ፈልግ

የር.ሊ.ጳ ሊዮ ምስሎች እና መልዕክቶች በገና ሰሞን የሮም ከተማ ማድመቃቸው ተነገረ የር.ሊ.ጳ ሊዮ ምስሎች እና መልዕክቶች በገና ሰሞን የሮም ከተማ ማድመቃቸው ተነገረ 

የር.ሊ.ጳ ሊዮ ምስሎች እና መልዕክቶች በገና ሰሞን የሮም ከተማ ማድመቃቸው ተነገረ

የቅድስት መንበር የኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ‘ሰልፊስትሪት’ ከተባለው ተቋም ጋር በመተባበር በቫቲካን ዙሪያ በተለያዩ ህንፃዎች ላይ የተገጠሙ ትልልቅ ስክሪኖች ላይ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ምስሎች እና መልዕክቶች እንዲታዩ በማድረግ ከተማዋን ያደመቀ ሲሆን፥ እነዚህ ምስሎች እና መልዕክቶች እስከ ታኅሣሥ 22 ቀን መቆየታቸው ተነግሯል።

አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ከዚህን በፊት በተለመደው መሰረት በሮም ዙሪያ የሚገኙ ህንፃዎች ላይ የሚገጠሙ የማስታወቂያ ስክሪኖች በጉዞ ጥቅሎች እና የበዓል ጣፋጭ ምግቦች ደማቅ ቀለም ያሸበርቁ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፥ ዘንድሮ ግን በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ምስሎች ተተክተው ልዩ ድባብ መፍጠራቸው ተነግሯል።

እነዚህ ምስሎች ለበርካታ ቀናት ዘላለማዊ ከተማ ተብላ በምትታወቀው ሮም ውስጥ ፒያሳ ሪሶርጊሜንቶ እና ቪያ ኦታቪያኖ ተብሎ በሚታወቁ ታዋቂ ሰፈሮችን ጨምሮ በቫቲካን ሙዚየም ፊት ለፊት ባሉ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች አከባቢ በሚገኙ በሚገኙ ህንፃዎች ላይ በተገጠሙ ትልልቅ ስክሪኖች ላይ በብርሃን ደምቀው የታዩ ሲሆን፥ ስክሪኖቹ ላይ ሲታዩ የነበሩት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ምስሎች እና ብርሃነ ልደቱን አስመልክተው ካደረጉት የተለያዩ ንግግሮቻቸው የተወሰዱ ወሳኝ እና አጫጭር መልዕክቶች እንደሆኑ ተገልጿል።

የተለያዩ መንገደኞች፣ ምዕመናን እና መንፈሳዊ ነጋዲያን ብዙውን ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ምስሎች ጎን የሚታዩትን መልዕክቶች ለማንበብ ለተወሰኑ ጊዜያቶች የሚቆሙ ሲሆን፥ እስከ ታህሳስ 22 ድረስ የቆየው ይህ የገና ዘመቻ ተነሳሽነት አካል የሆኑት ምስሎች እና መልዕክቶች በማህበራዊ ሚዲያም በስፋት እንደተሰራጩ ተነግሯል።

ዝግጅቱን አስመልክቶ የወጣው መግለጫ ‘በገና ሰሞን የቅዱስ አባታችን መልዕክት በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች መገኘት የመንፈሳዊ ቅርበት ምልክት እንዲሁም የሰላም፣ የተስፋ እና የወንድማማችነት እሴቶችን ለማስታወስ እንደሚያገለግል’ ገልጿል።

 

02 Jan 2026, 15:49