ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፡ “ውበት ወደ ሰማይ እይታችንን እንድናነሳ ይረዳናል” ማለታቸው ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
"ውበት በማይጎድልበት ዓለም ውስጥ እንኖራለን። ብዙ ችግሮች አሉ - ጦርነቶች፣ ግጭቶች፣ ጥላቻ፣ ዓመፅ፣ ሥራ አጥነት እና ሌሎች ብዙ ችግሮች። እንደዚህ ዓይነት አጋጣሚ ለመሰብሰብ እድል ማግኘት በእውነት ትልቅ ስጦታ ነው፣ምክንያቱም ከዚህ ሁሉ በላይ እንዳለ ያስታውሰናል። ወንዶችና ሴቶች፣ ስንመርጥ፣ ከልብ ወደ ልብ፣ ወደ ሰማይ ለማየት እና እይታችንን ለማንሳት የሚረዳንን ውበት ለመግለጥ አንድ ላይ መሰባሰብ እንደሚችሉ ያስታውሰናል።" በእነዚህ ቃላት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ቅዳሜ ምሽት ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው የሐዋርያዊ የእርፍት ማድረጊያ ፓላስ ግቢ ውስጥ በተካሄደው ኮንሰርት መደምደሚያ ላይ ለተገኙ ሰዎች ካደረጉት ንግግር የተወሰደ ሲሆን ኮንሰርቱ የተዘጋጀው በአልባኖ ሀገረ ስብከት ነበር፣ ይህም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በበጋ ወቅት በሮም ደቡባዊ ከተማ ባሳለፉት የበጋ ቆይታቸው ለጳጳሱ ያላቸውን ቅርበት እና ፍቅር የሚያሳይ ምልክት ነው።
ወደ ሰማይ እይታችንን አነሳን
"እንደምታውቁት፣ ከአንድ ወር በፊት ወደ ስፔን ተጓዤ ነበር፣ እናም የዚያ ጉዞ ዋና ዓላማ ዓይኖቻችንን፣ እይታችንን ወደ ሰማይ ማንሳት ነበር። ሙዚቃ፣ ስነጥበብ እና ውበት ወደ ላይ እንድንመለከት፣ ወደ እግዚአብሔር እንድንሄድ እና በእርግጥም ከሰው ልጅ ምርጥ ገጽታዎች አንዱ ወደሆነው እንድንሄድ የሚረዱን መንገዶች ናቸው" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተናገሩ ሲሆን የሙዚቃ እና የስነጥበብን ዋጋ በማሰላሰል፣ የሰውን እይታ ከአሁኑ መከራ በላይ ከፍ ለማድረግ የሚችሉ መንገዶች እንደሆኑ ገልጸዋቸዋል፣ ውበትን ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ እና ተስፋን የሚያድስ ተሞክሮ እንደሆነ ጠቁመዋል። በኮንሰርቱ ወቅት የተከናወነው በትክክል ይህ ነበር። የቫዮሊኒስት ማርኮ ሮሊያኖ ፖሎናይዝን ከኒኮሎ ፓጋኒኒ ሶስተኛው የቫዮሊን ኮንሰርቶ ልዩ በሆነ ሁኔታ አሳይቷል፣ የፒያኖ ተጫዋች ሮሳና ቶማሲ ጎልካር ደግሞ በማኢስትሮ ፒየር ካርሎ ኦሪዚዮ መሪነት በሉዊስ ባካሎቭ የሊቤራ ፋንታሲያ ኢ ቫሪያዚዮኒ ሱላ ኖርማ አቅርቧል፣ በቪንቼንሶ ቤሊኒ ኖርማ ላይ የተመሠረተ ዝግጅት እንደ ነበረም ተገልጿል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለሙዚቀኞቹ ያላቸውን ምስጋና እንዲህ በማለት ገለጹ፡- "ለአርቲስቶች ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቅርቡልኝ። እናም በዚህ የውበት ወቅት ታላቅ ነገርን ለመለማመድ ችለናል፤ እግዚአብሔር በፍጥረት ውስጥ ወደፈለገው ነገር ማለትም ወደ ውበት መግባት" ሲሉ ኮንሰርቱን ላዛጋጀው ለአልባኖ ሀገረ ስብከት ምስጋና አቅርበዋል።
የአልባኖ ጳጳስ አስተያየት
ምሽቱ የተከፈተው የአልባኖ ጳጳስ በሆኑት ቪንሴንዞ ቪቫ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወደ ካስቴል ጋንዶልፎ በመመለሳቸው ለአካባቢው ቤተክርስቲያን ያቀረቡትን ምስጋና በማስታወስ ተቀብለዋል። ኮንሰርቱ "ምስጋና የምንሰጥበት እና የሲምፎኒክ ሙዚቃ (ሲምፎኒ ሙዚቃ ማለት ለሙሉ ሲምፎኒ እርስ በእርሱ የሚግባባ የሙዚቃ ድምጽ ኦርኬስትራ የተጻፉ ትላልቅና ውስብስብ የሙዚቃ ቅንብሮችን ሲሆን ይህም ጭብጥ ያለው እድገትና ለግርማ ሞገስ አፅንዖት ይሰጣል) ስጦታን አብረን የምንጋራበት መንገድ" እንዲሆን ታስቦ እንደነበር አስረድተዋል። የቤሊኒን ኖርማ በመጥቀስ፣ ጳጳሱ ሀሳባቸውን ወደ "በብዙ የጦርነት ትይንቶች ውስጥ ዓለምን እያፈረሱ ከልጆቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ከፍተኛውን የግጭት ዋጋ የሚከፍሉ ሴቶች እና እናቶች" አዙረዋል። በእነርሱ ውስጥ "ለነገ እርቅ ለመፍጠር" የሚለው ተስፋ እንደሚንጸባረቅ አስተውሏል፣ ይህም የሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ የሰላም ጥሪን የሚያስተጋባ መሆኑን አስተውሏል፣ ይህም ከጵጵስና ሥልጣናቸው መጀመሪያ ጀምሮ ደግመውታል ሲሉ ተናግረዋል።
በፓጋኒኒ እና በቤሊኒ መካከል
የኮንሰርት ፕሮግራሙ ሁለት የአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን የጣሊያን ሙዚቃ ግንባር ቀደም ተዋናዮችን ኒኮሎ ፓጋኒኒ እና ቪንሴንዞ ቤሊኒ ወደ ውይይት አምጥቷል። ሁለቱ ስራዎች በግጥም እና በመዘመር ጥራታቸው አንድ ሆነዋል፣ የሙዚቃ ጉዞን በመፍጠር የሙዚቃ መሳሪያዊ ብቃታቸውን እና የኦፔራ ቋንቋን ያጣመረ ነበር። የኖርማ ዳግም ትርጓሜ፣ በተለይም፣ በፒያኖ እና በኦርኬስትራ ብቻ፣ የዋናው ገፀ ባህሪ ከመከራ ወደ ይቅርታ እና የራስን ጥቅም መሥዋዕትነት ጉዞ ተመልሷል፣ የግል ታሪክን በፍቅር እና በሰላም ኃይል ላይ ወደ ሁለንተናዊ ነጸብራቅ ቀይሯል። የኮንሰርት ፕሮግራሙ እንደገለጸው፣ ውበት "በጦርነት ነፋሶች በሚናወጠው አየር" እንኳን የመሰማት ችሎታን ጭምር ይናገራል። ከካስቴል ጋንዶልፎ ሰማይ በታች ዓለም አቀፋዊ ለመሆን የፈለገ የተስፋ መልእክት ነበር። ኮንሰርቱ የተጠናቀቀው በኮከብ የተሞላ ሰማይ በስክሪኑ ላይ ኦርኬስትራውን በመቅረጽ ነው። በዝግጅቱ መጨረሻ ላይ ቅዱስ አባታችን ሙዚቀኞቹንና ተሰብሳቢዎቹን ተቀብለው ከሐዋርያዊ የእረፍት ማድረጊያ ፓላስ ግቢ ከመውጣታቸው በፊት ሰላምታ መለዋወጣቸው ተገልጿል።
