ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ሊዮ ለባርሴሎና የበጎ አድራጎት ሠራተኞች፡ ሕይወት አብረን የምንጓዝበት መንገድ ነው ማለታቸው

በባርሴሎና ከሚገኙት የሀገረ ስብከት የበጎ አድራጎት እና የካሪታስ ድርጅቶች ጋር ባደረጉት ስብሰባ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ስለ ስቃይ፣ ይቅርታ እና የሕይወት ትርጉም በአንድ ትንሽ ልጅ ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፣ እውነተኛ በጎ አድራጎት የሚጀምረው ክርስቶስን በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ በማወጅ መሆኑን ለክርስቲያኖች ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

አንድ ልጅ ስለ ሕይወት፣ ስቃይ፣ ይቅርታ እና የእግዚአብሔር ዕቅዶች ያነሳቸው ጥያቄዎች ረቡዕ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በባርሴሎና በሚገኘው የቤተክርስቲያኗ የበጎ አድራጎት ማዕከል መካከል በሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ እና በባርሴሎና ውስጥ ላለው የቤተክርስቲያኗ የበጎ አድራጎት ማዕከል የግል ግንኙነት መንገድ ከፍተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወደ ስፔን ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት በአምስተኛው ቀን በቅዱስ አጎስጢኖስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሀገረ ስብከት የበጎ አድራጎት እና የካሪታስ ድርጅቶች ሰራተኞችን ጋር ከተገናኙ በኋላ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ድሆችን፣ አረጋውያንን፣ ስደተኞችን እና የተገለሉትን ሰዎች በማገልገል ላይ ከተሰማሩ ሰዎች ምስክርነት አዳምጠዋል፣ ሬንዞ በተባለ የስድስት ዓመት ልጅ የተጻፈ ደብዳቤ ምላሽ ከመስጠታቸው በፊት ማለት ነው።

ነገር ግን የሕፃኑን ጥያቄዎች ከማቅረባቸው በፊት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በዙሪያቸው ለተሰበሰበው ማህበረሰብ ያላቸውን ምስጋና እና ፍቅር ለመግለጽ ጊዜ የወሰዱ ሲሆን  "እዚህ፣ በእውነት፣ ቤት ውስጥ እንደሆንኩ ይሰማኛል" ብለዋል። የቅዱስ አውጉስጢኖስ ቤተክርስቲያን እንደ ቅዱስ አውጎስጢኖስ ማሕበር አባል ለእርሳቸው ልዩ ጠቀሜታ እንዳለው አምነው ሲቀበሉ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከአርባ ዓመታት በላይ የቆየ የግል ትዝታ አጋርተዋል።

"ለመጀመሪያ ጊዜ ወደዚህ ቤተክርስቲያን የመጣሁት እ.አ.አ በ1984 ዓ.ም ነበር" ሲሉ ያስታውሳሉ። "ከሮም ወደ ሌዮን በምድር እየተጓዝኩ ነበር እናም "በባርሴሎና የቅዱስ አውጎስጢኖስ ቤተክርስቲያን አለ፣ እንጎብኝው" አልኩ።" ዛሬ ግን ክፍት ነው፣ እናም በወቅቱ እጅግ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር" ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።  "የአውጎስጢኖስ ማህበረሰብ እና እዚህ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ያሉበት፣ እግዚአብሔርን የሚያወድሱ፣ በዚህ ቤተክርስቲያን እና በማህበራዊ አገልግሎቷ አማካኝነት ማህበረሰብን፣ ተቀባይነትን የሚያገኙ እና ውህደትን የሚያገኙ ቤተክርስቲያን ማግኘት እንዴት ውብ ነው! ሁላችሁንም በእውነት አመሰግናለሁ!"

ህይወት ብቸኛ ትርኢት አይደለም።

ሬንዞ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ካቀረባቸው ጥያቄዎች መካከል ስለ እግር ኳስ አንዱ ነበር። ቴኒስ ተመራጭ ስፖርታቸው እንደሆነ ቢያምኑም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በፔሩ ያሳለፏቸውን ዓመታት በደስታ ተናግረው፣ የአካባቢውን የእግር ኳስ ቡድኖችን ተከትለው ከዘረዓ ክህነት ተማሪዎች ጋር መጫወታቸውን ገልጸዋል።

"ትንሽ ስፖርት ለሁሉም ሰው ጥሩ ነው" ብለዋል። "ጤንነታችንን በአካል፣ በአእምሮ እና በነፍስ ለመጠበቅ መንገዶችን መፈለግ አለብን" ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እግር ኳስን ለሕይወት እንደ ምስል ተጠቅመዋል። "ሕይወት በራሳችን ላይ የምናበራበት ውድድር አይደለም" ብለዋል። "እንደ ቡድን የሚጫወት ነገር ነው" ያሉ ሲሆን እናም በጣም ተሰጦ ያለው ተጫዋች እንኳን ሌሎችን ለማሳተፍ ፈቃደኛ ካልሆነ በመጨረሻ እንደሚወድቅ ሲገልጹ፣ ቅዱስነታቸው ወደ በጎ ፈቃደኞች እና የካሪታስ ሰራተኞች ሐሳባቸውን በማዞር፣ የትብብር እና የአገልግሎት መንፈስ ስላሳዩ አመስግነዋል፣ "አንድ ሰው ኮከብ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ኳሱን ካላካፈለ ሌሎች ወደ ጨዋታው እንዲገቡ አይፈቅድም፣ እና ምናልባትም ሊሸነፍ ይችላል" ብለዋል።

እያንዳንዱ ልጅ የእግዚአብሔር ሕልም ነው

ሬንዞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ገና በለጋ ዕድሜው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመሆን ሕልም ነበራቸው ወይ የሚለውን ለማወቅ በመፈለግ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን "ስለዚህ ጉዳይ አስቤ አላውቅም" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ፈገግ ብለው መለሱ፣ የሚያስታውሱት ነገር ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር ለመስጠት የመጀመሪያ ፍላጎታቸው እንደሆነ አክለው ገልጸዋል።

"ከልጅነቴ ጀምሮ ሕይወቴን ለእግዚአብሔር የመወሰን ፍላጎት ተሰማኝ" ሲሉ ቀስ በቀስ ወደ ክህነት እና ወደ ቅዱስ አጎስጢኖስ ማሕበር ሥርዓት የሚመራውን መንገድ እንዳገኙ አስረድተዋል።

"እያንዳንዱ ልጅ የእግዚአብሔር ሕልም ነው። አንተም ሬንዞ አንተም የእግዚአብሔር ሕልም ነህ" ሲሉ ቅዱስነታቸው የተናገሩ ሲሆን ልጆች ራሳቸውን የበለጠ አስፈላጊ ጥያቄ እንዲጠይቁ ሐሳብ አቅርበዋል፣ የኢየሱስ ወዳጆች መሆን ይፈልጉ እንደሆነ ቅዱስነታቸው ጥያቄ አንስተዋል።

"ከኢየሱስ ጋር ወዳጅነት ደስታን ይሰጠናል፣ ነፃ ያደርገናል እንዲሁም እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ያዘጋጀልንን ጥሪ እና መንገድ ደረጃ በደረጃ እንድናውቅ ይረዳናል" ብለዋል።

በተስፋ መከራን መጋፈጥ

በሬንዞ የቀረበው በጣም ፈታኝ ጥያቄ መከራን እና መጥፎ ነገሮች በአንዳንድ ሰዎች ላይ ለምን እንደሚደርሱ እና በሌሎች ላይ ለምን እንደማይደርሱ የምያወሳ ጥያቄ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ቀላል መልስ እንደሌለ አምነዋል። ስለ ክርስቶስ ሕይወት ሲያሰላስሉ፣ ኢየሱስ “መልካም እያደረገ” እንደነበር እና ሆኖም ግን እንደተጣለ፣ እንደተፈረደበት እና እንደተሰቀለ አስታውሰዋል። ነገር ግን ታሪኩ በዚህ አላበቃም” ብለዋል። “በሦስተኛው ቀን ተነስቶ ክፋትንና ሞትን ድል አደረገ” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ለክርስቲያኖች እንደገለጹት፣ መከራ የመጨረሻው ቃል አይደለም። “መከራ ቢኖርም፣ እግዚአብሔር ልጆቹን ፈጽሞ አይጥልም” በማለት በቦታው የነበሩት ሰዎች ክርስቶስ በእያንዳንዱ ፈተና ውስጥ አብሯቸው እንዲሄድ እና ከሥቃይና ከኪሳራ በላይ ዘላለማዊ ደስታን እንደሚያዘጋጅ እንዲያምኑ አበረታተዋል።

አያቶች ብቻቸውን መተው የለባቸውም

የሬንዞ ሌላ ጥያቄ አያቶችን የሚዳስስ ሲሆን "በፍፁም ብቻቸውን መተው የለባቸውም" ብለዋል። ወላጆቻቸው ሲሰሩ እና እምነትን፣ ፍቅርን እና እሴቶችን ለወጣት ትውልዶች በጸጥታ ሲያስተላልፉ ለልጅ ልጆቻቸውን የሚንከባከቡ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን አያቶችን አመስግነዋል።

"ብቸኝነት እና መተው በአረጋውያን ሕይወት ውስጥ የተለመደ እንዲሆን አንፍቀድ። ይህ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የእንክብካቤ ኃላፊነት ከቤተሰብ ትስስር በላይ እንደሚዘልቅ እና የመረሳት አደጋ ላይ የሚወድቁትን እያንዳንዱን አረጋዊ ሰው እንደሚያቅፍ ጠቁመዋል።

ልብን የሚፈውስ ይቅርታ

ስለ ይቅርታ ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኢየሱስን ትምህርት አስታውሰዋል፣ ምንም እንኳን "ይቅር ማለት የተሳሳተው ነገር ትክክል ነው ማለት አይደለም" ሲሉ አስረድተዋል፣ "አንድ ሰው ጉዳት ማድረሱን እንዲቀጥል መፍቀድ ማለት አይደለም" ብለዋል።

ይቅርታ ማለት ጥላቻ በልብ ከመያዝ ይከላከላል እና ወደ ፈውስ እና ሰላም መንገድ ይከፍታል። "ይቅር ስንል፣ የሰቀሉትን ይቅር ያለውን የኢየሱስን ምሳሌ እንከተላለን" ብለዋል።

በጎነት የክርስቶስን ፊት ያሳያል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትኩረታቸውን በቅዱስ አጎስጢኖስ ማዕከል ውስጥ ወደ ተሰበሰቡት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ተልዕኮ አዙረው፣ ለሥራቸውም ምስጋናቸውን በማቅረብ የቅዱስ አውጎስጢኖስን መንፈሳዊነት ተጠቅመዋል፣ እናም የክርስትና ሕይወት የሚጀምረው በሰው ጥረት ሳይሆን በጸጋ እንደሆነ አስታወሷቸው።

"ክርስቲያን መሆን ከሁሉም በላይ ስጦታ እና ጸጋ ነው" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ተናግረዋል።

ከዚያ ጸጋ ሌሎችን የመውደድ እና ክርስቶስን የመለየት ኃላፊነት የሚፈሰው በሚሰቃዩ ሰዎች ውስጥ ነው። "ክርስቲያን ደግ እና ገር ከመሆኑ በተጨማሪ ርኅሩኅ፣ ራስ ወዳድ ያልሆነ ፍቅር እና የሌሎችን መልካም ነገር መፈለግ አለበት" ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በባርሴሎና ጠቅላይ ቤተ ክርስቲያን የተከናወነውን ሥራ አድንቀው የቤተክርስቲያኒቱ የበጎ አድራጎት ተልእኮ በተለይ አጣዳፊ የሚሆነው ኅብረተሰቡ ብዙውን ጊዜ የሰውን ልጅ ቅዱስ ክብር ችላ ብሎ በሚታይበት ወቅት እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ይህ ክብር በሀብት፣ በችሎታ ወይም በማህበራዊ ደረጃ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ እና በእርሱ የተወደደ በመሆኑ ላይ መሆኑን አጥብቀው ተናግረዋል፣ "የሰው ልጅ የቤተክርስቲያኒቱ ተግባር ማዕከል ነው" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቁሳዊ ድጋፍን አስፈላጊነት ሲገነዘቡ፣ በድህነትና በመገለል የሚኖሩ ሰዎች ለመንፈሳዊ አጃቢነትም እንደሚራቡ በድጋሚ ተናግረዋል። "ቁሳዊ እርዳታና የሞራል ድጋፍ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር፣ ጓደኝነቱ፣ በረከቱ፣ ቃሉ፣ በቅዱሳት ምስጢራትና በእምነት የእድገትና የብስለት መንገድ ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር ለመገናኘት ከተሰለፉት ብዙ ሰዎች ጋር የምስጋና ቃላትን ለመለዋወጥና ሰላምታ ለመስጠት ጊዜ ከመውሰዳቸው በፊት፣ የበጎ አድራጎት ሠራተኞቹ ከመንፈሳዊ አባቶቻቸው ጋር በመሆን ተልእኳቸውን እንዲቀጥሉ አበረታተዋል፣ "የክርስቲያን ተስፋ ታማኝ ምስክሮች" እንዲሆኑ እና በአገልግሎታቸው የእግዚአብሔርን መንግሥት ፍትህና ሰላም እንዲገልጹ አሳስበዋል።

11 Jun 2026, 15:01