ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፣ ቴክኖሎጂ እውነትን እና የጋራ ጥቅምን ማገልገል አለበት አሉ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ቤተክርስቲያኗ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (የሰው ሰራሽ አስትውሎት) የቀረቡትን እድሎች እና ተግዳሮቶች እያሰላሰለች እያንዳንዱ የቴክኖሎጂ መሳሪያ "ለእውነት እና ለጋራ ጥቅም አገልግሎት" እንዲውል አስተባባሪዎችን አበረታተዋል።
በቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የተፈረመው መልእክታቸው ከሐምሌ 20 እስከ ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም በሳንቲያጎ በሚገኘው የቺሊ የጳጳሳዊ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ በሚካሄደው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያን ግንኙነት ትምህርታዊ ጉባኤ ላይ ለተሳተፉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) ተግዳሮቶች በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ትምህርታዊ ጉባኤ ከላቲን አሜሪካ እና ከካሪቢያን የተውጣጡ የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎችን፣ ሐዋርያዊ መጋቢዎችን፣ ምሁራንን እና የቤተክርስቲያን ተወካዮችን በሊቀ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በላቲን ቋንቋ "Magnifica humanitas" (ድንቅ ሰብዓዊነት) በተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት መሰረት የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) ሥነ ምግባራዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ አንድምታዎችን ለማንፀባረቅ አስችሏል።
ጥበብ እና ኃላፊነት በ AI
የቺሊ ጳጳሳት ኮንፈረንስ ፕሬዝዳንት ሊቀ ጳጳስ ሬኔ ኦስቫልዶ ሬቦሌዶ ሳሊናስን ሲናገሩ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተሳታፊዎች "በቴክኖሎጂ ልማት የሚሰጡ አዳዲስ እድሎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሰውን ልጅ ክብር እንዴት መጠበቅ እንደሚችል የሚያውቅ እና እያንዳንዱን መሳሪያ ለእውነት እና ለጋራ ጥቅም እንዴት እንደሚያውል የሚያውቅ ግንኙነት" እንደሚያስተዋውቁ ተስፋ ያደርጋሉ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ትምህርታዊ ጉባኤውን መንፈስ ቅዱስ እንዲመራው በአደራ ሰጥተዋል፣ ተሳታፊዎቹ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚፈጠሩትን ተግዳሮቶች "በጥበብ እና በኃላፊነት እንዲፈቱ፣ የቤተክርስቲያን ግንኙነት በሰዎች መካከል መገናኘትን እንዲያበረታታ እና ወንጌልን ለማወጅ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ" ጸልየዋል።
ማህበራዊ ሚዲያ እንደ ሰው ቦታዎች
ትምህርታዊ ጉባኤውን ሲከፍቱ፣ የሳንቲያጎ ደ ቺሊ ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ፈርናንዶ ናታሊዮ ቾማሊ ጋሪብ የማህበራዊ ሚዲያን ተጽእኖ በማሰላሰል ስሜቶችን፣ ግንኙነቶችን እና ግጭቶችን ስለሚያንፀባርቁ "በእውነት ሰብዓዊ" ቦታዎች በማለት ገልጸዋቸዋል።
"በእኛ ላይ የሚደርስ ነገር ሁሉ እዚያም ይከሰታል" ሲሉ ለመግባቢያ አራት አስፈላጊ መስፈርቶችን አቅርበዋል፣ እውነት፣ መልካምነት፣ ውበት እና ጠቃሚነት። ካርዲናሉ በላቲን ቋንቋ "ማኝፊካ ሂውማኒታስ" (ታላቅ ሰብዓዊነት)፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመን የሰውን ልጅ ለመጠበቅ የተሰጡ፣ ከቴክኖሎጂ አንፃር ብቻ መነበብ እንደሌለባቸው አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።
"ዛሬ ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ብዙ ውይይት አለ" ብለዋል፣ "ነገር ግን ይህ ጳጳሳዊ መልእክት ከሁሉም በላይ ስለ ሰው ክብር እና እውነት ይናገራል" ሲሉ አብራርተዋል።
ባቢሎንን ሳይሆን ኢየሩሳሌምን መገንባት
ካርዲናል ቾማሊ በእነዚህ መርሆዎች ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እየጨመረ በመጣው ግለሰባዊ ማህበረሰብ ውስጥ የማህበረሰብ ህይወትን ሊያጠናክር እንደሚችል ተናግረዋል።
"ውይይትን እናበረታታለን፣ ወንድማማችነትን እናበረታታለን፤ በመጨረሻም ባቢሎንን ሳይሆን ኢየሩሳሌምን እንገነባለን" ብለዋል። ቀጥሎ በተደረገው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ካርዲናል ቾማሊ ባደረጉት ስብከት ውስጥ ተመሳሳይ ጭብጦች ተስተጋብተዋል። በላቲን ቋንቋ "ማኚፊካ ሂውማኒታስ"ን (ታላቅ ሰብዓዊነት) "ክሪስቶሎጂካል" (ማለት ከክርስቶስ ጋር የተያያዘው የክርስቶስ ትምህርት ክፍል ሲሆን ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ስብዕና፣ ተፈጥሮ እና ሥራ ላይ ያተኮረ ነው። ኢየሱስ ፍጹም ሰው እና ፍጹም አምላክ እንዴት እንደሆነ እና የሰውን ልጅ በማዳን ረገድ ያለው ሚና ምን እንደሆነ ጥናቶችን ወይም ሀሳቦችን ይገልፃል) የሆነ ጳጳሳዊ መልእክት በማለት የገለሱ ሲሆን፣ በማስተዋል ምልክት የተደረገበት ግንኙነት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሁልጊዜ ለሰው ልጅ ክብር አገልግሎት እንደሚውል ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ለቤተክርስቲያኑ የጋራ ጉዞ
በመክፈቻው ቀን ከተናገሩት መካከል የቺሊ የጳጳሳት ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ዳይሬክተር የሆኑት ሁዋን ካርሎስ ደ ላ ሌራ እና ሊቀ ጳጳስ ሬቦሌዶ ሳሊናስ ይገኙበታል፤ እነዚህም ስብሰባውን የሲኖዶሳዊነት እና የቤተክርስቲያኒቱን የጋራ ጉዞ የሚያሳይ ተጨባጭ መግለጫ አድርገው ገልጸውታል።
በላቲን ቋንቋ "ማኝኒፊካ ሂውማኒታስ" (ታላቅ ሰብዓዊነት) የተሰኘው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጳጳሳዊ መልእክት ህትመት ቤተክርስቲያኒቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በተመለከተ ያላትን የአባታዊ እና የሐዋርያዊ አስተሳሰብ እንደገና እንዳሳየች ተናግረዋል።
የሰው ልጅ የማይደፈር ክብር የቴክኖሎጂ እድገትም ሆነ የሳይንስ እድገት መርህ፣ መስፈርት እና የመጨረሻ ግብ መሆን አለበት" ብለዋል።
