ፈልግ

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር፥ በስሎቬኒያ ብሌድ ከተማ በተካሄደው 20ኛው የብሌድ ስትራተጂክ መድረክ ስብሰባ ላይ ሊቀ ጳጳስ ጋላገር፥ በስሎቬኒያ ብሌድ ከተማ በተካሄደው 20ኛው የብሌድ ስትራተጂክ መድረክ ስብሰባ ላይ   (Bled Strategic Forum)

ሊቀ ጳጳስ ላገር፥ የውይይት እና የጋራ መግባባት አስፈላጊነትን እንደገና መገንባት እንደሚገባ አሳሰቡ

በቫቲካን የመንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግንኙነት ክፍል ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፖል ሪቻርድ ጋላገር፥ በስሎቬንያ ብሌድ ከተማ በተካሄደው የስትራቴጂክ ፎረም ስብሰባ የመጨረሻ ቀን ባደረጉት ንግግር፥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተከፋፈለ በመጣው ዓለም ውስጥ የውይይት እና የጋራ መግባባት አስፈላጊነትን እንደገና መገንባት እንደሚገባ አስምረውበታል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በስሎቬኒያ ከተማ ብሌድ ውስጥ በተካሄደው 20ኛው የብሌድ ስትራተጂክ መድረክ ላይ የተሳተፉት በቅድስት መንበር የመንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግንኙነት ክፍል ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፖል ሪቻርድ ጋላገር፥ የነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ፈለግ በመከተል ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ውይይትን፣ መተሳሰብን እና ቆራጥነትን በማጎልበት ሰላምን ለማስፈን የሚያደርጉትን ጥረት በማስመልከት ተናግረዋል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2006 የተከፈተው የብሌድ ስትራተጂክ ፎረም፥ አውሮፓን እና ዓለምን በሚመለከቱ ፖለቲካዊ፣ ፀጥታን እና የልማት ጉዳዮች የሚመለከት ስብሰባ አዘጋጅቷል። የዘንድሮው ስብሰባ መሪ ሃሳብ “ለማምለጥ የሚሞክር ዓለም” የሚል ሲሆን፥ አውሮፓ እና በተለይ የአውሮፓ ኅብረት ዓለማችንን እያጋጠመው ያለውን ውስብስብ ጂኦፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የአየር ንብረት ቀውሶች እና ውጥረቶችን ለመፍታት የሚቻልበት ሚናን በማቀናጀት ላይ ያተኮረ እንደ ነበር ታውቋል።

ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በፎረሙ የመጨረሻ ቀን ማክሰኞ ነሐሴ 27/2017 ዓ. ም. “በግጭት እና በመበታተን ዘመን ውስጥ አመራርን እና መልቲላተራሊዝምን ማደስ” በሚል ርዕሥ በቀረበው ውይይት ላይ ተሳትፈዋል። ክርክሩ ፖለቲካዊ እና ማህበረሰባዊ ጥረቶች ሰላምን በመደገፍ፣ አመራርን በድፍረት በማካተት፣ የባለብዙ ወገን መንገዶችን በተከፋፈል ዘመን ውስጥ እንደገና መገንባትን የተመለከት እንደ ነበር ታውቋል። ውይይቶቹ ለሰላም የቆመ አመራር የዛሬውን ዓለም ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት ደፋር እና የጋራ ተግባር እንደሚያስፈልግ የሚጠቁሙ እንደ ነበር ተመልክቷል።

ከተሳታፊዎቹ በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ውይይት ከተደረጉባቸው ርዕሠ ጉዳዮች መካከል ሊቀ ጳጳስ ጋላገር፣ የጋራ መግባባት እና ውይይት ባለመኖሩ ምክንያት በፖለቲካዊ ጥረቶች መካከል የተፈጠሩ ተግዳሮቶችን በማስመልከት ሌሎች ተሳታፊዎች የሰጡትን አስተያየት አምነዋል። የጋራ መግባባትን መፍጠር ዛሬ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ እና አዳዲስ ሃሳቦችን፣ አካሄዶችን እና መፍትሄዎችን ማምጣት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። በየደረጃው የጋራ መግባባት መፍጠር አስቸኳይ ነው በማለት እንደ የተባበሩት መንግሥታት ወይም በከፍተኛ ብሔራዊ ደረጃ ላይ ባሉት ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ሁኔታዎች ጀምሮ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሊቀ ጳጳስ ጋልገር አክለውም፥ አብዛኞቹ የፖለቲካ መሪዎቻችን ወደ አወንታዊ አቅጣጫ የመቀየር ብቃት እንዳለ በግል ቢያምኑም ውይይት፣ መግባባትን መፍጠር እና መተሳሰር ያስፈልጋል ብለዋል። በተቋማት ውስጥ እየጨመረ ያለው መከፋፈል እና ልዩነት ብሄራዊ መንግሥታትን ጨምሮ ታማኝነትን በማጣት እምነት እንዳይጣልባቸው አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለው፥ ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው የሚፈልጓቸውን ሁለቱን መሠረታዊ ነገሮች ማለትም ብልጽግናን እና ደኅንነት ማስጠበቅ ስለማይችሉ ዛሬ ስንቱ በዴሞክራሲ ቀውስ ውስጥ ይገኛል? ሲሉ አክለዋል።

በቅድስት መንበር የመንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግንኙነት ክፍል ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፖል ሪቻርድ ጋላገር፥ በውድቀት ላይ የሚገኝ ሥርዓትን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፥ ዛሬ ሕጎችን ማክበር ያለብን አንዳንድ ጥቅማጥቅሞች ሲኖሩ እንደ ሆነ ገልጸው፥ ቀደም ባሉት ጊዜያት ግን ሥርዓተ ደንቡ ሁሉንም ሰው ለመጠበቅ የሚያስችል መንገድ ይሰጥ ነበር ብለዋል።

 

03 Sep 2025, 16:44