የሃይማኖት ሥራዎች ተቋም (IOR) እ.አ.አ የ2025 የፋይናንስ ሪፖርት ይፋ አደረገ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በተለምዶ የቫቲካን ባንክ ወይም ኦፊሴላዊ በሆነው መጠሪያው የሃይማኖት ሥራዎች ተቋም (IOR) እ.አ.አ የ2025 ዓ.ም የፋይናንስ ሪፖርቱን ማክሰኞች ዕለት ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም በተቋሙ በወጣው የጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት፣ ሪፖርቱ የIOR ዘላቂ ፋይናንስን እና የሰውን ልጅ የሚያገለግል፣ የሰውን ክብር የሚያስከብር እና የጋራ ጥቅምን የሚያራምድ ኢኮኖሚንበማበረታታት ረገድ ያለውን አስተዋጽኦ ይዘረዝራል። በተጨማሪም በዓመቱ ውስጥ የአካባቢ፣ የማህበራዊ እና የአስተዳደር (ESG) ጉዳዮችን ወደ ተቋሙ ተግባራት በማዋሃድ የተገኘውን እድገት ያጎላል።
በቫቲካን ከተማ ግዛት ውስጥ ሙያዊ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን እንዲያከናውን የተፈቀደለት ብቸኛው ተቋም እንደመሆኑ መጠን፣ IOR ከ12,000 በላይ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቋማት አባላት የሆኑ ወይም በ110 አገሮች ውስጥ በአገልግሎቱ ውስጥ የሚሰሩ ደንበኞችን ያገለግላል።
ተቋሙ በጊዜ ሂደት በተዘጋጀ የአሠራር ሞዴል አማካኝነት፣ በጥንቃቄ የተመረጡ የኢንቨስትመንት ምርጫዎችን ከደንበኞች የኢንቨስትመንት ዓላማዎች እና የአደጋ መገለጫዎች ጋር በማጣመር ንቁ የኢንቨስትመንት አቀራረብን በመጠቀም በፋይናንስ ገበያዎች ላይ ኢንቨስት ያደርጋል።
'ድርብ አቋማዊ ወይም አካላዊ' ግምገማ ('Double materiality' assessment)
ድርብ አቋማዊ ወይም አካላዊ ግምገማ (DMA) የዘላቂነት ጉዳዮችን በሁለት ሌንሶች ወይም እይታዎች ይገመግማል፡- የአካላዊ ወይም ተቋማዊ ተፅዕኖ ይህ ማለት (አንድ ኩባንያ ኅብረተሰቡን እና አካባቢውን እንዴት እንደሚነካ) እና የፋይናንስ አቁማዊ ወይም አካላዊ ግምገማ (አካባቢያዊ እና ማህበራዊ ሁኔታዎች የአንድን ኩባንያ የፋይናንስ ጤና እንዴት እንደሚነኩ) የሚያሳዩ መለኪያዎች ሲሆኑ ይህ ድርብ አቀራረብ እንደ አውሮፓ የዘላቂነት ሪፖርት ደረጃዎች (ESRS) ባሉ ማዕቀፎች ያስፈልጋል የኮርፖሬት ዘላቂነት ሪፖርት መመሪያ (CSRD) አካል ሆኖ ያገለግላል።
ቀደም ባለው እትም ላይ እንደተገለጸው፣ ሪፖርቱ የተዘጋጀው በአውሮፓ የኮርፖሬት ዘላቂነት ሪፖርት መመሪያ (CSRD) መርሆዎች እና ዘላቂ የፋይናንስ ሪፖርት ከሚደረጉ ግንባር ቀደም ዓለም አቀፍ ማዕቀፎች አንዱ በሆነው በዓለም አቀፍ የሪፖርት አቀራረብ ተነሳሽነት በተነሳ "ድርብ አቋማዊ ወይም አካላዊ" ግምገማ በመጠቀም ነው።
ይህ አካሄድ በተቋሙ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ውስጥም ተንፀባርቋል፣ ይህም ኢንቨስትመንቶች ከካቶሊክ እምነት መርሆዎች ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ በደንበኞች የተሰጡ ንብረቶችን ለመጠበቅ እና ለማሳደግ በሚሰራ ነው። ለሰው ልጅ ሕይወት፣ ለአካባቢ፣ ለኅብረተሰብ ወይም ለመልካም አስተዳደር ጎጂ እንደሆኑ በሚታሰቡ ተግባራት ላይ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ጋር የተያያዙ የፋይናንስ መሳሪያዎች ወይም መመሪያዎችን አያካትትም።
እ.አ.አ በ2025 ዓ.ም ሁሉም የንብረት አስተዳደር ምርቶች አዎንታዊ ጠቅላላ ትርፍ በማስመዝገብ ከካቶሊክ የሥነ ምግባር መርሆዎች ጋር ሙሉ በሙሉ የተጣጣሙ ሆነው ቀጥለዋል። በዓመቱ ውስጥ፣ IOR እ.አ.አ በ2024 ዓ.ም ከነበረው 50 ሚሊዮን ዩሮ ወደ 67.6 ሚሊዮን ዩሮ የኢኮኖሚ ዋጋ አስገኝቷል፣ ይህም እ.አ.አ በ2024 ዓ.ም ከነበረው 50 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ሲሆን የተጣራ ትርፍ 51 ሚሊዮን ዩሮ ነበር።
የተገኘው እሴት ለቅዱስ አባታችን (36%) ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዓለም ዙሪያ ለሚያከናውኑት የበጎ ተግባር ሥራዎች የሚውል፣ ለሠራተኞች (23%) እና ለአቅራቢዎች (14%) ተከፋፍሏል፣ የቀረው ድርሻ ደግሞ የተቋሙን ካፒታል ለማጠናከር፣ የረጅም ጊዜ መረጋጋት እና ዘላቂነትን ለመደገፍ ተጠብቆ ይቆያል።
የአደራ ንብረቶች አስተዳደርም በግምት 142.5 ሚሊዮን ዩሮ ዋጋ አስገኝቷል፣ ይህም ለIOR ሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ተልዕኮ አስተዋጽኦ አድርጓል።
ለሰዎች እና ለተፈጥሮ የሚደረግ ቁርጠኝነት
ሪፖርቱ በተጨማሪም ተቋሙ በሠራተኞች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያጎላል። እ.አ.አ በ2025 ዓ.ም ሰራተኞች ከ2,700 ሰዓታት በላይ የቴክኒክ እና የልዩ ባለሙያ ስልጠና አግኝተዋል፣ ይህም ከ300 ሰዓታት በላይ፣ አደጋን እንዴት ማስተዳደር እንደሚቻል እና ለኦዲት እንዲሁም ለሃይማኖት የሕነጻ ትህምርቶች ይሆን ዘንድ የተሰጡ ናቸው።
ተቋሙ ለ300 ደንበኞች የተዋቀረውን የፋይናንስ ትምህርት መርሃ ግብሩን ቀጥሏል፣ በካቶሊክ የሥነ ምግባር መርሆዎች እና በማህበራዊ ኃላፊነት ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ባህልን ያበረታታል።
ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር፣ IOR የአካባቢ ተፅዕኖውን በኃይል ቆጣቢነት መለኪያዎች፣ በታዳሽ የኃይል ምንጮች አጠቃቀም እና የጥሬ ዕቃዎችን ፍጆታ ለመቀነስ የታለሙ ተነሳሽነቶችን ለመቀነስ ጥረቱን ቀጥሏል።
በዓመቱ ውስጥ፣ ተቋሙ የIORPortal የመስመር (የሆንላይን) ላይ የባንክ አገልግሎትን ቀጣይነት ባለው ልማት እና የተመዘገቡ ሰነዶችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በማድረግ ሰነዶች ዲጂታል በሆነ መልኩ እንዲቀመጡ አስችሏል።
እነዚህ ተነሳሽነቶች በወረቀት ግዢዎች ላይ 37% ቅናሽ አድርገዋል፣ በተቋሙ የሚመነጩት ቆሻሻዎች በሙሉ ወደ መልሶ የመጠቀም (ሪሳይክሊንግ) ሂደቶች የተመሩ ናቸው።
እ.አ.አ የ2025 ዓ.ም የዘላቂነት ሪፖርቱን በማሳተም፣ IOR ከቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ እና የጋራ ጥቅምን ለማገልገል ካለው ተልዕኮ ጋር በሚስማማ መልኩ ጤናማ የፋይናንስ አስተዳደርን ከሰዎች እና ከአካባቢ እንክብካቤ ጋር ለማጣመር የሚያደርገውን ቀጣይ ጥረት ያጎላል።