ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስተል ጋንዳልፎ የጳጳስ የዕረፍ ማድረጊያ ሥፍራ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በካስተል ጋንዳልፎ የጳጳስ የዕረፍ ማድረጊያ ሥፍራ  (foto di padre Bruno Silvestrini)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሐምሌ ወር በካስቴል ጋንዶልፎ የበጋ የእረፍት ጊዜ እንደ ምያሳልፉ ተገለጸ

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት አቃበ ነዋይ እንደ ገለጹት ከሆነ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሰኔ 28 እስከ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ድረስ በሮም ከተማ አቅራቢ በሚገኘው በካስቴል ጋንዶልፎ የጳጳስ የእረፍት ማድረጊያ ሥፍራ እንደሚቆዩ እና በዚህ ጊዜ ውስጥ ሁሉንም ይፋዊ ሥራቸውን እና ከታዳሚዎች ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት እንደምያቋርጡ ተናግሯል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ

ባለፈው ዓመት እንዳደረጉት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በበጋ ወቅት ከቫቲካን አንድ ሰዓት ያህል ርቀት ላይ በሚገኘው በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው የጳጳስ መኖሪያ ቤት የተወሰነ ጊዜ ያሳልፋሉ።

"እሁድ ሰኔ 28/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ፣ ቅዱስ አባታችን እስከ ሰኞ፣ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ድረስ ለእረፍት ወደ ካስቴል ጋንዶልፎ ሐዋርያዊ የጳጳስ ማረፊያ ቤተ ይሄዳሉ" ሲሉ እሁድ ዕለት የወጣው የሊቀ ጳጳሱ ቤተ አቃበ ነዋይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ይህ መግለጫ በዚህ ጊዜ ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተለምዶ ያደርጓቸው የነበሩ ይፋዊ ግንኙነቶች እና አስተምህሮዎች ለጊዜው እንደሚቋረጡ እና ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 በድጋሚ እንደሚቀጥል ከወጣው መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።

እ.አ.አ በ2025 ዓ.ም የበጋ ወቅት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እ.አ.አ ከሐምሌ 6 እስከ ሐምሌ 22/2025 ባለው ጊዜ ውስጥ በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው ቪላ ባርቤሪኒ ለ16 ቀናት አሳልፈዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ፣ ለአካባቢ ጥበቃ በተዘጋጀው “ላውዳቶ ሲ መንደር” (‘ቦርጎ ላውዳቶ ሲ’) ላይ መስዋዕተ ቅዳሴ ከማሳረግ ጀምሮ አንዳንድ የሕዝብ ዝግጅቶችን ማከናወናቸውን ቀጥለው እንደ ነበረ ይታወሳል። እንዲሁም የቪላኖቫ የቅዱስ ቶማስ ጳጳሳዊ ቁምስና እና የአልባኖ ካቴድራልን ጎብኝተዋል።

በዚያ ወቅት በርካታ አስፈላጊ ስብሰባዎችን አካሂዷል፤ ከእነዚህም መካከል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቪላ ባርቤሪኒ የተቀበሉትን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ እና እስራኤል በጋዛ በሚገኘው የቅድስት ቤተሰብ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ ውይይት አድርገዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በኋላም ከፍልስጤም ግዛት ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ጋር የስልክ ውይይት አድርገው እንደ ነበረም ይታወሳል።

 

06 Jul 2026, 15:12