የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን   (© Archdiocese of Malta)

ካርዲናል ፓሮሊን የቅድስት መንበር እና የማልታ ግንኙነት 60ኛ ዓመት ክብረ በዓልን አክብረዋል

የቅድስት መንበር እና የማልታ 60ኛ ዓመት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ሲያከብሩ፣ የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ፒትሮ ፓሮሊን በማልታ በቫሌታ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ግንኙነቱን በውይይት እና በመገናኘት “በግልጽነት ላይ ተመስርቶ ኖሯል” በማለት የሁለቱንም አገራት ግንኙነት አድንቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፒትሮ ፓሮሊን ከጥር 23 እስከ ጥር 24/2018 ዓ.ም፣ ቅዳሜና እሁድ ከቅድስት መንበር ጋር መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የተጀመረበትን 60ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ለማክበር ወደ ማልታ ሪፐብሊክ ማቅናታቸው ይታወሳል።

እሁድ ዕለት ካርዲናሉ በቫሌታ በሚገኘው የቅዱስ ዮሐንስ ካቴድራል መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ይተገለጸ ሲሆን ይህ ክብረ በዓል የተካሄደው ቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ጳውሎስ በማልታ የመርከብ መሰበር አደጋ የተከሰተበ ቀን በሚታወስበት በዓል ላይ እንደ ነበረም ተገልጿል።

በስብከታቸው ካርዲናል ቲዬትሮ ፓሮሊን እንደ ተናገሩት የአሕዛብ ሐዋርያ የሆነው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮም ባደረገው ጉዞ ያጋጠመውን ነገር ተመልክተዋል።

ቅዱስ ጳውሎስን “ያለ ፈቅዱ በቁጥጥር ሥር በኃይል የዋል፣ በማዕበል የተወዛወዘ፣ በሌሎች ውሳኔ የሚገዛ እስረኛ” ሲሉ ገልጸውታል፣ ነገር ግን “በማዕበሉ መካከል” ነገሮችን በግልጽ ማየት፣ በሀላፊነት መናገር እና ሠራተኞችን እና ተሳፋሪዎችን ማበረታታት፣ ተስፋን መዝራት ችሏል" በማለት በስብከታቸው የተናገሩት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን “አትፍሩ፣ እግዚአብሔር ታማኝ ስለሆነ ሕይወት እንደማይጠፋ የተስፋ ስብከት አውጇል” ሲሉ ካርዲናሉ ተናግረዋል።

ካርዲናል ፓሮሊን “የቅዱስ ጳውሎስ ሥልጣን እዚህ ላይ ከማዕረግ፣ ከኃይል ወይም ከጥንካሬ የመነጨ አይደለም” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፣ ነገር ግን “ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ግንኙነት እና ለሌሎች ካለው የኃላፊነት ስሜት የመነጨ ነው፣ ምንም እንኳን ተጋላጭ እስረኛ ቢሆንም፣ መሪ እና የጥንካሬ ምንጭ ሆነ” ሲሉ ካርዲናሉ ተናግረዋል።

ለእኛ በዛሬው ዘመን ላለነው ሰዎች የሚሰጠው ትምህርት “እውነተኛ ሥልጣን - መንፈሳዊ፣ ሐዋርያዊ ወይም ዲፕሎማሲያዊ ቢሆንም እንኳን - ከቁጥጥር የተወለደ ሳይሆን ከእምነት እና ከመታመን የተወለደ ነው፤ በፈተና ጊዜያት ታማኝ ሆኖ በመቆየት” ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ካርዲናል ፓሮሊን የቅዱስ ሉቃስን ወንጌል በማጉላት የመርከብ አደጋ ለደረሰባቸው ሰዎች “ያልተለመደ ደግነት” ያሳዩትን የማልታ ነዋሪዎች አጉልተው ገልጸዋል። “በማልታ ምድር ላይ የመጀመሪያው የክርስትና ድርጊት እንግዳ ተቀባይነት ነው” ብለዋል።

ከመጀመሪያው ጀምሮ የማልታ የክርስትና ታሪክ “ሌላውን ለመቀበል፣ አደጋን ወደ መገናኘት እና ፍርሃትን ወደ ግንኙነት ለመቀየር” ባለው አቅም ተለይቷል፣ ስለዚህም “ቅዱስ ጳውሎስ እንደ እንግዳ ይመጣል፣ ነገር ግን በእምነት እንደ አባት ይሄዳል” ብለዋል።

ካርዲናል ፓሮሊን ወደ አሁኑ ጊዜ ሲመለሱ “ቅዱስ ጳውሎስን ወደ ማልታ ያመጣው ባህር ሕዝቦችና አገራት  ዛሬም ድረስ ከሚጓዙበት የታሪክ ባህር የተለየ አይደለም” ብለዋል። ዓለም “በጦርነት፣ በስደት፣ በማህበራዊ መከፋፈል እና የወደፊቱን በመፍራት” የተሞላች ናት ብለዋል፣ ይህም “ኃላፊነታችንን እንድንተው ወይም በኃይል ደህንነት እንድንፈልግ” ሊፈትነን ይችላል፥ ቅዱስ ጳውሎስ ካርዲናሉ እንዳሉት፣ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ በትኩረት በመከታተል፣ በማዳመጥ እና በመናገር ሌላ መንገድ ያሳያል፣ ሕይወታቸው አስፈላጊ መሆኑን እና በእግዚአብሔር የዝግጅት እጅ ውስጥ መሆናቸውን ያስታውሳል" ሲሉ ተናግረዋል።

“ይህ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ውስጥ የቤተክርስቲያኗ ጥሪም ነው” ሲሉ ካርዲናል ፓሮሊን ተናግረዋል። “ቅድስት መንበር እያንዳንዱን ማዕበል እንደሚረጋጋ አትናገርም። ነገር ግን ማንም መጥፋት እንደሌለበት፣ ሰላም እንደሚቻል እና ውይይት ፈጽሞ ከንቱ እንዳልሆነ ያላትን እምነት በትህትና እና በጽናት ለማቆየት ትፈልጋለች” ሲሉ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ተናግረዋል።

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት የካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በመቀጠልም ከስልሳ ዓመታት በፊት የተጀመረው የማልታ እና የቅድስት መንበር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት “ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት የቆየ ትስስር” ውጤት መሆኑን አስታውሰዋል።

ከጊዜ በኋላ፣ ቤተክርስቲያን እና መንግሥት፣ አንዱ የሌላውን ነፃነት ሲያከብር፣ ለጋራ ጥቅም መተባበር እንደሚችሉ አሳይተዋል - “በትሕትና፣ በግልፅነት እና በጽናት” ከተከናወነ ግንኙነቱ ዘላቂ ሊሆን ይችላል ማለታቸው ተገልጿል።

የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልዑክ “በትኩረት እና በማዳመጥ መገኘት”፣ ከአካባቢው ቤተክርስቲያን ጋር በቅርበት የተጣጣመ እና የመንግስት ተቋማትን የሚያከብር መሆኑን" ጠቁመዋል።

ማልታ ወደ አውሮፓ ውህደት ከተመለሰች በኋላ በነበረው ጊዜ፣ ቅድስት መንበር ውይይትን ለማስቀጠል፣ አለመግባባቶችን ለማስወገድ እና በምክንያታዊነት፣ በጋራ መከባበር እና በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረቱ መፍትሄዎችን ለማስተዋወቅ እንደረዳ ጠቁመዋል።

በትምህርት፣ በጋብቻ፣ በቤተክርስቲያን ንብረት እና በመመስረት ላይ ለዓመታት የተደረጉ ስምምነቶች “እንደ ህጋዊ መሳሪያዎች” ሳይሆን “በትዕግስት የተገነባ እምነት ምልክቶች” እንደሆኑ መታየት አለባቸው ያሉት ካርዲናሉ እነዚህ ስምምነቶች ማህበረሰቡን “ከኃላፊነቶች ጋር ሳይጋጭ” ለማገልገል ያላቸውን የጋራ ፍላጎት ይገልጻሉ፤ ይህም ግጭት ወይም የሃይማኖት ጉዳይ ሳይሆን የንግግርና ተጨባጭ ግንኙነት ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ካርዲናል ፓሮሊን ከዚህ ቀደም የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪዎች ወደ ማልታ ያደረጉትን ጉብኝት “የጸጋ ጊዜያት” ሲሉ አስታውሰዋል፤ ተቋማዊ ትስስር በፍቅር፣ በጸሎት እና በጋራ እምነት የበራበት ወቅት ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

“ማልታ የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪዎችን እንደተቀበለች ሁሉ ቅዱስ ጳውሎስን በፍርሃት ሳይሆን በታላቅ ጉጉት እና በልግስና ተቀብላለች” ብለዋል። ካርዲናል ፓሮሊን የእያንዳንዱን የሰው ልጅ አስፈላጊነት በመጠበቅ እና ይህ ሰብዓዊ መብት ፈጽሞ መተው የለበትም ካሉ በኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

02 Feb 2026, 11:26