ፈልግ

ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የባምቢኖ ገሱ የሕፃናት ሆስፒታልን በጎበኙበት ወቅት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የባምቢኖ ገሱ የሕፃናት ሆስፒታልን በጎበኙበት ወቅት   (copyright Ospedale Pediatrico Bambino Gesù)

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ‘የታመሙ ህፃናትን ተቀብለን በተንከባከብን ቁጥር ክርስቶስ ይወለዳል’ ማለታቸው ተነገረ

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ማክሰኞ፣ ታኅሣስ 14 ባምቢኖ ገሱ የህፃናት ሆስፒታልን የጎበኙ ሲሆን፥ ብፁዕነታቸው በጉብኝቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር ለታመሙ ህፃናት እና ቤተሰቦቻቸው ትኩረት እና እንክብካቤ በሰጠን ቁጥር ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለን ህብረት እንደሚጠነክር ጠቁመዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ማክሰኞ ታኅሣሥ 14 የቅድስት መንበር የሕጻናት ሆስፒታልን በጎበኙበት ወቅት ለሆስፒታሉ ሠራተኞች፣ የአስተዳደር ዳይሬክተሮች እና ህሙማን ባደረጉት ንግግር “ይህ ሆስፒታል የገና ሆስፒታል የተባለው ‘ባምቢኖ ገሱ’ (“ሕፃኑ ኢየሱስ”) ተብሎ ስለሚጠራ ብቻ ሳይሆን፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወለደው ትንንሾችን ተቀብለን በተንከባከብን ጊዜ ሁሉ ስለሆነ ነው” በማለት ተናግረዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በሆስፒታሉ የጸሎት ቤት ውስጥ በነበረው የማሰላሰያ ጊዜ በስፍራው ለነበሩት ሰዎች “የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮን ሰላምታ እና መልካም ምኞት ይዤላችሁ መጥቻለሁ” በማለት የተናገሩ ሲሆን፥ በመርሃ ግብሩም ላይ ዶክተሮች፣ ነርሶች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ ታካሚዎች እና ቤተሰቦች፣ የሆስፒታሉ እና የባምቢኖ ገሱ ፋውንዴሽን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና የሆስፒታሉ ገዳማዊያት ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን፥ በአከባቢው ልማድ መሰረት ለመላው ማህበረሰብ የገና ሰላምታ አቅርበዋል።

ካርዲናሉ ከቫቲካን በቅርብ ርቀት በሚገኘው የባምቢኖ ገሱ ሆስፒታል ሲደርሱ የሆስፒታሉ ፕሬዝዳንት ቲዚያኖ ኦኔስቲ እና የሆስፒታሉ የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን፥ በመቀጠልም በሆስፒታሉ የህክምና ክፍሎች በመዞር ለታካሚዎች እና ቤተሰቦቻቸው ሰላምታ አቅርበዋል።

በጣም ጥሩ እንክብካቤ እና ሰብዓዊ እይታ
ካርዲናል ፓሮሊን በጸሎት ቤቱ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ በጉብኝታቸው ወቅት ከታማሚ ወላጆች ጋር ባደረጉት ውይይት የሰሙትን ታሪክ ያካፈሉ ሲሆን፥ አንድ የታካሚ ወላጅ “ግማሽ ፈውስ የሚገኘው በሕክምና ነው፥ ግማሹ ደግሞ ከቤተሰብ በሚያገኙት ቅርበት እና ፍቅር ነው” ብለው እንደነገሯቸው አስታውሰዋል።

ካርዲናሉ ይህ የባምቢኖ ገሱ ምኞት እንደሆነ ጠቁመው፥ ‘በእንክብካቤ ውስጥ የላቀ ብቃት ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊ አመለካከትም ጭምር አለ’ ብለዋል።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊው “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልባችን መወለዱ እንዴት ሊሆን ይችላል?” በማለት ራሱን የጠየቀውን ጣሊያናዊ ባለቅኔ ጆቫኒ ፓፒኒን አስታውሰው፥ “ይህ የማይቻል አይደለም” ብለዋል።

ገጣሚው “ለአንድ ሰው ደስታን ያመጣህ ቀን ወይም የአንድን ሰው ህመም ያቀለልክ መስሎህ የተሰማህ ቀን ደስ ይበልህ፥ ምክንያቱም ጊዜው ደርሷል፥ አዳኛችንም በልባችሁ ውስጥ ተወልዷል፥ ከእንግዲህ ብቻህን አይደለህም” ብሎ የፃፈውን ጽሁፍ በማስታወስ ተናግረዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የባምቢኖ ገሱ ሆስፒታል ተግባርም ገጣሚው ካለው ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ጠቁመው፥ “ለህፃናት እና ለቤተሰቦቻቸው ትኩረት በተሰጠ ቁጥር፣ የዕለት ተዕለት ሥራችሁን ባከናወናችሁ ቁጥር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና ይወለዳል” በማለት አጠቃለዋል።

25 Dec 2025, 14:27