ፈልግ

16ኛው የብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤ 16ኛው የብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤ  (Vatican Media)

ቅዱስ ሲኖዶስ ድህነትን፣ የአካባቢ ጥበቃን እና ከአንድ በላይ ጋብቻን የተመለከቱ ሪፖርቶችን አቀረበ

የቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የጥናት ቡድን 2፥ “የድሆችን እና የምድርን ጩኸት መስማት” በሚል የቀረበውን ሪፖርት ጨምሮ “ከአንድ በላይ ጋብቻ በሐዋርያዊ ተግባር ላይ የደቀነው ፈተና” የሚለውን የአፍሪካ እና የማዳጋስካር ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ምክር ቤት (SECAM) የመጨረሻ ሪፖርቶችን ይፋ አድርጓል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ዋና ጽሕፈት ቤቱ ዛሬ “የድሆችን እና የምድርን ጩኸት መስማት” የሚለውን ጨምሮ የአፍሪካ እና የማዳጋስካር ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ (SECAM) “ከአንድ በላይ ጋብቻ በሐዋርያዊ ተግባር ላይ የደቀነው ፈተና” በሚል ያዘጋጀውን በማካተት የጥናት ቡድን 2 የመጨረሻ ሪፖርቶች አሳትሟል።

ሁለቱም ሪፖርቶች በጭብጥ ልዩነታቸው  ሌሎችን ምታዳምጥ፣ የምታስብ እና የምትደግፍ፣ መሠረቷን በወንጌል ላይ ያደረገች፣ ለዘመናችን ተግዳሮቶች ምላሽ የምትሰጥ እና ሳታቋርጥ ወደ እያንዳንዱ መእመን የምትቀርብ ቤተ ክርስቲያን መሆንኗን በሲኖዶሳዊነት ተመልክቷል። የመጨረሻ ሪፖርቶቹ በሲኖዶሱ ዋና ጽሕፈት ቤት ድረ ገጽ ላይ www.synod.va በአምስት ቋንቋዎች ይፋ ሆነዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እነዚህ የመጨረሻ ሪፖርቶች በሲኖዶሱ ጉባኤ ወቅት የተከናወኑ የማስተንተን እና የማስተዋል ፍሬዎችን በግልጽነት እና በተጠያቂነት መንፈስ ለሌሎች ይፋ እንዲሆኑ መመሪያ ሰጥተዋል። የጥናት ቡድኖች የመጨረሻ ሪፖርቶችን ለሲኖዶሱ ዋና ጽሕፈት ቤት በማስረከብ ኃላፊነት አጠናቅቀዋል።

የቡድን 2 የመጨረሻ ሪፖርት

የቡድን 2 የመጨረሻ ሪፖርት “የድሆችን እና የምድርን ጩኸት መስማት” በሚለው ላይ በርካታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፥ ሪፖርቱ ከዚህ በፊት ቤተ ክርስቲያን የድሆችን እና የምድርን ጩኸት በተሻለ መንገድ መስማት እንደምትችል ለቀረቡት አምስት መሠረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል።

ሠነዱ የድሆችን እና የምድርን ጩሄት ማዳመጥ ሐዋርያዊ ምርጫ እንዳልሆነ ከሚገልጸው ሥነ-መለኮታዊ እምነት የሚመነጭ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልዕኮ የሚወክል የእምነት ተግባር ሲሆን፥ በሁለት የፍቅር ትእዛዝ እና በመልካሙ ሳምራዊ ምሳሌ ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ታውቋል። ብጹዕ ካርዲናል ቼርኒ በሠነዱ መግቢያ ላይ  “ማዳመጥ” የሚለው ቃል እርስ በርስ መገናኘትን፣ ችግርን መረዳትን፣ እርምጃ መውሰድን፣ መገምገምን እና መንፈሳዊ ድጋፍ መስጠትን የሚያካትት እና እያንዳንዱን ክርስቲያን ጨምሮ ድህነት የሚሰማቸውን የሚያካትት ዋና ሂደት መሆኑን አስታውሰዋል።

የቡድኑ ሥራ መሪ ጥያቄ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ሁለት የተያያዙ ጩሄቶችን እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማዳመጥ ትችላለች? ለድሆች ጩኸት ምላሽ መስጠት ለምድር ጩኸት ምላሽ መስጠት የሚል እንደሆነ ታውቋል።

ቡድኑ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ማለትም ቁምስናዎችን፣ ማኅበረሰቦችን፣ እንቅስቃሴዎችን፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን፣ የአብያተ ክርስቲያናት እና ዓለም አቀፍ አውታረ መረቦች ሚናን ያጎላል። በተመሳሳይም ተገቢ ባልሆነ መንገድ ለልዩ መዋቅሮች ውክልና የመስጠት ፈተናን እንዲያሸንፉ ጥሪ በማቅረብ እያንዳንዱ የተጠመቀ ሰው ኃላፊነትን በጋራ እንዲወስድ ያስታውሳል።

ከተጨባጭ ሃሳቦች መካከል በአብዛኛው በአካል ጉዳተኞች የተዋቀረ ንዑስ ቡድን የሚጠቁመውን አብነት መሠረት ያደረገ ሲሆን ይህም ለተገለሉ ቡድኖች ድምጽ ለመስጠት በአካባቢው እና በክልል ደረጃ ሊደገም የሚችል ሞዴል እንደሆነ ታውቋል።

በሥነ-መለኮት ደረጃ ሪፖርቱ ድሆችን እና ምድርን እንደ ትክክለኛ ሥነ-መለኮታዊ ምህዳር በማዳመጥ የሥነ-መለኮት አስፈላጊነትን አጉልቶ ያሳያል። እጅግ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦች የመጡ የሃይማኖት ሊቃውንት በሠነዶች ዝግጅት ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ያቀርባል። ለምዕመናን፣ ለሃይማኖት እና ለዘርዓ ክህነት ተማሪዎች የሚሰጥ የሥልጠና ፕሮግራሞችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለስልጠና ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል።

ሪፖርቱ የሚያበቃው የማዳመጥ መንገዶችን በማቅረብ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ አባል እጅግ ተጋላጭ ከሆኑት ጋር በሚስዮናዊነት መንገድ መለወጥ የሚችልበት የሲኖዳዊት ቤተ ክርስቲያን ራዕይን በማቅረብ እንደሆነ ተመልክቷል።

ከአንድ በላይ ጋብቻን የተመለከተ ታሪክ

ከአንድ በላይ ጋብቻ ላይ ያተኮረው የአፍሪካ እና የማዳጋስካር ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ምክር ቤት እንደ ጎርጎርሳውያን ጥቅምት ወር 2023 ዓ. ም. በጳጳሳት ሲኖዶስ ጉባኤ 16ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ነው። ይህም የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ምክር ቤት ከአንድ በላይ ጋብቻ ሥነ-መለኮታዊ እና ሐዋርያዊ ግንዛቤ እንዲያበረታታ እና ወደ እምነት እየመጡ ያሉ ከአንድ ሚስት በላይ ያላቸውን ሰዎችን እንዲያግዝ አበረታቷል። በዚህ መሠረት የአፍሪካ ቤተ ክርስቲያን በአህጉራዊ የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ምክር ቤት አማካኝነት፣ የተወሰነ የባለሙያዎች ቡድን አቋቁማለች።

የባለሙያዎች ቡድን ከተለያዩ የአፍሪካ ክልሎች እና ደሴቶቿ የተውጣጡ 12 ባለሙያዎችን ያቀፈ ሲሆን እንደ ዶግማ፣ መሠረታዊ ሥነ-መለኮት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፣ የሐዋርያዊ እንክብካቤ፣ የሕገ ቀኖና እና የሕዝብ እና ባሕል ጥናት ያሉ የተለያዩ ዘርፎችን የሚወክሉ ሰዎች በአካል እና በበይነ መረብ ተሰብስበዋል።

የአፍሪካ እና የማዳጋስካር ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ምክር ቤት ሪፖርት ጠቅላላ እይታ

በአፍሪካ አህጉር ባህላዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-መለኮታዊ አውድ ላይ የተመሠረተውን ከአንድ በላይ ጋብቻ በሐዋርያዊ ተግባር ላይ የደቀነውን ፈተና በማስመልከት አስተንትኖ አዘጋጅቷል።

ሪፖርቱ የሚጀምረው የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር በገባው ቃል ኪዳን ላይ የተመሠረተውን የአፍሪካ ቤተሰብ ቅዱስ እሴት በመገንዘብ ሲሆን፥ በዚህ ውስጥ ልጅ እንደ መለኮታዊ በረከት ተደርጎ የሚቆጠርበት እና ለብዙ ልጆች የመውለድ ፍላጎት የኅብረተሰቡ ማንነት ዋና አካል እንደሆነ ያቀርባል። በዚህ አድማስ ውስጥ ከአንድ በላይ የማግባት ታሪካዊ ህልውና የሚገኝበት ሲሆን ይህም ለአፍሪካ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በተለይ ሥር የሰደደ የሐዋርያዊ አገልግሎት አጣዳፊ ክስተት እንደሆነ ተመልክቷል።

አሻሚነቱን የሚያሳየው መጽሐፍ ቅዱሳዊው ትንተናው በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተቀባይነትን አግኝቶ በአዲስ ኪዳን መገለጥ ኢየሱስ የፈጣሪን የመጀመሪያ እቅድ በማስታወስ የጋብቻን አንድነት እና አለመፍረስ በግልጽ ያረጋግጣል። የቤተ ክርስቲያኒንን ትምህርት አጥብቆ የሚደግመው ሠነዱ የክርስቲያን ጋብቻ በሥነ-መለኮት መሠረት አንድ እንጂ ባሕላዊ ጫና እንዳልሆነ ያስረዳል።

ሐዋርያዊ አገልግሎትን መሠረት በማድረግ የአፍሪካ እና የማዳጋስካር ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ምክር ቤት ለ “ከአንድ በላይ ጋብቻ” እውቅናን አይሰጥም። በመሆኑም ንዑሰ ክርስቲያን ለአንድ ጋብቻ ያላቸውን ቁርጠኝነት በነፃነት ከመግለጻቸው በፊት ምስጢረ ጥምቀት እንዳይቀበሉ ይመክራል። ይህ የማግለል ወይም የመገለል ጉዳይ ሳይሆን ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረት በትዕግስት እና በአክብሮት የሚሰጥ አገልግሎት ነው።

የሴቶች ክብር በዚህ የሐዋርያዊ አቀራረብ ዋና ማዕከል ሲሆን፥ የኢየሱስ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በባህል ውስጥ የተዋበ የወንጌል አገልግሎት ሞዴል ሆና ቀርባለች። መደምደሚያው የሚጀምረው የቤተ ክርስቲያንን በሮች ለመክፈት የሚያስችል ቅርብ የሐዋርያዊ እንክብካቤ ሲሆን፥ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ለታማኝ ፍቅር እና ለቃል ኪዳኑ የተጠራ ስለመሆኑ እውቅናን ይሰጣል።

የ “ከአንድ በላይ ጋብቻ” ሪፖርት መደምደሚያ

ሪፖርቱ ዛሬ በአፍሪካ ማህበረሰቦች ውስጥ ከአንድ በላይ ማግባት እውን ሆኖ የቀጠለ ቢሆንም ነገር ግን የእርሱ መኖር እና መስፋፋት እንደ እያንዳንዱ መንግሥት ፖሊሲዎች፣ እንደ ዋና ሃይማኖት እና እንደ የባሕል ተጽዕኖ ይለያያል።

በዚህ አውድ ስብከተ ወንጌል ከአንድ በላይ ጋብቻን የማክበር ሃሳብ አንዳንድ ጊዜ በባህላዊ ምክንያቶች የተደገፈ በመሆኑ የተወሰነ ተቃውሞ ያጋጥመዋል።

በወንጌል ስርጭት ታሪክ ውስጥ ከአንድ በላይ ጋብቻን የመሠረቱ ሰዎች የተለያዩ ሞዴሎችን የያዙ፣ አንዳንድ ጊዜ ከአንድ ሀገረ ስብከት ወደ ሌላ ሀገረ ስብከት፣ ከአንድ የጳጳስ ጉባኤ ወደ ሌላ፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ቦታ ውስጥ የተለያዩ ሞዴሎችን በያዙ የክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ እንዲገቡ ለማድረግ ሙከራዎች እንደ ነበሩ ይገነዘባሉ።

“ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ የሲኖዶሳዊነት ባህሪዋን፣ የሁሉም ሰው ኅብረት እና ተሳትፎ ውስጥ ለመኖር በምትፈልግበት በዚህ ወቅት በአፍሪካ ውስጥ ያለች ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ሞዴሎች ማጋራት እና በአስተምህሮ እና በሐዋርያዊ የአገልግሎት መንገድ መገምገም ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ ከክርስቶስ እና ከወንጌሉ ጋር የመገናኘት ዕድልን ለማቅረብ ሌሎች መንገዶችን ማቅረብ አስቸኳይ ይሆናል።”

በአፍሪካ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ በላይ ጋብቻን የመሠረቱ ጥንዶችን በማጀብ የምትወስደው እርምጃ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት እንዲኖራቸው የሚጠይቁ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን ስለ ጋብቻ እና ስለ ክርስቲያን ቤተሰብ ላላት ግንዛቤ ታማኝ ለመሆን የሚደረግ ሙከራ ይመስላል።

“ግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን የመቀበል እና አብሮ የመጓዝ አስፈላጊነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ መጥቷል” የአፍሪካ ብጹዓን ጳጳሳት “በቤተ ክርስቲያን እና በኅብረተሰብ ውስጥ ስለ ቤተሰብ ጥሪ እና ተልዕኮ በወንጌል የተገለጠ እውነት ለቀረበላቸው ጥሪ የበለጠ ግልጽ ምላሽ እንዲሰጥ” በማለት አፅንዖት ሰጥተዋል።

“ስለዚህ የጋብቻን ቅዱስ ምስጢር እንደ ማኅበራዊ ስምምነት ሳይሆን እንደ የትዳር ጓደኞች ቅድስና እና የመዳን ስጦታ መሆኑን ለማወቅ የሚረዳ ቅርብ እና ትኩረት ያለው የሐዋርያዊ አገልግሎት አቀራረብ አጣዳፊነት መሠረት እንደ ጥሪ፣ ተልዕኮ እና ስጦታ መቀበል ይገባል” በማለት ደምድመዋል።

 

 

25 Mar 2026, 16:40