ሲኖዶስ፡ የአስሩ የጥናት ቡድኖች አስተባባሪዎች እና ጸሃፊዎች ስብሰባ አደረገ
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የጳጳሳት ሲኖዶስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አንደኛ ጉባኤ ላይ የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት በሊቀ ጳጳሱ ከተቋቋሙት የቡድን ተወካዮች ጋር ማክሰኞ የካቲት 11/2017 ዓ.ም ረፋድ ላይ ውይይት ተካሂዷል። ከስብሰባው በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ እያንዳንዱ አስተባባሪ በቡድናቸው ሥራ ላይ ያተኮረ ማሻሻያ አቅርቧል፣ በተጠቀመበት ዘዴ፣ በሚመለከታቸው አካላት፣ ሪፖርቶችን ለማቅረብ የሚጠበቀው የጊዜ ሰሌዳ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ማንኛቸውም አስደናቂ ጥያቄዎች ላይ በማተኮር የተከናወነ ሲሆን ስብሰባው የተከፈተው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከህመማቸው በቶሎ እንዲያገግሙ በመጸለይ እንደ ነበረም ተገልጿል።
ከእያንዳንዱ አስተባባሪ የተሰጡ መግለጫዎች
በመቀጠልም እያንዳንዱ አስተባባሪ በየተራ የቡድናቸውን ሂደት አቅርቧል፣ የተጠቀሙበትን ዘዴ፣ የሚመለከታቸውን ሰዎች እና ድርጅቶች፣ የመጨረሻ ሪፖርታቸውን ለማቅረብ የሚጠበቀው የጊዜ ገደብ፣ ያጋጠሟቸውን ችግሮች እና ማንኛቸውም ክፍት ጥያቄዎችን ዘርዝረዋል። መግለጫው ይህ “የበለፀገ የመጋራት ጊዜ፣ በተለይም ‘ተለዋዋጭ’ ጉዳዮችን ለሚመለከቱ የጥናት ቡድኖች ጠቃሚ ነው” ብሏል።
እያንዳንዱ አስተባባሪ ከተናገረ በኋላ፣ የጠቅላይ ጽህፈት ቤቱ አማካሪ የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል የሆኑት አባ ጂያኮሞ ኮስታ እንደ ተናገሩት "ሪፖርቶችን በማዘጋጀት እና በማስረከብ ላይ ወጥነት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ መመሪያ" ሰጥተዋል።
ከቀኖናዊ ኮሚሽን ድጋፍ
በተለይ ህጋዊ ወይም ቀኖናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ቀኖናዊ ኮሚሽኑ ሊረዳቸው እንደሚችል አስተባባሪዎቹ ተነግሯቸዋል። ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች ለተሳታፊዎች የውጫዊ አስተዋጾ ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑን አስታውሰው አሁንም በኢሜል (synodus@synod.va) ለጠቅላይ ጽህፈት ቤቱ እስከ መጋቢት 21/2017 ዓ.ም ድረስ መቅረብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። ቀደም ሲል የጳጳሳት ሲኖዶስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሁለተኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ እንደተገለጸው ማንኛውም አዲስ አስተዋጽዖ ለሚመለከታቸው አካላት ቢደርስ በፍጥነት ይስተናገዳል የምል መመሪያ እንደ ወጣም ይታወቃል።
የጥናት ቡድኖች
አሥሩ የጥናት ቡድኖች የተቋቋሙት የጳጳሳት ሲኖዶስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አንደኛ ጉባኤን ተከትሎ ሲሆን በጉባኤው ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕይወትና ተልዕኮ ከሲኖዶስ አንፃር የሚመለከቱ አንገብጋቢ ጉዳዮች ተለይተዋል። ጉባኤው በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ሰፊ መግባባት ላይ ደርሷል፣ ይህም አስፈላጊነታቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለንተናዊ ቤተክርስቲያን ደረጃ ላይ ማሰላሰል እና ጥልቅ ጥናት ማድረግን ይጠይቃል።
የጥናት ቡድኖቹ እ.አ.አ በመጋቢት 2024 ዓ.ም የተቋቋሙት ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅድስት መንበር ጽ/ቤቶች እና በሲኖዶስ አጠቃላይ ጽሕፈት ቤት ትብብር እንዲሁም ለካርዲናል ማሪዮ ግሬች የላኩት ደብዳቤ ነው። በዚህ ደብዳቤ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ግሬች የጥናት ቡድኖችን ሥራ “በእውነትም በሲኖዶሳዊ መንፈስ” እንዲቆጣጠሩ አደራ ሰጥተው ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከእዚህ መመሪያ አንጻር የቡድኖቹን ኃላፊነት የሚገልጽ የሥራ ዝርዝር እንዲያዘጋጁ ጠይቀዋል።