በቫቲካን የምስራቃውያን አብያተ ክርስቲያናትን ጉዳዮች የሚመለከተው ጽ/ቤት አባላት ሹመት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን የምስራቃውያን አብያተ ክርስቲያናትን ጉዳዮች ለሚመለከተው ጽ/ቤት በሕዳር 12/2018 ዓ.ም አዳዲስ አባላትን ሾመዋል፤ እነሱም በቫቲካን የመለኮታዊ እምነት እና የምስጢራት አስጣጥ ሥነ-ሥርዓቶችን የሚመለከተው ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል አርተር ሮሽ፤ የባይዛንታይን (የሰሜን አመሪካ) የፒትስበርግ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ዊሊያም ቻርለስ ስኩርላ፤ እና የአዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) ርዕሰ ኤጳርቅና ረዳት ኤጳርቃ የሆኑት አቡነ ተስፋዬ ታደሰ ገብረስላሴ (የኮምቦኒ ማሕበር አባል) መሆናቸው ተገልጿል።
21 Nov 2025, 14:01