ፈልግ

የቅዱስ ፒየስ 10ኛ የካህናት ወንድማማችነት ማሕበር በቤተክርስቲያን ተወገዘ! የቅዱስ ፒየስ 10ኛ የካህናት ወንድማማችነት ማሕበር በቤተክርስቲያን ተወገዘ!   (AFP or licensors)

የቅዱስ ፒየስ 10ኛ የካህናት ወንድማማችነት ማሕበር በቤተክርስቲያን ተወገዘ!

በካርዲናል ቪክቶር ማኑኤል ፈርናንዴዝ የተፈረመ ሰነድ፣ በሰኔ 14/2018 ዓ.ም የተከበረውን እርሳቸው በሰነዳቸው ውስጥ “የመለያየት ተግባር” ሲሉ የገለጹትን ሥነ ሥርዓት ያወገዙ ሲሆን ይህም ውግዘቱ ከባድ ቀኖናዊ ማጣቀሻዎችን በዝርዝር በመጥቀስ እና በማብራራት የተከናወነው ውግዘት መሆኑን ተገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የቅዱስ ፒየስ 10ኛ የካህናት ወንድማማችነት ማሕበር አልፎንሶ ደ ጋላሬታ እና በርናርድ ፌሌይ - በቅደም ተከተል ዋና ቀዳሽ እና ተባባሪ ቀዳሽ - እና አዲስ ሲመተ ጵጵስና የተሰጣቸው ጳጳሳት ፓስካል ሽሬይበር፣ ሚካኤል ጎልዴድ፣ ሚሼል ፖይንሲኔት ዘ ሲቭሪ እና ማርክ ሃናፒየር፣ በሮም ማዕከሉን ያደርገው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ሥልጣን፣ መንፈሳዊ እና ሐዋርያዊ የአስተዳደር አካል የሆነውን፣ በተለይም የሮም ጳጳስ እና የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ የሆኑትን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያንን በመምራት ረገድ የሚረዳውን ማዕከላዊ የአስተዳደር  ሐዋርያዊው መንበር (ወይም የቅድስት መንበር) ፈቃድ ሳያገኝ የተሰጡትን ሲመተ ጵጵስና እርሳቸው “የመለያየት ድርጊት” በማለት የገለጹትን በማከናወናቸው ለቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ተተኪ ብቻ የተወሰነውን በላቲን ቋንቋ "latae sententiae" (በራሱ ሥር) የተሰኘውን የቤተ ክርስቲያን ቀኖና በመጥቀስ ያለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፈቃድ ሲመተ ጵጵስና በማከናወናቸው ግዝት ወይም ውግዘት እንደ ተላለፈባቸው ተገልጿል።

ይህ የተገለጸው ሰኔ 25/2018 ዓ.ም በወጣው አዋጅ ላይ ሲሆን በቫቲካን የቀኖና እና የእምነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ በሆኑት በካርዲናል ቪክቶር ማኑዌል ፈርናንዴዝ በተፈረመው እና በተመሳሳይ የጽ/ቤቱ ሁለት ምክትል ጸሐፊዎች ተፈርሞ ይፋ በሆነው ሰነድ መሆኑ ተገልጿል።

ውሳኔው የተወሰደው ሰኔ 24/2018 ዓ.ም ጠዋት በስዊዘርላንድ ኤኮኔ ከተከበረው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ከሃያ አራት ሰዓታት በኋላ እንደ ነበረ ተያይዞ የደረሰን ዘገባ ያሳያል።

በቫቲካን የቀኖና እና የእምነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ድንጋጌ ሥርዓቱን በመፈጸም ተግባር ላይ የተሳተፉትን እና ሲመተ ጵጵስናውን የተቀበሉት ሰዎች ጭምር እንደ ተወገዙ የወጣው ሰነድ ይደነግጋል።

አሳዛኙ ክፍል የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ወንድማማችነት ማሕበር ጳጳሳትን እና ካህናትን በተደጋጋሚ ይህንን የሲመተ ጵጵስና አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት እንዳያከናውኑ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ሊዮ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ይህንን የማሳሰቢያ የማስጠንቀቂያ ድርጊት ችላ ብለው ድርጊቱን በመፈጸማቸው ምክንያት የወሰዱት ውሳኔ ውጤት ነው።

የውግዘት ተግባር የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ወንድማማችነት  ማሕበር ጳጳሳትን እና ካህናትን ከሮም ቤተክርስቲያን ይለያቸዋል።

ምዕመናንን በተመለከተ፣ በወንድማማችነት ሕግ መሠረት በይፋ እነዚህን ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እውቅና ውጪ ሲመተ ጵጵስና የተቀበሉትን ሰዎች በይፋ የሚከተሉ ምዕመናን እንደተወገዙ ይቆጠራሉ።

የጽ/ቤቱ ማስታወሻ

ከቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ ዘመን ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ፣ በዚህ በቫቲካን የእምነት እና የቀኖና ጉዳዮችን በሚመልከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ውስጥ እስከተደረጉት የቅርብ ጊዜ ንግግሮች ድረስ፣ በሊቀ ጳጳስ ማርሴል ሌፌብሬ የተጀመረውን የንቅናቄው አባላት ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር ወደ ሙሉ ህብረት ለመመለስ የተደረጉት ብዙ ሙከራዎች ከንቱ ሆነዋል።

ይህ ሁኔታ በቅርብ ጊዜ የቅዱስ አባታችንን ፈቃድ በመቃወም እና የቀኖና ሕግን በግልጽ በመጣስ በተከናወኑት የሲመተ ጵጵስና ተግባራት የበለጠ ተባብሷል።

ስለዚህ፣ ይህ ጽ/ቤት፣ በተሰጡት ተግባራት፣ ይህ ድርጊት የመከፋፈል ችግር እንደሆነ፣ ለቅዱሳን አገልጋዮች እና ለምእመናን ቀኖናዊ ውጤቶች እንዳለው መግለጽ አስፈላጊ እንደሆነ ያሳስባል። በእርግጥም፣ እ.አ.አ በ1988 እንደተገለጸው፣ “እንዲህ ዓይነቱ አለመታዘዝ - በተግባር የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን የበላይነት አለመቀበልን የሚያሳይ - የተመከፋፈል ድርጊት ነው” (ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በላቲን ቋንቋ ' Ecclesia Dei' (የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያ) በተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት አንቀጽ 3 ላይ እንደ ተጠቀሰው)።

ከአሁን በኋላ በዚህ ጉዳይ

1. የቅዱስ ፒየስ 10 የክህነት ወንድማማችነት አባል የሆኑት አገልጋዮች ለቤተክርስቲያን ቀኖና እና ሕግ የማይታዘዙ በመሆናቸው ምክንያት የተነሳ እንደ ከፋፋይ ተደርገው መታየት አለባቸው (በላቲን ቋንቋ፣ Ecclesia Dei  "የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን" ጳጳሳዊ መልእክት አንቀጽ 5 እና 'ከሃዲ፣ መናፍቅ እና መለያየትን የሚፈጥር ሰው በውግዘት ሊወገድ ይገባዋል' የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀኖና 1364) እንደ ተገለጸ፣ በዚህ ሕግ በተደነገገው መሰረት ለውግዘት ተገዢ ናቸው።

2. ምዕመናንን በተመለከተ፣ የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ የካህናት ወንድማማችነትን በይፋ የሚከተሉ ሰዎች እ.አ.አ በ1996ቱ የሕግ አውጪ ጽሑፎች የጳጳሳዊ ምክር ቤት ማብራሪያ ማስታወሻ ደንብ መሰረት (አንቀጽ 7) ላይ በተደነገገው መሠረት የቤተክርስቲያንን አንድነት እንደ መለያየት ተደርገው ሊወሰዱ ይገባል በተሰኘው ሕገ ደንብ መሰረት፣ ይህም በሥራ ላይ የቆየ እና ይህ በቫቲካን የእምነት እና የቀኖናዎችን ጉዳይ የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት የራሱ አድርጎ የሚቀበለው ሕግ በመሆኑ የተነሳ የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ የካህናት ወድማማቾችን በይፋ የሚከተሉ ሰዎች የውግዘቱ አካል ናቸው።

3. በመጨረሻም፣ የእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ የቅዱስ ፒየስ 10ኛ የካህናት ወንድማማችነት ማሕበር ቅዱሳት ምስጢራትን ያለአግባብ እንደሚያቀርቡ እና በእነሱ የሚተዳደረው ምስጢረ ንስሐ እና በእነሱ የሚደገፉ ጋብቻዎች ዋጋ እንደሌላቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ቤተክርስቲያኗ፣ እንደ አሳቢ እናት፣ ወደ ሙሉ ሕብረት ለመመለስ ለሚፈልጉ ሁሉ በቅን ልቦና እና ሕያው በሆነ ልመና ትቀበላለች። ሐዋርያዊ ጳጳሳት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸውን ሂደቶች ያዘጋጃሉ።

በመጨረሻም፣ ሁሉም ምእመናን ከሮማው ጳጳስ፣ ከጳጳሳት ጋር በኅብረት እና ከመላው ቤተክርስቲያን ጋር (ሉመን ጄንሲዩም አንቀጽ 22፤ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሕገ ቀኖና አንቀጽ  751) ጋር በኅብረት እንዲቀጥሉ እና ከላይ በተጠቀሰው የቅዱስ ፒየስ 10ኛው የካህናት ወንድማማችነት በሚያበረታቱ በዓላት እና ተግባራት ላይ ከመሳተፍ እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ማህበር እ.አ.አ በ1970 ዓ.ም በሊቀ ጳጳስ ማርሴል ሌፌብሬ የተመሰረተ፣ በዓለም ዙሪያ 720 ካህናት፣ 700 አብያተ ክርስቲያናት እና ከግምሽ ሚልዮን በላይ የሚቆጠሩ ምዕመናን አቅፎ የያዘ የካቶሊክ ካህናት ወንድማማችነት ማሕበር ነበር።

02 Jul 2026, 15:38