በካስቴል ጋንዶልፎ የሚገኝ የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የአትክልት ሥፍራ በካስቴል ጋንዶልፎ የሚገኝ የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የአትክልት ሥፍራ   (© Mauro Salvatori, The Prince Albert II of Monaco Foundation)

በ“ሰው እና ተፈጥሮ” ርዕሥ የተዘጋጀ ኤግዚቢሽን በ“ውዳሴ ላንተ ይሁን” መንደር መከፈቱ ተገለጸ

የሞናኮ ፋውንዴሽን ልዑል አልበርት ዳግማዊ እና የዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የወጣቶች ፋውንዴሽን በመተባበር ያዘጋጁት አዲስ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን በካስቴል ጋንዶልፎ የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የአትክልት ሥፍራ ተከፍቷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“ሰው እና ተፈጥሮ” በሚል ርዕሥ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽኑ በ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” መንደር የተከፈርተው ዓርብ ሰኔ 26/2018 ዓ. ም. ሲሆን እስከ ሐምሌ ወር መጨረሻ ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል።

የጣሊያኑ ፋውንዴሽን ቅርንጫፍ በሆነው የሞናኮ ፋውንዴሽን አባል ልዑል አልበርት ዳግማዊ ድጋፍ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽኑ ጎብኚዎች የሰው ልጅ በፍጥረት ውስጥ ያለውን ቦታ እንዲያይ እና እንዲያስብበት የሚያግዝ እንደ ሆነ ታውቋል።

ኤግዚቢሽኑ ከመከፈቱ አስቀድሞ የተካሄደ ስብሰባ
ኤግዚቢሽኑ ከመከፈቱ አስቀድሞ የተካሄደ ስብሰባ   (© Mauro Salvatori, The Prince Albert II of Monaco Foundation)

ከዚህ በፊት ሽልማትን ባገኙ ፎቶግራፎች ስብስብ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽኑ ተፈጥሮን የሚገልጹ የሞናኮ ፋውንዴሽን ፎቶግራፍፎች ስብስብ ሲሆን፥ ለዝግጅቱ ድጋፍ ያደረጉት በቅድስት መንበር የሞናኮ ርዕሠ መስተዳድር ኤምባሲ፣ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” መንደር እና ሌሎች የግል ድርጅቶች መሆናቸው ታውቋል።

ሁሉም ፎቶዎች የሕይወት ዓይነቶችን የሚገልጹ እና በመካከላቸው ያለውን ጥልቅ ግንኙነቶች የሚያሳዩ እንደሆኑ ታውቋል። ይህም ጎብኚዎች ብዝሃ ሕይወት የምድራችን ሚዛን መሠረት እንደሆነ እና የዚህ ግንኙነት መቋረጥ ሁሉን የሰው ልጅ የሚጎዳ መሆኑን ያስታውሳሉ። ከዚህም በላይ ኤግዚቢሽኑ ጎብኚዎች የሥነ-ምህዳር ተጋላጭነትን እና እነሱን የመጠበቅ ኃላፊነትን በመገንዘብ የፍጥረትን ውበት እንዲገነዘቡ ይጋብዛል። ኤግዚቢሽኑ ከሮም እና ከካስቴል ጋንዶልፎ በተጨማሪ በሌሎች የጣሊያን ከተሞችም እንደሚዘጋጅ ታውቋል።

እንክብካቤ ለማድረግ በቅድሚያ ፍጥረትን ማወቅ

ኤግዚቢሽኑ ከመከፈቱ ጥቂት ደቂቃዎች አስቀድሞ “እንክብካቤን ለማድረግ ስለ ፍጥረት ማወቅ” በሚል ርዕሥ የተዘጋጀው ጉባኤ በሰው ልጅ እና በአካባቢ መካከል ስላለው ደካማ ሚዛን የሚገልጽ መንፈሳዊ፣ ሳይንሳዊ እና ባህላዊ አመለካከቶችን አቅርቧል።

ይህ ተነሳሽነት የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን፣ የዲፕሎማሲ ተወካዮችን፣ የተቋማት ሰዎችን፣ ምሁራንን፣ የሳይንስ ጥበብትን እና ባለሙያዎችን በአንድ ላይ አሰባስቦ የተቀናጀ ሥነ-ምህዳር ተግዳሮትን፣ የብዝሃ ሕይወት ጥበቃን እና የሰው ልጅ የጋራ መኖሪያ ምድርን ለመንከባከብ ያለውን የጋራ ኃላፊነት እንዲያስብ አድርጓል።

የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” ከፍተኛ የትምህርት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ካርዲናል ፋቢዮ ባጆ እንግዶችን በደስታ የተቀበሏቸው ሲሆን፥ እንግዶችም በበኩላቸው ተነሳሽነቱን በማስተባበር በጊዜያችን ላሉ የሥነ-ምህዳር ተግዳሮቶች ምላሽ ለመስጠት፣ ግንዛቤን ለማስጨበጥ እና እርምጃን ለማስተዋወቅ በሮችን ከፍተዋል።

ፕሮግራሙ የተጀመረው በ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” መንደር በተደረገ ጉብኝት ሲሆን ተሳታፊዎች የተቀናጀ ሥነ-ምህዳርን ለማስፋፋት የቅድስት መንበርን ቁርጠኝነት የሚገልጹ ተጨባጭ መግለጫዎችን እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

“የታሪክ ግንዛቤ ብቻውን በቂ በማይሆንበት ወቅት ላይ እንገኛለን” ያሉት በሞናኮ የሚገኝ የጣሊያን ቅርንጫፍ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ማርኮ ኮላሳንቲ በንግግራቸው “ዛሬ እውቀትን ወደ ኃላፊነት እና ኃላፊነትን ወደ ተጨባጭ ተግባር እንድንለውጥ ተጠርተናል” ብለዋል።

የአካባቢ ጥበቃ በባሕል፣ በሳይንስ፣ በተቋማት እና በመንፈሳዊነት መካከል በሚደረግ ውይይት ብቻ የሰውን ክብር፣ የኑሮ ጥራት፣ ማኅበራዊ ፍትህ እና የወጣት ትውልድን የወደፊት ሁኔታ ይመለከታል” ብለው፥  “ለፍጥረት በሚሰጥ አክብሮት ላይ የተመሠረተ ትክክለኛ የልማት ሞዴል መገንባት እንደሚቻል ጠይቀዋል።

በካስቴል ጋንዶልፎ የሚገኝ የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የአትክልት ሥፍራ
በካስቴል ጋንዶልፎ የሚገኝ የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የአትክልት ሥፍራ   (© Mauro Salvatori, The Prince Albert II of Monaco Foundation)

“ስለማናውቀው ነገር መጠበቅ አንችልም” ሲሉ የተናገሩት ፕሬዝዳንት ማርኮ ኮላሳንቲ፥ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ሊለይ እንደማይችል አፅንዖት ሰጥተው፥ በቫቲካን ኤግዚቢሽኑን ለማስተናገድ ዕድል በማግኘታቸው ካርዲናል ፋቢዮ ባጆን አመስግነዋል።

ፍጥረትን የመጠበቅ ግዴታ

የዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የወጣቶች ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ዳኒኤል ብሩኖ በበኩላቸው፥ የፍጥረት ውበት ጌጥ ሳይሆን ጥሪ፣ ልዩ መብት ሳይሆን ግዴታ መሆኑን በመግለጽ፥ ወጣቶች ፍጥረትን በመጠበቅ ላይ ላላቸው ጠቃሚ ሚና አፅንዖት ሰጥተዋል።

በተለይም እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2013 ዓ. ም. ጀምሮ በዓለም የወጣቶች ፌስቲቫሎች አማካኝነት የዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የወጣቶች ፋውንዴሽን የፍጥረት እንክብካ ለማሳደግ እና በወጣቶች መካከል ወንድማማችነትን ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ዳኒኤል ብሩኖ በተጨማሪም፥ በቅርቡ ይፋ የሆነው “የሰው ልጅ ታላቅነት” ሐዋርያዊ ሠነድን ጨምሮ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” እና “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በሚሉት ሐዋርያዊ ሠነዶች ውስጥ የተካተቱት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት መልዕክቶች ወንድማማችነትን እና ቴክኖሎጂን ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ መጠቀምን በማስመልከት የሚቀርቡ ትምህርቶችን ተግባራዊ ማድረግ እና ማጋራት እንደሚያስፈልግ አስታውሰዋል።

በተጨማሪም በኮርያ መዲና ሴኡል ላይ የሚከበረውን የዓለም ወጣቶች ቀን በማስመልከት ፋውንዴሽኑ ፍጥረትን ለመጠበቅ በተለይም በወንድማማችነት ጭብጥ ላይ አምስተኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ እንደሚኖር አስታውቀዋል።

ኤግዚቢሽኑ በጳጳሳዊ የአትክልት ሥፍራ ውስጥ ለማስተናገድ የተደረገው ውሳኔ ድንገተኛ አለመሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንት ብሩኖ፥ ቦታው ከታሪኩ እና ከጥሪው ጋር በመሆን የፎቶግራፎቹን መልዕክት የሚያጎላ እና ለተጨባጭ የጋራ ቁርጠኝነት የሚጋብዝ መሆኑን አቶ ብሩኖ አስረድተዋል።

በሞናኮ የሚገኝ ፋውንዴሽን ያዘጋጀው የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን
በሞናኮ የሚገኝ ፋውንዴሽን ያዘጋጀው የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን   (© Mauro Salvatori, The Prince Albert II of Monaco Foundation)

 

22 Jul 2026, 15:10