ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ‘የተደበቀውን፣ የፍቅር የልብ ምት’ አዳምጡ ማለታቸው ተገለጸ።

በግራን ካናሪያ በተካሄደው መስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “በሁሉ ቦታ የሚገኝ እና እረፍት የሌለው ‘እኔ’ የሚል ጩኸት” እንዳይሰማ ያስጠነቅቃሉ፣ እና ወደ ደሴቲቱ በደረሱ ጊዜ ህይወታቸውን ላጡ ስደተኞችን በጸሎት አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሐሙስ ሰኔ 4/2018 ዓ.ም ምሽት በግራን ካናሪያ ስታዲየም መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉ ሲሆን ስለ ፍቅር፣ ስቃይ እና ትህትና በተመለከተ ቅዱስነታቸው ትኩረት ሰጥተው ተናግረዋል።

ግራን ካናሪያ፣ ከምዕራብ አፍሪካ የባህር ዳርቻ ርቃ የምትገኘው የስፔን ደሴት፣ በአውሮፓ አዲስ ሕይወት ለሚፈልጉ ስደተኞች ዋና የመድረሻ ቦታ ናት።

በመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ ሥርዓቱ ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ይህች ምድር የምትመሰክራቸው ስቃዮች” ማስታወስ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፣ እና አድማጮቻቸው “በባህር ላይ ሕይወታቸውን ላጡ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን” አብረው እንዲጸልዩ ጋብዛቸዋል።

‘ለልብ ስቃይ’

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ መስዋዕተ ቅዳሴውን የጀመሩት ከኦሪት ዘዳግም መጽሐፍ የተወሰደውን እና እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ያለውን “ቅድመ ሁኔታ የሌለው” ፍቅር የሚገልጽ የመጀመሪያውን የመስዋዕተ ቅዳሴው ንባብ ላይ በማሰላሰል ነበር።

ይህ ፍቅር ነው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት፣ “በመላው ማንነታችን ውስጥ የሚዘልቅ” እና “ለነፍስ እሳት፣ ለአእምሮ ብርሃን፣ ሰላም፣ ለነፃነት የማይበገር ግፊት… የልብ መታደል” ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንደተናገሩት፣ የራሳችን የፍቅር ጥሪ የተመሠረተው በዚህ “ያለ ቅድመ ሁኔታ” መለኮታዊ ፍቅር ውስጥ ነው ብለዋል።

መንፈሳዊ፣ አእምሯዊ እና አካላዊ እድገት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከዚያም ከዮሐንስ የመጀመሪያ መልእክት የተወሰደውን የዕለቱን ሁለተኛ ንባብ ለማጤን ሐሳባቸውን ወደ እዚያው ያዞሩ ሲሆን በዚህም ስለሁኔታው እንደተናገሩት፣ በሐዋርያው ​​ቃል፣ “በእናትነት ርኅራኄ የሚሰቃዩትን ለመቀበል” ግብዣ አለ ብለዋል።

ይሁን እንጂ ርኅራኄያችን በቁሳዊ እርዳታ ላይ ብቻ መቆም የለበትም፣ ይልቁንም “መንፈሳዊ፣ አእምሯዊ እና አካላዊ” እድገትን ለማበረታታት ጥረት ማድረግ አለበት ብለዋል።

‘እረፍት የለሽ’

የቀኑ መስዋዕተ ቅዳሴ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ የተከበረበት እለት ነበር፣ ስብከታቸውን ቅዱስነታቸው ሲቀጥሉ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የክርስቶስን ልብ ልዩ ባህሪ ማሰላሰል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፣ ይህም ትሕትና የተሰኘው እንደ ሆነ አሳውቀዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “በአድናቆት የተሞላ፣ በሁሉም ቦታ የሚገኝ እና እረፍት በሌለው ‘እኔ’ በተሰኘው ግላዊ  ጩኸት በመደነቃቸው” ብዙዎች ዛሬ “በራሳቸው ውስጥ ለመስማት የሚያስፈልገው ጸጥታ የላቸውም… ይህም የተደበቀ፣ ልብ የሚመታ የፍቅር ልብ ነው” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ኢየሱስ መፍትሄውን ያሳየናል፡- “ከሚከፋፍሉን የትዕቢት መሠረቶች መውረድ እና አንድ በሚያደርገን ትህትና ውስጥ ራሳችንን ማየት አለብን” ሲሉ አክለው ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

12 Jun 2026, 15:54