ካርዲናል ፓሮሊን፦ ቅድስት መንበር ለጋዛ የሰላም ዕቅድ ስኬት ሙሉ ተስፋ አላት ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የቅድስት መንበርን ስጋት በመግለጽ በጋዛ በድጋሚ በተቀሰቀሰው ዓመፅ ላይ ቅድስት መንበር ጉዳዩ ቢያሳስባትም ቫቲካን ግን የታቀደው የሰላም ዕቅድ አሁንም ሊሠራ ይችላል በሚል “ተስፋ የተሞላች ናት” ብለዋል።
ይህንን የተናገሩት በእንግሊዘኛው "ቱ ዘ ቸርች ኢን ኒድ" ለተሰኘውና በሥቃይ እና በመከራ ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን በሚረዳው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ድርጅት የተጠናቀረውን የአለም የሃይማኖት ነፃነት ሪፖርት የቅርብ ጊዜ እትም ይፋ ባደረገበት ወቅት ነበር።
ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ከጳጳሳዊ አውጉስቲንያን ተቋም ግቢ ውጭ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በዌስት ባንክ በተለይም በታይቤ መንደር በእስራኤል ሰፋሪዎች አማካይነት በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደርሰው በደል በተጠየቁበት ወቅት ነበር።
“ይህ በእርግጥ በጣም የተወሳሰበ ጉዳይ ነው” ሲሉ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ተናግሯል። አክለውም “ስለ ስደት ማውራት ትንሽ ችግር ያለው ጉዳይ ነው፣ ግን በእርግጠኝነት እነዚህ ልንቀበላቸው የማንችላቸው ሁኔታዎች ናቸው” ብሏል።
በናይጄሪያ ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ጥቃት
ወደ አፍሪካ እና በአንዳንድ የናይጄሪያ ክፍሎች ባሉ ክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለውን የጥላቻና የዓመፅ ድርጊት ስንመለከት ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የአካባቢውን ምንጮች በመጥቀስ ሁኔታው“ሃይማኖታዊ ግጭት ሳይሆን የበለጠ ማኅበራዊ ጉዳይ ነው” ሲሉ አበክረው ገልጸው ነበር።
"በተጨማሪም በናይጄሪያ ውስጥ ያሉ ብዙ ሙስሊሞች ራሳቸው የዚህ ይነት አለመቻቻል ሰለባ መሆናቸውን ልንገነዘብ ይገባናል" ሲሉ ተናግሯል። "እነዚህ አላማቸውን ለማሳካት ምንም ዓይነት ልዩነት የሌላቸው ጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈጽሟቸው ነገሮች ናቸው፣ እንደ ተቃዋሚ በሚያዩት ሰው ላይ ጥቃትን ይፈጽማሉ" ሲሉ ተናግረዋል።
የነጻ ፕሬስን ማስፈራራት
በሃይማኖታዊ ነፃነት ላይ በስፋት በማንፀባረቅ፣ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፣ በቅርቡ በነጻው ፕሬስ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የማስፈራራት ተግባርም በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል።
እሱ ባለፈው ሐሙስ የጣሊያን የምርመራ ፕሮግራም ሪፖርት አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሲግፍሪዶ ራኑቺ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በመጥቀስ ከቤቱ ውጭ ፈንጂ እንዲፈነዳ እንደ ተደረገ ጠቀሰዋል።
ለአቶ ራኑቺ ያላቸውን አጋርነት የገለጹት ካርዲናል ፓሮሊን “የመናገር ነፃነት በሌለበት፣ አለመቻቻል በሌለበት ሁኔታ ውስጥ የመኖር አደጋ እየበዛ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
"ሁሉም ሰው ሃሳቡን በአክብሮት እና በተጨባጭ እንዲገልጽ እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ሰዎች እንደዚህ ዓይነት ማስፈራሪያ ሳይደርስባቸው ሃሳባቸውን በነጻነት እንዲገልጹ እንፈልጋለን" ብሏል።