ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ነጋዲያን የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ በር መሻገራቸው ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ከልዩ ልዩ አካባቢዎች በአጫጭር እና ረጃጅም ሰልፎች የሚመጡ ነጋዲያን የእንጨት መስቀሎቻቸውን በማስቀደም ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ እንዲያደርሳቸው የተዘጋጀላቸውን መንገድ ይዘው ጸሎት እያደረሱ በሚጓዙበት ጊዜ አረንጓዴ ጃኬት በለበሱ የጉዞው አስተባባሪዎች በመታጀም እንደሆነ ተመልክቷል። የጎርጎሮሳውያኑ 2025 ቅዱስ ዓመት ከገባ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የባዚሊካውን ቅዱስ በር የተሻገሩት ነጋዲያን ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መድረሱ ተነግሯል።
ጅምሩ እጅግ የሚያስደስት እና ጠቃሚ ነው!
በቅድስት መንበር የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት የኢዮቤልዩ በዓል ዝግጅት አስተባባሪ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረጉት መግለጫቸው፥ ቅዱስ ዓመት በገባ ሁለተኛው ሳምንታት ወደ ባዚሊካው የመጡት ነጋዲያን ቁጥር በትክክል 545,532 መድረሱን ገልጸው፥ ይህ በብዙ ቁጥር የሚገለጽ ተሳትፎ ትልቅ ትርጉም ያለው እና መልካም ጅምር ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሚወስደው “በቪያ ዴላ ኮንቺሊያሲዮኔ” ጎዳና ላይ የሚታዩ አጫጭር እና ረጃጅም የነጋዲያን ሰልፎች ጠቃሚ ምስክርነት እየሰጡ መሆናቸውን የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ፥ ይህ ደግሞ በሮም እና በአራቱ ጳጳሳዊ ባዚሊካዎች አካባቢ ምዕመናን ለደህንነታቸው ያለውን ታላቅ ግንዛቤ የሚያሳይ ምልክት ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
የደህንነት እና የነጋዲያን ፍሰት ቁጥጥር
የኢዮቤልዩ ቅዱስ ዓመት በዓል ዝግጅት አስተባባሪ ክፍል መግለጫ እንዳመለከተው፥ ቅድስት መንበር ከስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት፣ ከጣሊያን እና ከቫቲካን የጸጥታ ኃይሎች ጋር የቅርብ ትብብር እንዳላት ገልጾ፥ ይህም የምእመናንን ተሳትፎ በቋሚነት ይጨምራል” ተብሎ እንደሚጠበቅ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ ገልጸው፥ ነጋዲያኑን በማስተናገድ ላይ የሚታዩ የመጀመርያዎቹን ችግሮች በጊዜ ሂደት መገምገም እንዳለባቸው እና ነጋዲያንን ለመቀበል የሚያስችል ልምድ እንዲኖረው ለማድረግ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቱ ያለመታከት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የቅድሚያ ምዝገባ
ቅዱስ በሮች ከተከፈቱ በኋላ ባለፉት ቅርብ ቀናት ውስጥ አራቱን ጳጳሳዊ ባዚሊካዎች የሞሉት እና ከባዚሊካው ፊት ለፊት ያሉትን አደባባዮች ያጨናነቁ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ነጋዲያን በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ምን እንደሚፈጠር ምልክቶችን ያሳየው የኢዮቤልዩ ክስተቶች የቀን መቁጠሪያው፥ ወደ ፊት የሚጠበቁትን የምዕመናን ረጅም ወረፋዎች ግምት ውስጥ በማስገባት “iubilaeum2025.va” በሚለው የኢዮቤልዩ ድረ-ገጽ ላይ በቅድሚያ መመዝገብ እንደሚያስፈልግ መግለጫው አስታውሷል።
የመጀመሪያው ክስተት የሚሆነው ከዓለም ዙሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ባለሙያዎች ወደ ሮም በበምጣት ከጥር 16-18/2017 ዓ. ም. ድረስ የሚያከብሩት የመገናኛው ዓለም ኢዮቤልዩ በዓል እንደሚሆን ይጠበቃል።