ፈልግ

ሦስተኛውን እና የመጨረሻው የአውሮፓውያኑ የብርሃነ ልደቱ ዝግጅት አስተንትኖ ሦስተኛውን እና የመጨረሻው የአውሮፓውያኑ የብርሃነ ልደቱ ዝግጅት አስተንትኖ   (@VATICAN MEDIA)

አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ፥ ቤተ ክርስቲያን የእርስ በርስ ግንኙነትን ልታበረታታ ይገባል” ሲሉ አሳሰቡ

በቅድስት መንበር ለጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቶች ሠራተኞች ስብከት የሚያቀርቡት አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ፥ ሦስተኛውን እና የመጨረሻውን የአውሮፓውያኑ የገና ሰሞን አስተንትኖ ስብከታቸውን አቅርበዋል። አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ፥ “መዳን ያለ ቅድመ ሁኔታ ለሁሉ የተሰጠ ተስፋ ነው” በሚል ጭብጥ ያዘጋጁትን ሦስተኛውን እና የመጨረሻውን የብርሃነ ልደቱ ዝግጅት ስብከታቸውን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በተገኙበት በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ዓርብ ታኅሳስ 10/2018 ዓ. ም. ጠዋት አቅርበዋል። አባ ሮቤርቶ ስብከታቸውን፥ ለማያውቁት ሰው ራሳቸውን ክፍት ለማድረግ በደፈሩት ሰብዓ-ሰገሎች ላይ ትኩረት አድርገዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት በብርሃን በመቀበል ለማስፋት እና ለዓለም ማቅረብ የብርሃነ ልደቱ እና የኢዮቤልዩ በዓል የሚጠይቀን ተልዕኮ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል” ያሉት አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ፥ ይህንን ተልዕኮ በማስመልከት ባቀረቡት የመጨረሻው የብርሃነ ልደቱ ዝግጅት ስብከታቸው፥ በመዳን ሁለንተናዊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል።

የሚገለጠው ብርሃን

የካፑቺን ማኅበር ካኅን አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ፥ የመዳን ሁለንተናዊ መገለጥን መሠረት በማድረግ፥ የሰው ልጅ ውስብስብነት ተሞክሮን ማብራራት እና መምራት የሚችል፣ ጥያቄዎችን፣ ምኞቶችን እና ፍላጎቶችን የሚያገናኝ እና ወደ ሙሉ ትርጉማቸው የሚመራ እውነተኛ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን አስገንዝበዋል።

“ዓለም ይህንን ብርሃን የተቀበለው የሰው ልጅ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለወደደ አይደለም” ያሉት አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ፥ “አስፈላጊ እና የሚያምር በመሆኑ፣ ነገር ግን ይህን ብርሃን ለመቀበል ማስመሰልን ማስወገድ፣ ቅራኔዎችን ማጋለጥ እና ማየት የማንፈልገውን ለማየት ፈቃደኞች መሆንን ይጠይቃል” ሲሉ አስረድተዋል።

“ኢየሱስ ክርስቶስ ክፉ የሚያደርጉትን መልካም ከሚያደርጉት ጋር አያነጻጽርም፤ ነገር ግን እውነት የሆነውን ከሚያደርጉት ጋር ያነጻጽራል” ብለው፥ ይህ ማለት ሥጋ መልበስን መቀበል፣ አስቀድሞ ጥሩ ወይም ፍጹም መሆን ሳይሆን ነገር ግን በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ አስፈላጊው እውነትን ተግባራዊ ማድረግ መጀመር እንደሆነ አስረድተው፥ ራሳችንን ሳንደብቅ ማን መሆናችን እንዲታይ ስናደርግ እንደሆነ እና እግዚአብሔር ይበልጥ የሚፈልገው ውጫዊ በጎነትን ሳይሆን እውነተኛነታችንን እንደሆነ አስረድተዋል።

ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ብርሃን የምትኖር ማኅበረሰብ ናት

ለቤተ ክርስቲያን ይህ ማለት የእውነት ጉዞ መጀመር ማለት እንደሆነ፥ ይህም የሥነ ምግባር ንጽሕና ወይም ፍጹም ወጥነት ማለት ሳይሆን ነገር ግን ራስን በቅንነት በማቅረብ ድክመትን መቀበል ማለት እንደሆነ ተናግረው፥ ዓለም እንከን የለሽ ወይም ምን ማድረግ እንዳለበት የሚነግር ተቋም እንደማይጠብቅ ተናግረው፥ ፍጹም ጉድለቶች እና ተቃርኖዎች ቢኖሩም ዓለም በክርስቶስ ብርሃን ውስጥ በእውነት የሚኖር እና እራሱን ለማጋለጥ ከማይፈራ ማኅበረሰብን ጋር መገናኘት እንደሚፈልግ አስረድተዋል።

“ሰብዓ ሰገል የኢየሱስን መንገድ በመከተል እውነተኛ የመሆንን ልዩ መንገድ አሳይተውናል” ያሉት አባ ሮቤርቶ፥ “ከሩቅ አገር በመምጣት የልደቱን ብርሃን ለመቀበል በተወሰነ ርቀት ላይ መሆን አስፈላጊ መሆኑን በማሳየት፥ ይህም ነገሮችን በተሻለ ሁኔታ ለማየት እና ጥልቅ እይታ እንዲኖረን እና የመገረም ችሎታን እንድናገኝ ያስችለናል” ብለዋል።

“እውነታን በቅርበት መመልከት ሊተነበዩ የሚችሉ ፍርዶች እና ከመጠን በላይ የተጠናከሩ ትርጓሜዎች እስረኞች ሊያደርገን ይችላል” ብለው፥ ይህ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ በቋሚነት የሚኖሩ እና ኃላፊነቶችን ወደሚሸከሙት ሊደርስ ይችላል” ሲሉ ተናግረው፥ “በየዕለቱ ከሚገለጹ ሚናዎች፣ መዋቅሮች፣ ውሳኔዎች እና አጣዳፊነቶች ጋር መተዋወቅ ከጊዜ በኋላ አመለካከታችንን ሊያጠበብ እንደሚችል እና እግዚአብሔር በዓለም ውስጥ ራሱን የሚያቀርብባቸውን አዳዲስ ምልክቶችን አለማወቅ አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል አስረድተዋል።

የእግዚአብሔር ያልተጠበቁ መንገዶች

በብርሃነ ልደቱ ቀን ወደ ዓለም የመጣውን ብርሃን የምናከብር ከሆነ በበዓለ ጥምቀቱ ደግሞ ይህ ብርሃን እንዲታወቅ ያስችላል” ብለው፥ በጨለማ እና በፍለጋ ውስጥ ለሚገኙት ራሱን በመግለጥ ወደ ፊት ለመጓዝ ፈቃደኛ ለሆኑት እራሱን የሚያቀርብ መሆኑን አስረድተዋል።

“ይህን ብርሃን ሁሉም ሰው በተመሳሳይ መንገድ እና በተመሳሳይ ጊዜ አይገነዘበውም” ያሉት አባ ሮቤርቶ ምክንያቱም የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን ከራሳቸው ወጥተው እርሱን ለመፈለግ እና ለመቀበል ፈቃደኞች ለሚሆኑት ሰዎች የሚገለጥ መሆኑን ተናግረው፥ ይህም ለቤተ ክርስቲያን ጉዞ እውነት እንደሆነ በማስረዳት፥ እውነት የሆነው ሁሉ ወዲያው ግልጽ ሆኖ እንደማይታይ፥ እንዲሁም ወንጌላዊ ሁሉ ወዲያው ውጤታማ እንደማይሆን፥ አንዳንድ ጊዜ እውነት ሙሉ በሙሉ ግልጽ ከመሆኑ በፊት እንዲከተሉት የሚጠይቅ መሆኑን አስረድተዋል።

“ይህ በእያንዳንዱ አማኝ ሕይወት ውስጥ እውነት ነው” ያሉት አባ ሮቤርቶ፥ “በተለይም መንጋውን የመጠበቅ፣ የመምራት እና የማሰላሰል ኃላፊነት ባለባቸው ሰዎች ዘንድ እውነት ነው” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል። “ሕያው እና ዘላቂ ሆኖ የመቆየት ፍላጎት ከሌለ ከፍተኛ የአገልግሎት ዓይነቶችም ሳይቀሩ ተደጋጋሚ፣ ራስን የማመዛዘን እና የመደነቅ ላለመቻል አደጋ ይጋረጣሉ” ብለዋል።

ሰብዓ ሰገልን የመራው ኮከብ’’ “እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ ራሱን እያሳየ የሚቀጥልበት የድብቅ ጥሪ ምልክት ነው” ብለው፥ የእስራኤላውያንን ታሪክ የማያውቁ ቢሆኑም ነገር ግን ሰማያትን የሚያነቡ ጠቢባን፥ እግዚአብሔር ባልተጠበቁ መንገዶች እና ልምዶች ከእውነታው ጋር የሚነሱ ጥያቄዎች መጠበቅን ያስታውሱናል” ሲሉ አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ ተናግረዋል።

የኢየሱስ ልደት እውነተኛ ብርሃን

አባ ሮቤርቶ በስብከታቸው “እንድናስብበት የሚጋብዘን የመጨረሻው ገጽታ፥ እግዚአብሔር በውስጣችን ለመኖር ከመረጠ እያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት በራሱ ብርሃን፣ ጥሪ እና ሊጠፋ የማይችል እሴት ነው” ብለው፥ ይህም ወደ ዓለም የመጣነው ለመኖር ወይም ጊዜን በተቻለ መጠን በተሻለ መንገድ ለማሳለፍ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ልጆች ሕይወት ለማግኘት ብለን እንድንደመድም ሊያደርገን ይገባል” ብለዋል። የቤተ ክርስቲያን ተግባር የኢየሱስ ክርስቶስን ብርሃን ወደ ዓለም ማምጣት እንደሆነ አስረድተው፥ ይህም በግዴታ ሳይሆን ለማንኛውም ሰው በስጦታነት ለማቅረብ የሚያስችል ነው” ብለዋል።

አባ ሮቤርቶ “ከዚህ አንፃር ተልዕኮ ማለት የእርስ በርስ ግንኙነትን ማስገደድ ሳይሆን እንዲቻል ማድረግ ነው” ብለው፥ ቤተ ክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስን ብርሃን ለሁሉም ሰው የምታቀርብ እና ወደ ብርሃን የምትጋብዝ እንጂ የበላይ ሆና የምትቆጣጠር መሆን እንደሌለባት፥ በዚህ ምክንያት ሁሉም ሰው ክርስቶስን የሚያውቅበት እና በፊቱ የሕይወቱን ትርጉም እንደገና የሚያገኝበት ቦታ ትሆናለች” ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል።

“ይህ አመለካከት የሚስዮናዊነት ልማዶቻችንን እንደገና እንድንመለከት ያስገድደናል” ብለው፥ ስብከተ ወንጌል ማለት የጎደለውን ነገር ማምጣት፣ ባዶነትን መሙላት እና ስህተትን ማስተካከል ማለት እንደሆነ ብዙ ጊዜ ብናስብም፥ ነገር ግን ብርሃነ ጥምቀቱ ሰዎች በውስጣቸው ያለውን ብርሃን እንዲያቁ፣ ክብራቸውን እና አስቀድመው የያዙትን ስጦታዎች እንዲያውቁ መርዳትን የሚጠቁም መሆኑን አስረድተዋል።

“ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ካቶሊካዊነት መልካምነት እና እውነት በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ መኖራቸውን እና ሙሉ ትርጉማቸውን እንዲያውቅ፥ በእምነት ለሁሉም ሰው ለማቅረብ ክርስቶስን ማስቀድም እና የኢየሱስ ክርስቶስ ልደትም እያንዳንዱ ሰው የራሱን እውነት፣ የራሱን ጥሪ እና እግዚአብሔርን መምሰልን ማወቅ የሚችል በመሆኑ እውነተኛ ብርሃን ለእያንዳንዱ ሰው ሊበራለት ይገባል” ብለዋል።

 

20 Dec 2025, 16:23