ፈልግ

የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቫርሰን አግቤኪያን የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቫርሰን አግቤኪያን  

የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፡ ‘ሰላም እና ፍትህን ማስፈን ይቻላል' ማለታቸው ተገለጸ!

‘ሰላም እና ፍትህን ማስፈን ይቻላል' የሚለው አባባል በዚህ ሳምንት የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ባደረጉት የሰብአዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት መጨረሻ ላይ ከቅድስት መንበር ባለስልጣናት ጋር የተደረገ ውይይት አጀንዳ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሯ በሮም ቆይታቸው በጣሊያን እና በቫቲካን ሆስፒታሎች ህክምና የሚያገኙ የፍልስጤም ልጆችን ገብኝተዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዚህ ሳምንት የጠቃላይ ሚኒስትሯ የቫርሰን አግቤኪያን የኢጣሊያ ጉብኝት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ሰኞ እለት ከቫቲካን ዋና ጸኃፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒትሮ ፓሮሊን ጋር ያደረጉት ምክክር እና የቅድስት መንበር እና የፍልስጤም ብሄራዊ ባለስልጣን በተለይም አንገብጋቢ የሆኑ ሰብዓዊ ጉዳዮችን በሚመለከት ያለውን ትብብር ማጠናከር ነው።

ሚኒስትር አግቤኪያን የፍልስጤም ብሄራዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሆኑ በቅድስት መንበር በቫቲካን የፍልስጤም አምባሳደር ኢሳ ካሲሴህ በጋዛ እና በዌስት ባንክ እየደረሰ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ከምስራቅ እየሩሳሌም ጋር ለመቅረፍ የሚደርገውን ጥረት ተቀላቅለዋል።

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በሁኔታው ላይ ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው በመግለጽ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እና ሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን መፍቀድ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት የሰው ልጅን ሽንፈት ያሳያል ማለታቸው ተገልጿል።

የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከጣሊያን አቻቸው አንቶኒዮ ታጃኒ እና ሌሎች የጣሊያን ባለስልጣናት ጋር እና በጣሊያን የፍልስጤም አምባሳደር ሞና አቡ አማራ ጋር በመሆን በሮም ኡምቤርቶ ፕሪሞ ሆስፒታል እና በቫቲካን ባምቢኖ ጄዙ የህፃናት ህክምና መስጫ እና በጂሜሊ ሆስፒታሎች የሚገኙ አንዳንድ ፍልስጤማውያን ታዳጊዎችን ጎብኝተዋል።

ሚኒስተር አግቤኪያን በቫቲካን የነበራቸውን ቆይታ ከማጠናቀቃቸው በፊት ለቫቲካን ረዲዮ/ቫቲካን ዜና እንደተናገሩት ሆስፒታሎችን የምጎበኙበት ዋና ዓላማ “ሕጻናትን እና ቤተሰቦቻቸውን ይበልጥ እንዲቀራረቡ፣ አንድ ሰው ከእኛ ወገን በእርግጥ እንደሚያስፈልጋቸው ለማረጋገጥ ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም አምባሳደር አቡ አማራን በህክምና ላይ ከሚገኙት ህሙማን ጋር በተሻለ መልኩ የመተዋወቅ አጋጣሚ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፣ “የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ወደ ጣሊያን የመጡት በኤምባሲው እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መካከል ከህሙማንና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ ለመሥራት ነው" ብለዋል።

"የተሻለ ቅንጅት እንዲኖር እና የተሻለ ክትትል እንዲደረግ የቅርብ ትስስር ለመፍጠር ተስማምተናል" ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ አክለው ገልጸዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ አግቤኪያን በመቀጠል ጣሊያናዊያን አሁን ላለው ቀውስ እና ድንገተኛ አደጋ “በሰብአዊ ርዳታ ፣ በምግብ ዕርዳታ እና በሽተኞቹን ወደዚህ በማምጣት” ምላሽ ሰጥተዋል ብለዋል ።

በተለያዩ ደረጃዎች የቅድስት መንበር ተሳትፎን በተመለከተም ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው ብለዋል። የቅዱስነታቸው ቃላቶች በመላው አለም ያስተጋባሉ

“እናም ለፍልስጤማውያን የድጋፍ መልእክት ይዤ እንደምምጣቴ መጠን ጉብኝቱ አስፈላጊ ነው”፣እንዲሁም አስፈላጊ የሆነ “የሥነ ምግባራዊ መመሪያ ሁከት ባለበት ዓለም ምን መደረግ እንዳለበት ያስተምራል” ብለዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ "በጋዛ እና በዌስት ባንክ ላይ እየሆነ ያለው ነገር አስከፊ ነው፣ እናም መቆም አለበት። አንዳንድ አቅጣጫ እንዲሰጡን እንደ ጳጳሱ ዓይነት የማበረታቻ ቃላት እንፈልጋለን" ብለዋል።

እየተፈጠረ ያለው ነገር አስከፊ ነው፣ እናም መመሪያ ለመስጠት እንደ ጳጳሱ ዓይነት ቃላት እንፈልጋለን ያሉት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አግቤኪያን በመቀጠል ከቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፓሮሊን ጋር ያደረጉትን ቆይታ “በጣም ጥሩ ስብሰባ ነው” ሲሉ ገልጸውታል።

"በጋዛ ስላለው ሁኔታ፣ በዌስት ባንክ፣ በክርስቲያኖች መገኘት፣ የክርስቲያኖች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን፣ በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደረገው ቅስቀሳ፣ ምን መደረግ እንዳለበት፣ በአካባቢው ሰላም ሊያመጣ ስለሚችለው ሁኔታ... ወዘተ ተወያይተናል ብለዋል።

ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በተለያዩ ሀገራት ያደረጉት ጉብኝት ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ “ለትክክለኛው ነገር እንዲቆም” ለመጠየቅ አጋጣሚ ሆኖ ቆይቷል ያሉ ሲሆን “በአሁኑ ጊዜ ትክክል የሆነው የሰዎች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እና ዓለም አቀፍ ህግ ነው” ብለዋል፣  አክለውም ሁሉም ፍልስጤማውያን የሚጠይቁት አለም አቀፍ ህግ እንዲከበር ነው ሲሉ በአጽኖት ተናግረዋል።

ፍልስጤማውያን ዓለም አቀፍ ህግን ለመከተል እና አለም አቀፍ ህግን ለማክበር ብቻ ነው የሚጠይቁት ያሉ ሲሆን

"ለአለም አቀፍ ህግ እና ለሰብአዊ መብት ነው የምንታገለው የምትል ሀገር ያን፣ አለም አቀፍ ህግጋት ያለ ምንም ድርብ መስፈርት ማክበር አለባት፣ ይህ በአለም ላይ ሌላ ቦታ ቢሆን ኖሮ" ሁሉም ሀገራት "በእግራቸው ይቆሙ ነበር" ሲሉ አለም ስለፍልስጤማዊያን ችላ ያለበትን ሁኔታ አስረድተዋል።

እኛ የጠበቅነው ነገር ነው ያሉት ሚኒስትሯ፣ ምንም ይሁን ምን እየተከሰተ ወይም ማን ምን እንደምያደርግ ሳይለይ መላው ዓለም “ትክክለኛው ነገር ትክክል ነው” እንዲል እንጠብቃለን ብለዋል።

ይህ ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት፣ እንደተጠቀሰው፣ ጣሊያን እና ሳን ማሪኖ ከመድረሳቸው በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አግቤኪያንን ወደ ስሎቬኒያ፣ ክሮኤሺያ፣ ላቲቪያ እና ሊቱዌኒያ አቅነተው የነበረ ሲሆን አላማውም “ለፍልስጤማውያን ችግር ድጋፍ ማሰባሰብ፣ ለፍልስጤም እውቅና እና ለተጨማሪ ሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ማሰባሰብ” እንደሆነ ገልጸዋል።

ፍልስጤማውያን ህሙማን እዚህ ሆስፒታሎች ውስጥ እየታከሙ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ከባድ ሥር የሰደዱ ሕመም ያለባቸውም ሆነ በጦርነት የቆሰሉትን ሁኔታ በተመለከተ አንዳንድ ጉዳዮች አሳሳቢ እና አንዳንድ ሕመምተኞች በጣም ከባድ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው ቢሆንም አስፈላጊውን እንክብካቤ እያገኙ መሆናቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ምንም እንኳን ለመልሶ ማቋቋም እና ለማገገም ጊዜ ቢያስፈልግም አንዳንዶቹ በጥሩ ሁኔታ በማገገም ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

04 Sep 2025, 11:34