አቶ ጆሴፍ አውን፣ የሊባኖስ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አቶ ጆሴፍ አውን፣ የሊባኖስ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት  (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 14ኛ ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኙ፣ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም ያስፈልጋል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሐሙስ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም በቫቲካን ከሊባኖስ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ጋር መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ በመቀጠልም በዩናይትድ ስቴትስ፣ እስራኤል እና ሊባኖስ በተፈረመው ስምምነት ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል። ለቅድስት መንበር ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ በሚፈጠሩ ችግሮች ላይ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል እና ለዚህም ዓላማ ቅድስት መንበር ድጋፍ እንድትሰጥ ተማጽነዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ፕሬዝዳንቱ በመቀጠልም ከቅድስት መንበር ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፒትሮ ፓሮሊን ጋር እና ከቅድስት መንበር ከሌሎች አገራት እና ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገው ግንኙነት የሚከታተለው ጽ/ቤት ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ​​ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ጋር ተገናኝተዋል።

ከስብሰባዎቹ በኋላ በቅድስት መንበር የፕሬስ ጽሕፈት ቤት በሰጠው መግለጫ፣ ከቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፕዬትሮ ፓሮሊን ጽሕፈት ቤት የተደረጉት ውይይቶች “ሞቅ ያለ” እና “በመሠረቱ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በእስራኤል እና በሊባኖስ የተፈረመው እና የሊባኖስን ደቡባዊ ድንበሮች ለማረጋጋት እና ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የታሰበ የሶስትዮሽ ማዕቀፍ ስምምነት ላይ ያተኮሩ ነበሩ” ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።

"ቅድስት መንበር ሰነዱ በመፈረሙ እርካታዋን ስትገልጽ፣ በተግባር ላይ ስለሚገጥሟቸው ችግሮች ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል፣ እናም በዚህ ረገድ ለሚደረጉ ጥረቶች ድጋፍ እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል" ሲል መግለጫው ደምድሟል።

ለሊባኖስ ፕሬዝዳንታዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል

ፕሬዝዳንት አውን በሊባኖስ ፕሬዝዳንት ድረ-ገጽ ላይ በታተመው መግለጫ፣ ለሊባኖስ ፕሬዝዳንትነት ድጋፍ ላደረጉት ጥረት ሁሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እና ለቅድስት መንበር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በተለይም የቤሩትን ጥያቄዎች መደገፋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፣ ከእነዚህም መካከል እስራኤል እ.አ.አ ሰኔ 26/2026 ዓ.ም በአሜሪካ ድጋፍ የተፈረመውን የማዕቀፍ ስምምነት ውሎች ተግባራዊ እንድታደርግ የቀረበው ጥሪ ይገኝበታል።

አውን እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ውስጥ በተለይም ሲቪሎችን፣ መሠረተ ልማቶችን እና መንደሮችን ላይ  የሚያነጣጥሩ ዕለታዊ ጥቃቶች እንድታቆም እና ከተያዙ ግዛቶች እንድትወጣ ጥሪ አቅርበዋል፣ ይህም የፈረሰውን መልሶ ለመገንባት እና የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመመለስ መንገድ ይጠርጋል።

ፕሬዝዳንት አውን የሊባኖስ ፕሬዝዳንት መግለጫ በመቀጠል፣ እነዚህ እርምጃዎች የሊባኖስ መንግስት በሁሉም ግዛቷ ላይ ያለውን ሥልጣን ማራዘም እንዳለበት አፅንዖት ሰጥቷል።

በደቡባዊ ሊባኖስ ውጥረት ነግሷል

በቫቲካን የሚደረጉት ስብሰባዎች በተለይም በደቡባዊ ሊባኖስ ከፍተኛ ውጥረት በነገሠበት ወቅት ነው፣ እ.አ.አ የካቲት 17/2026 ከእስራኤል ጋር የተደረሰውን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢቀጥልም ጥቃቶች ግን እስካሁን ድረስ አልቆሙም።

እስራኤል የሂዝቦላህ መሠረተ ልማት እና ሰራተኞችን ብቻ ኢላማ እያደረገች እንደሆነ ስትናገር ቤሩት ደግሞ የእስራኤልን ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ማውገዛቷን ቀጥላለች።

ከዚህ ዳራ አንጻር፣ በደቡባዊ ሊባኖስ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ የፖለቲካ አለመግባባት ቀጥሏል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የማዕቀፍ ስምምነት ለማራመድ እና የሰላም ካርታ ለማቋቋም ያለመ ለስምንተኛው ዙር የአሜሪካ ሽምግልና ውይይት ገና የተወሰነ ቀን የለም።

 

21 Aug 2026, 16:29