የአቶ አንድሪያ ቦቼሊ የሰላም መዘምራን ፋውንዴሽን የአቶ አንድሪያ ቦቼሊ የሰላም መዘምራን ፋውንዴሽን  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በካስቴል ጋንዶልፎ ‘ለሰላም የሚደርገውን ዝማሬ" እንደሚመሩ ተገለጸ!

ቫቲካን ኒውስ በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው 'ቦርጎ ላውዳቶ ሲ’ ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የሚመራውን የጸሎት ፕሮግራም፣ በአቶ አንድሪያ ቦቼሊ እና ከአምስት አገሮች የተውጣጡ 164 ወጣቶችን ያቀፈውን በእንግሊዜኛው ቋንቋ የABF Voices መዘምራን የሚያደርጉትን ዝማሬ ቅዱስነታቸው እንደሚመሩት ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ረቡዕ፣ ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ቫቲካን ኒውስ በድረገጹ www.vaticannews.va እና በዩቲዩብ ቻናሉ ላይ በቦርጎ ላውዳቶ ሲ’ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የሚመራውን የጸሎት እና የወንድማማችነት ስብሰባ፣ እና ለሰላም የሚደርገውን መዝሙር  በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው ቦርጎ ላውዳቶ ሲ’ ይመራሉ። ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በላውዳቶ ሲ’ ከፍተኛ የትምህርት ማዕከል እና በአቶ አንድሪያ ቦቼሊ ፋውንዴሽን ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በችግር ከተጎዱ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ሕፃናትና ወጣቶችን ያቀፈ ዓለም አቀፍ የመዘምራን ቡድን ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እና አቶ አንድሪያ ቦቼሊ ጋር በመሆን ለጸሎት ጊዜ ይሰጣሉ...

የኤቢኤፍ ድምጾች የመዘምራን ምስክርነት

በእንግሊዘኛው ቋንቋ የ(ABF Voices choir) ፕሮጀክት የተሰኘው በአቶ በአንድሪያ ቦቼሊ ፋውንዴሽን የተመሰረተ ዓለም አቀፍ የትምህርት እና የማህበራዊ ሙዚቃ ፕሮግራም ሲሆን በዓለም ዙሪያ ካሉ ተጋላጭ ክልሎች የተውጣጡ ህጻናትን እና ወጣት መዘምራንን ያሰባስባል። ከጣሊያን፣ ኡጋንዳ፣ ሄይቲ እና ቅድስት አገረ ወይም ምድርን ጨምሮ 164 ወጣት ተሳታፊዎችን አካቶ የያዘ ፕሮጄክት ነው።

ዝግጅቱ የአዚዚን የቅዱስ ፍራንችስኮስ ሞት ስምንተኛ ምዕተ ዓመት የሚከብረው ክብረ በዓል አካል ነው። ጸሎቱ በሙዚቃ ልዕቁ አቶ አንድሪያ ቦቼሊ ድምፅ እና ከእስራኤል፣ ከዌስት ባንክ፣ ከኡጋንዳ፣ ከሄይቲ እና ከጣሊያን የተውጣጡ 164 ልጆችን እና ወጣቶችን ያቀፈው የኤቢኤፍ ድምጾች መዘምራን አጣምሮ የያዘ ነው።

እነዚህ ወጣቶች የተለያዩ የሕይወት ታሪኮችን ይዘው ይመጣሉ፣ ብዙዎቹም በጦርነት፣ በድህነት ወይም በመከራ የተመሰሉ ናቸው። አብረው ሲዘምሩ፣ የኪነጥበብ ኃይልን ለመመስከር ያለሙ ሲሆን ይህም የውይይት፣ የተስፋ እና የእርቅ ቋንቋ እንዲሆን ነው።

29 Jul 2026, 16:16