ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በማድሪድ ስታዲየም ከሀገረ ስብከቱ ምዕመናን ጋር ሲገናኙ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በማድሪድ ስታዲየም ከሀገረ ስብከቱ ምዕመናን ጋር ሲገናኙ  (@Vatican Media) ርዕሰ አንቀጽ

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድሪድ ወደር የሌለውን ተቀባይነት ማግኘቱ ተገለጸ

የቅድስት መንበር መገናኛ ምክትል የአርታኢ ዳይሬክተር ማሲሚሊዮኖ ሜኒኬቲ በማድሪድ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት የተሰጠውን የእምነት፣ የአንድነት እና የፍቅር መግለጫ ከፍተኛ ምላሽ ጥቅሶ፥ ቅዱስነታቸው ለምዕመናኑ ባስተላለፉት መልዕክትም ስፔይን እና አውሮፓ ወንጌልን ወደ ሰላም፣ ወደ አንድነት እና ወደ ተሃድሶ የሚወስድ መንገድ አድርገው እንዲውስዱት ማሳሰባቸውን አስታውሷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በስፔይን በማድረግ ላይ ባሉት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው፥ በማድሪድ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን፣ ገዳማውያን እና ገዳማውያት በኅብረት ሆነው ባከበሩት ደማቅ በዓል ጉልህ መሆኑን ማሲሚሊያኖ ገልጿል።

በማድሪድ አደባባዮች፣ ጎዳናዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች እና ስታዲየሞች በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ምስል እና በስፔይን ባንዲራዎች ለቀናት ማሸብረቃቸው፥ ምእመናንን በእምነታቸው ለማጠናከር፥ የሰላም፣ የአንድነት እና የስምምነት መልዕክቶችን ይዘው ለመጡት የሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ የቀረበ የፍቅር መግለጫዎች መሆናቸውን ማስሚሊያኖ አስረድቷል።

ምዕመናኑ በማድሪድ ስታዲየም የተዘጋጀውን ስብሰባ የተሳተፈው በጸሎት ሥነ-ሥርዓት በተመስጦ ሲሆን፥ ቅዱስነታቸው ለስፔይን ፓርላማ ያደረጉት ንግግር በረጅም የተጨበጨበለት የማይረሳ ክስተት እንደ ነበርም ተመልክቷል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለመንግሥታዊ ተቋማት ባስተላለፉት መልዕክት፥ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አብሮነት ለእያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት ከሚደረግ እንክብካቤ፣ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ከሚደረግ ድጋፍ፣ ከኅሊና እና ከሃይማኖት ነፃነት ጥበቃ፣ ሁሉንም ጦርነቶች እና የዓመፅ ድርጊቶችን ውድቅ ከማድረግ ተነጥሎ ሊታይ እንደማይችል አረጋግጠው፥ ፍትሃዊ ማኅበረሰብ ለአደጋ ለተጋለጡት በሚያደርገው እንክብካቤ የሚለካ መሆኑን አስገንዝዋል።

የቅዱስነታቸው የመጀመሪያዎቹ የስፔይን ሐዋርያዊ ጉብኝት ምስሎች፥ ከብዙ ዓመታት በኋላ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን ለመቀበል ያለውን ጉጉት የሚገልጹ እውነተኛ ምላሾች፣ ሕያው ሕሊና እና መልካም የሆነውን ነገር የሚያረጋግጡ እንደሆኑ ተመልክቷል።

በተገንጣዮች ጫና፣ በፖለቲካ ውጥረት፣ በልዩነት እና በዓለማዊነት የምትታወቀው ስፔይን ጠንካራ እምነት እንዳላት፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት ምላሽ በመስጠት እና ለኢየሱስ ክርስቶስ መታዘዟን ብዙዎች ተናግረው፥ በእያንዳንዱ ዝግጅት፣ ጉባኤ እና የጸሎት ሥነ-ሥርዓት ላይ ሰዎች የጋራ ቋንቋን እና የጋራ ትዝታን ሲያጠናክሩ ተመልክቷል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአሰቃቂ በደል የቆሰሉት ሰዎች ስቃይን በመቀበል፥ የአገሪቱ ቤተ ክርስቲያን በብዝሃነት መካከል የአንድነት ምሳሌ እንድትሆን ጋብዘው፥ ለአገሪቱ ሕዝቦች በሙሉ ባስተላለፉት መልዕክትም፥ የወንጌልን ደስታ፣ የፍቅርን ኃይል እና ዛሬ ኢየሱስ ክርስቶስን በሥር ነቀል ቁርጠኝነት እንደገና እንዲያገኙ አሳስበው፥ ይህም ወንድማማችነት፣ ሁሉን አቀፍ፣ ደጋፊ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ሰብዓዊ እና ሰላም ያለበት ልዩ ዓለምን ለመገንባት መሆኑ ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለስፔይን ሕዝብ ባደረጉት ንግግር፥ ዓይናቸውን ወደ ፈጣሪ እንዲያነሳ እና ይህም አገሪቱን፣ አውሮፓን እና መላውን ዓለም በእውነት ማደስ የሚችል እውነተኛ መንገድ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህ መንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የወዳጅነት ዘርን በመዝራት፣ እርሱን መቀበል የእያንዳንዱን ሰው ሕይወት ሊለውጥ እንደሚችል፣ ሰዎችን ከራስ ወዳድነት፣ ከብዝበዛ፣ ከክፋት እና ከጥላቻ የሚያድኑ መንገዶች እንደሚፈጠሩ፣ ወደ እያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት የሚደርስ የሕይወት እና የፍቅር ኃይል የሚዘረጋ መሆኑን ማሲሚሊያኖ አስረድቷል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በማድሪድ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ወቅት ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት የዓለምን አመክንዮ ወደ ራሳቸው በማዞር፥ አንደኛው ወገን በሌላኛው ላይ ድልን በሚቀዳጅበት መንገድ ሳይሆን ይልቁን በእያንዳንዱ የሰው ልጅ ልብ ውስጥ ለሚኖረው ትርጉም ፍለጋ በሩን እንደገና ከፍቶ ሕይወትን በሙላት ለመኖር የሚያስችለውን መንገድ በማሳየት መሆኑን ማሲሚሊያኖ ተናግሯል።

10 Jun 2026, 15:34