ፈልግ

Cookie Policy
The portal Vatican News uses technical or similar cookies to make navigation easier and guarantee the use of the services. Furthermore, technical and analysis cookies from third parties may be used. If you want to know more click here. By closing this banner you consent to the use of cookies.
I AGREE
በሮም ከተማ የሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል በሮም ከተማ የሚገኘው የጂሜሊ ሆስፒታል   (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ትላንት ምሽት በሆስፒታል ውስጥ በመልካም ሁኔታ ማሳለፋቸው ተገልጿል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትላንት መጋቢት 04/2017 ዓ.ም ምሽቱን በመልካም ሁኔታ ማሳለፋቸው የተገለጸ ሲሆን በእለቱ የሮማ ኩሪያ የሚያደርገውን ሱባሄ ካሉበት ሁነው በቪዲዮ ተከታትለዋል ሲል የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ቢሮ አስታወቀ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት በሮም ጂሜሊ ሆስፒታል የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን ምሽት አስመልክቶ ጋዜጠኞችን ለማሳወቅ አርብ መጋቢት 05/2017 ማለዳ ላይ መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው “ጳጳሱ መልካም ምሽት አሳልፈዋል" ሲል አክሎ ገልጿል።

ሐሙስ ምሽት ላይ የፕሬስ ጽህፈት ቤቱ መግለጫ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ተተኪ ሁነው የተመረጡበትን 12ኛ አመት አስመልክተው የጤና አጠባበቅ ሰራተኞች በተገኙበት በእዚያው በሆስፒታል ሁነው አክብረዋል ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሮማን ኩሪያ ዓመታዊ መንፈሳዊ ልምምዶችን ወይም ሱባሄ ከጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ በቪዲዮ ሲከታተሉት ቆይተዋል፣ ይህም ሱባሄ አርብ ይጠናቀቃል።

አብ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ "የዘላለም ሕይወት ተስፋ" በሚል መሪ ሃሳብ ላይ በየቀኑ ሁለት ጊዜ አስተንትኖ ለሮማ ኩሪያ ባለስልጣናት እንደሚሰጡ ታውቋል።

ቅዱስ አባታችን በምሽት አየር መተንፈሻ ማሽን እግዛ የተደርገላቸው ሲሆን ቀን ቀን በአፍንጫቸው ውስጥ በሚደረግ ቱቦ ከፍተኛ ፍሰት ያለው ኦክሲጅን በመጠቀም ላይ እንደሚገኙም ተዘግቧል።  የፕሬስ ጽህፈት ቤቱ አርብ አመሻሽ ላይ ስለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጤና አዲስ የሕክምና መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

 

 

14 Mar 2025, 11:38
Prev
March 2025
SuMoTuWeThFrSa
      1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031     
Next
April 2025
SuMoTuWeThFrSa
  12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930