ቅድስት መንበር፣ ሴቶች ፍትህ እንዳያገኙ የሚከለክሏቸውን እንቅፋቶች ይፍቱ ዘንድ ጥሪ አቀረበች!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
"ለሴቶችና ልጃገረዶች የፍትህ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ከመደበኛ የሕግ ጥበቃዎች የበለጠ ያስፈልጋል" ሲል መግለጫው አጉልቶ አሳይቷል። "እንዲሁም ለአደጋ የሚያጋልጧቸውን፣ ፍትህን ከመፈለግ የሚከለክሉ እና በመጨረሻም እግዚአብሔር የሰጣቸውን ሰብዓዊ ክብር የሚያዳክሙ ዋና ዋና ምክንያቶችን መፍታትን ያካትታል" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።
"የፍትህ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ፍትሃዊ ማህበረሰብን ለማግኘት ወሳኝ ነው" እና "ድህነትን ማስወገድ፣ አድልዎና ዓመፅን መዋጋት፣ ተቋማትን ማጠናከር እና ትምህርትን የሚያካትት ሁሉን አቀፍ አቀራረብን ይጠይቃል" ሲል መግለጫው ገልጿል።
ዓመፅንና አድልዎን መዋጋት
የቅድስት መንበር ቋሚ ተልዕኮ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባቀረበው መግለጫ "ሴቶችና ልጃገረዶች የሚያጋጥሟቸውን እንቅፋቶች እንደ ዓመፅና መድልዎ" እውቅና መስጠትና ድርጊቱን ማውገዝ አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥቶ የገለጸ ሲሆን ጥቃትን ለመከላከልና ጥሰቶችን ነፃ ለማውጣት"ውጤታማ የተጠያቂነት ሥርዓቶች እና የኃላፊነት ባህል" እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርቧል።
መግለጫው “እነዚህን ጉዳዮች መፍታት አለመቻል ሴቶችንና ልጃገረዶችን እንደገና ለብዝበዛ አደጋ ላይ እንደሚጥላቸው” በተለይም በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ረገድ አደረገኛ ሁኔታዎችን ሊፈጥር ይችላል ያሉ ሲሆን ሴቶችና ልጃገረዶች አብዛኛዎቹ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች እንደሆኑ እና ብዙውን ጊዜ ለዝሙት አዳሪነት ወይም ለጋብቻ፣ በልጅነታቸው የለጅ ልጅ እንዲያዩ ወይም ለወንጀል እንደሚበዘብዙ አስረድተዋል።
መግለጫው በተጨማሪም በወንጀል የተከሰሱ ሴቶችንና ልጃገረዶችን መብቶች ማክበር አስፈላጊ መሆኑን አጥብቆ አሳስቧል፤ ለምሳሌ “ፍትሃዊ የፍርድ ቤት ዋስትናዎች፣ በቂ የሕግ ውክልና፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ንጽህና ያለው፣ ለአንድ ጾታ ብቻ የተሰሩ ተቋማት” እና ለእናቶችና ለነፍሰጡር ሴቶች በቂ እንክብካቤ መስጠት እንደ ሆነም መግለጫው አክሎ ገልጿል።
ድህነትን መፍታት
የቅድስት መንበር ቋሚ ተልዕኮ ለተባበሩት መንግስታት እንደገለጸው ድህነትን የሴቶችን የፍትህ ተደራሽነት የሚነካ ሌላ እንቅፋት እንደሆነ አጥብቆ ተናግሯል። ድሆች ሴቶችና ልጃገረዶች ብዙውን ጊዜ የሕግ ውክልና ለማግኘት የሚያስችል ሀብት እንደሌላቸው፣ ጥራት ያለው ትምህርት እንዳላገኙ ወይም መብቶቻቸውን እንዳላወቁ እና የፍትህ ስርዓቱን እንዴት እንደሚያስተዳድሩ እንደማያውቁ አስረድተዋል።
በተጨማሪም፣ በገጠር አካባቢዎች፣ ብዙ ሴቶችና ልጃገረዶች አስተማማኝ የትራንስፖርት ወይም የመገናኛ አውታረ መረቦች ባለመኖራቸው ተጎጂ እንደሆኑ አስረድተዋል።
በተጨማሪም “እኩል የፍትህ ተደራሽነት ሴቶች ልጆች ከወንዶች ጋር ተመሳሳይ ሀብቶችን እና እድሎችን እንዲያገኙ እንዲሁም ቤተሰቦች ለሁሉም ጤናማ እና ሰላማዊ አካባቢ እንዲሆኑ ይጠይቃል” ሲል መግለጫው አስታውቋል።