስጥ የተካተቱትን የግለሰብ አገላለጾች ወይም ቀመሮች ትክክለኛ ውይይት፣ ጥናት እና ሥነ-መለኮታዊ ማብራሪያ” ማቆም ማለት እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

ይህ ሙከራም ከንቱ ሆነ። የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር የቀረበው የዶክትሪን ጽሑፍ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቋል።

በቀጣዮቹ ዓመታት የዶክትሪን መግቢያዎች ወደ ጎን እንዲደረጉ ተደርጋውል፣ እናም እንደ ሐዋርያዊ አስተዳደር ወይም የግል ቅድመ ዝግጅት ያሉ ቀኖናዊ መፍትሄዎች ጥናት ተደርጎባቸዋል። ነገር ግን በወቅቱ የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር የበላይ አለቃ የነበሩት ጳጳስ ፌሌይ “የካህናት የወንድማማችነት በመጀመሪያ ደረጃ ቀኖናዊ እውቅና እየፈለገ አይደለም” ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጣልቃ ገብነቶቹ ተለውጠዋል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅዱስ ጴጥሮስን ወንበር ተቆጣጠሩ።

እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም የልዩ የምህረት አመት ኢዮቤልዩ በዓል ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር አባላት ምስጢረ ንስሐ የማስገባት እና ምእመናንን በዚህ ምስጢር የማንጻት ልዩ ፈቃድ ሰጥተዋል። ምእመናንን አንድ ለማድረግ የታሰበ እርምጃ ነበር፣ ይህ ትምህርት በኋላ ላይ ከልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት ኢዩቤሊዩ በዓል በኋላ በተረጋጋ መሠረት በላቲን ቋንቋ "Misericordia et misera" (ምሕረት እና ሰቆቃ) በተሰኘው ሐዋርያዊ መልክታቸው ውስጥ ተጠቅሷል።  

ምንም እንኳን የጳጳሶቻቸው መባረር እ.አ.አ በ2009 ውሳኔው እንደ ገና ቢቀለበስም፣ የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መደበኛ የዳኝነት መዋቅር ውስጥ ሳይካተቱ መስራታቸውን ቀጥለዋል። በዚህ ተግባር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር የሚከተሉ ምእመናንን ጥቅም ከማሰብ በላይ የውይይት እና የእረኝነት እርቅ ምልክት ለማድረግ ፈልገው ያደረጉት ተግባር ነበር።

አዲሱ ክፍፍል፣ የምስጢረ ንስሐ እና የምስጢረ ተክሊል ሥነ-ሥርዓቶችን እንዳያከናውኑ ይከለክላል

እ.ኤ.አ. የካቲት 2/2026፣ የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር ለአራት አዲስ ጳጳሳት ሲመተ ጵጵስና እንደ ሚሰጥ እ.አ.አ በሐምሌ 1/2026 አስታውቆ ነበር።

እ.ኤ.አ. የካቲት 12/2026 ዓ.ም የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር የበላይ አለቃ አባ ዴቪድ ፓግሊያራኒ እና በቫቲካን የሐይማኖት ቀኖናዎችን እና የእመነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቀድስት መንበር ጽ/ቤት ዋና ጸሐፊ ከሆኑት  ከካርዲናል ቪክቶር ማኑኤል ፈርናንዴዝ ጋር በቫቲካን ተገናኝተው ነበር።

ካርዲና ቪክቶር ለቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር የበላይ አለቃ አባ ዴቪድ ፓግሊያራኒ "እስካሁን በቂ ማብራሪያ ያላገኙ ጉዳዮችን በተመለከተ በግልጽ የተቀመጠ ዘዴ ያለው ልዩ ነገረ መለኮታዊ (የቲዎሎጂካል) መንገድ" አቅርበው "ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር ሙሉ ህብረት ለማድረግ የሚያስፈልጉትን ዝቅተኛ መስፈርቶች" ከቀኖናዊ መፍትሄ ጋር ለመለየት ሀሳብ አቅርበዋል፡ "ይህንን ውይይት የማካሄድ እድሉ ማሕበሩ በታወጀው የኤጲስቆጶስ ሹመቶች ላይ ያደረገውን ውሳኔ እንዲያቆም ያስገድዳል"።

የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር የበላይ አለቃ አባ ዴቪድ ፓግሊያራኒ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ ታዛዥ እንደሆኑ ቢናገሩም፣ አዲሶቹን የኤጲስቆጶስ ሹመቶች እንዳይቀጥሉ ተደጋጋሚ ጥሪ እና ማስጠንቀቂያዎች ቢኖሩም፣ ለጴጥሮስ ተተኪ በቃላት እንደሚታዘዙ ቢናገሩም፣ በተግባር ግን ምንም መንገድ አልከፈቱም እና የጴጥሮስ ተተኪ ጥያቄዎችን አላጤኑም፣ ይልቁንም እቅዳቸውን በመከተል አዲስ ክፍፍል እንዲፈጠር አድርገዋል።

እ.አ.አ ሰኔ 16/2026 በካስቴል ጋንዶልፎ ለአንድ ጋዜጠኛ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እንዲህ ብለዋል፣ "በእርግጥ፣ በክርስቲያኖች መካከል መከፋፈል ሁልጊዜ የሚያም ነገር ነው፣ ነገር ግን የቤተክርስቲያኒቱን አንዳንድ መሠረታዊ ነገሮች ለመቀበል እምቢ ይላሉ፣ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የሰፈሩትን በርካታ ነጥቦች ጨምሮ። እነሱ የሚያደርጉት ምርጫ ይህ ከሆነ፣ ይቅርታ እጠይቃለሁ፣ ግን ወደፊት መሄድ አለብን" ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ካህናት የወንድማማችነት ማሕበር በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ 720 ካህናት፣ 700 የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ማሕበር እንደ ሆነም ይታወቃል።

03 Jul 2026, 16:11