ቅዱስ ሲኖዶስ የጳጳሳት ምርጫ እና አዳዲስ ርዕሦችን የተመለከተ የመጨረሻ ሪፖርት ይፋ አደረገ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
የጥናት ቡድኖች 7 እና 9 የመጨረሻ ሪፖርቶች ጳጳስን በመምረጥ ረገድ ማስተዋል ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን በማረጋገጥ፥ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያጋጥሟቸውን እጅግ አስቸጋሪ ጥያቄዎችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል ለማወቅ የሚያግዙ የተወሰኑ ሥነ-መለኮታዊ መስፈርቶች እንዳሉ የጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች ገልጸዋል።
የጥናቱ ሂደት ወደፊት መቀጠሉ እንዳለ ሆኖ፥ አንድ ጳጳስ ለሐዋርያዊ ጉብኝት ወደ ሮም የሚያደርጋቸው ጉዞዎች፣ ለጵጵስና የሚያዘጋጅ ስልጠና እና የጳጳሳት ምርጫ መስፈርቶችን የተመለከተ የመጨረሻው ሪፖርት ቀዳሚ ክፍል ይፋ ሆኗል። በመቅድሙ ላይ እንድተገለጸው፥ “ያለ መንጋ እረኛ የለም፥ ያለ እረኛ መንጋ የለም” የሚለውን መሠረታዊ ፅንሰ-ሃሳብ ተጨባጭነት በድጋሚ አረጋግጧል።
ለጳጳስነት የሚታጩትን በተመለከተ ሲኖዶሳዊ ብቃትን የመረጠው የጥናት ቡድን 7 ሪፖርት፥ ካኅናት ኅብረትን ለመገንባት፣ በውይይት ላይ ለመሳተፍ፣ የአካባቢ ባሕሎችን ለማወቅ እና ከእነርሱም ጋር ለመቀራረብ ፍላጎት እንዳለው የማሳየት ችሎታን ያካትታል። የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ እንደራሴዎችንም በማማከር ሲኖዶሳዊ እና ሚስዮናዊ ገጽታ እንዲኖራቸው ጥሪ በማቅረብ እና ይህንን ገጽታ ለጳጳስነት በተጠቆሙት ካኅናት ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ ይችላል።
ሪፖርቱ እያንዳንዱ ሀገረ ስብከት ስለ ሁኔታው እና ስለ ፍላጎቶቹ በየጊዜው የማሰላሰል ሂደቶችን ማከናወን እንዳለበት ገልጾ፥ እነዚህ ሂደቶች የሲኖዶስዊት እና ሚስዮናዊት ቤተ ክርስቲያን መመዘኛዎችን የሚያሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ ገንቢ ልምዶችን መጋራት ያበረታታል።
“የስመተ ጵጵስና ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ ጳጳሱ የካኅናት ምክር ቤትን እና የሀገረ ስብከቱ ሐዋርያዊ ምክር ቤት አባላትን ሰብስቦ አባላቱ በአንድነት መንፈስ ከሀገረ ስብከቱ ፍላጎቶች እና ሃሳቦች ጋር ይስማማል ብለው የሚያስቧቸውን ካህናት ስሞች በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ለጳጳሳት ምክር ቤት ያቀርባል” ይላል። “በተቻለ መጠን የምክክር ሂደቱ የጳጳሳት ጉባኤን፣ የፋይናንስ ምክር ቤትን፣ የምእመናን ምክር ቤትን፣ የገዳማውያን እና ገዳማውያት፣ የወጣቶች እና ድሃ ማኅበረሰብ ተወካዮችን ማካተት አለበት” ይላል።
በምክክር ሂደት ገዳማውያንን እና ምዕመናን መሳተፍ
የጥናት ቡድኑ “ብቁ የሚሆኑትን ለማዘጋጀት የሚደረግ ጥረት” ሲል የገለጸውን በማበረታታት፥ ይህም ሁሉንም የእግዚአብሔር ሕዝብ የማስተዋል አቅማቸው እንዲያሳድግ ለመርዳት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ቀጣይነት ባለው በካኅናት ምሥረታ ጳጳሱን ማገዝ የሚችሉ የተወሰኑ ቡድኖችን የመፍጠር ሃሳብን በማቅረብ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የጳጳስ ጽሕፈት ቤት ባዶ በሚሆንበት ወቅት ሐዋርያዊ እንደራሴው ስለ ሀገረ ስብከቱ ሁኔታ፣ ስለ አዲሱ እረኛ እና ጳጳስ ሊሆኑ የሚችሉ እጩ ካኅናት ገጽታ በሚገባ ማብራራት የሚችል ቡድን ሊያማክር ይችላል።
ቡድኑ በምክክር ሂደቶች ቤተ ክኅነትን ብቻ ሳይሆን በተቻለ መጠን ተመጣጣኝ ቁጥር ያላቸውን ገዳማውያን እና ገዳማውያት፣ ምዕመናንም ጭምር እንዲያሳትፉ ያደርጋል። ዓላማው በተቻለ መጠን እውነትን ሙሉ በሙሉ ለማውጣት እንደሆነ ያስረዳል።
ሪፖርቱ በተጨማሪም በሮም የሚገኙ የቅድስት መንበር ከፍተኛ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቶች ሂደቶቻቸውን በሲኖዳላዊነት አቅጣጫ እንዲገመግሙ እና በምርጫ ሂደቶች በየጊዜው ገለልተኛ የሆኑ ግምገማዎችን እንዲያቀርቡ ይጠይቃል።
የቋንቋ እና የስልታዊ አርዓያነት ለውጥ
የመጨረሻው የጥናት ቡድን 9፥ በሐዋርያት ሥራ ምዕ. 10-15 ላይ በተጠቀሰው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምስል ላይ በማትኮር፥ ይህም የባሕል ልዩነት የወንጌልን አዲስነት ሳይክድ እንዴት ዋጋ ሊሰጠው እንደሚችል ያሳያል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ እጅግ አስቸጋሪ የሆኑ ሐዋርያዊ እና ሥነ-ምግባራዊ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጥያቄዎችን በምትመልስበት ስልት ለውጥን እንደ ሃሳብ ያቀርባል። ሪፖርቱ በመጀመሪያ እነዚህን ጥያቄዎች “አወዛጋቢ” ከሚላቸው ይልቅ “አዲስ” የሚል ቅጽል መጠቀምን ይመርጣል።
ሪፖርቱ፥ “ዋና ዓላማው ችግሮችን መፍታት ብቻ ሳይሆን በአዲስ የግንኙነት መንገድ አማካይነት በኅብረት መማር እና በግልጽነት የጋራ ጥቅምን መገንባት ነው” ሲል አስረድቶ፥ በተጨማሪም “መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በሥራ ላይ ባለው ጣልቃ ገብነት ላይ ኃላፊነትን ሳይወስድ የወንጌል ምስክርነት ሊኖር በመሆኑ የሐዋርያዊነት መርህን ያስተዋውቃል።
ሪፖርቱ እነዚህን ጥያቄዎች ለመፍታት የሚረዱ ሦስት ስልታዊ ደረጃዎችን እነርሱም፥ “ራሳችንን ማዳመጥ፣ እውነታን ማዳመጥ እና ልዩ ልዩ የእውቀት ዓይነቶችን ማሰባሰብ” የሚሉትን ለይቶ በማቅረብ በመንፈስ ቅዱስ ዕርዳታ የሚደረግ ውይይት የቤተ ክርስቲያንን የሲኖዶስዊነት ባሕል ለማዳበር ልዩ መሣሪያ ሆኖ መቀጠሉን ያስታውሳል።
ለግንዛቤ መሠረት የሆኑ ተጨባጭ ምስክርነቶች
ሪፖርቱ እነዚህ መመሪያዎች በካቶሊካዊ ግብረ ሰዶማውያን ተጨባጭ ልምድ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተግባራዊ እንዲሆኑ ይጠይቃል።
በተለይም በሰላማዊ ወይም ዓመፅ በሌለበት መንገድ በሚለው ላይ ቡድኑ፥ የሰርቢያ ወጣቶች ከጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ምዕምናን ተነሳሽነትን በማግኘት ሚሎሴቪችን በሰላማዊ መንገድ ከሥልጣን ለማውረድ አስተዋጽኦ ባደረጉበት ምስክርነት ተመርቷል።
በሁለቱም ሁኔታዎች ውስጥ ምስክርነት ለሥነ-ምግባር እና ሥነ-መለኮታዊ ግንዛቤ መንገዶች እንዲሁም ለክፍት ጥያቄዎች መነሻ ነጥብ ሆኖ ያገለግላል። ስለዚህ እያንዳንዱ ማኅበረሰብ “እግዚአብሔር በታሪክ እና በሰዎች ተሞክሮ ውስጥ የሚሠራውን መልካም ነገር የማወቅ እና የማስፋፋት ኃላፊነት” ሊወስድ እንደሚችል በመግለጽ ሪፖርቱ የቡድን 7 እና የቡድን 9 ጥናት ውጤት ያጠቃልላል።