ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳ ሊዮ፥ ቅዱስ አጎስጢኖስ ወደ ውስጣች የመመለስ አስፈላጊነት እንደሚገልጽ ተናገሩ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ቅዳሜ ሰኔ 13/2018 ዓ. ም. ጣሊያን ውስጥ ቅዱስ አጎስጢኖስ ወደ ተቀበረበት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ጎብኝት አድርገዋል። ቅዱስነታቸው በሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ወቅት በውስጣዊነት፣ በተስፋ ቢስነት እና የዘመኑን ምልክቶች በማንበብ አስፈላጊነት ላይ በማሰላሰል ለምዕመናን ቃለ-ምዕዳን አስምተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የሰሜን ጣሊያን ከተማ ወደ ሆነች ፓቪያ በመጓዝ ቅዱስ አጎስጢኖስ በተቀበረበት በ8ኛው ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ጉብኝት አድርገዋል።

ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ባደረጉባት ፓቪያ፥ የሰፊው ሎምባርዲ ክልል ካቶሊካዊ ምዕመናን፣ ካኅናት፣ ገዳማዊያን እና ገዳማውያት፣ የዘርዓ ክኅነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ብጹዓን ጳጳሳት ተገኝተዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ወደ ሥፍራው ከደረሱ በኋላ በቅዱስ አጎስጢኖስ ቅዱስ አጽም ፊት የቀረበውን አጭር ጸሎት ከመሩ በኋላ ለምዕምናን ንግግር አድርገዋል።

አፍራሽ አመለካከትን ማስወገድ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ “የፓቪያ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ ባሕል ያላት ብትሆንም ነገር ግን የዛሬ ጊዜ ምልክቶችን ማንበብ ችላለች” ብለው፥ የአሁኑን ጊዜ በጥንታዊ የእምነት ዓይን የሚመለከቱ ሰዎች ወደ ጥልቅ እውነታ መድረስ እንደሚችሉ እና ይህም በሚያጋጥሟቸው ችግሮች ተስፋን እንዳይቆርጡ ያስችላቸዋል” ብለዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲመስሉ ምዕመናኑን ያበረታቱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ “በችግሮች እና መግባባት በጠፋበት ጊዜ ውስጥ እንደ ወፎች እና አበቦች ቀላል በሆኑ ፍጥረታት ውስጥ መለኮታዊ ዕርዳታን ማየት ችለዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

አዳዲስ መዋቅሮች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በፓቪያ የሚገኙ ቁምስናዎችን አስቸኳይ ዕርዳታ እና ጥረት የሚጠይቁ ጊዜያት እንደሚያጋጥሟቸው በማመን፥ ነገር ግን እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ማቅረብ አስፈላጊ እንደሆነ አፅንዖት በመስጠት፥ ይህ የማዕዘን ድንጋይ ከሌለ ሥራዎቻችንን የመበታተን እና በራሳችን ጥረት ላይ ብቻ የማትኮር አደጋ ሊያጋጥመው እንደሚችል ተናግረዋል።

ቤተ ክርስቲያኒቱን አስፈላጊ ወደ ሆነው የለውጥ ሂደት ማድረስ ያለፈውን መዋቅር እና ደህንነት መተው ሊሆን እንደሚችል ተናግረው፥ በመሆኑም በፓቪያ ያለች ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ውስጥ ያለው መልካም ነገር በሎምባርዲ ክልል በአካባቢው ማኅበረሰቦች ውስጥ ትልቅ ሚና መጫወት የቀጠሉ የወጣቶች ማዕከላት እንዲሁም እንደ ሲኖዶሳዊነት ያሉ የቅርብ ጊዜ ፅንሰ ሃሳቦችን ተግባራዊ ማድረግ መቀጠሏን ተናግረዋል።

ቅዱስ አጎስጢኖስ እና ወደ ውስጣችን የመመለስ አስፈላጊነት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ምሳሌነቱ በከበረ ብርሃን የሚበራው ቅዱስ አጎስጢኖስ በዚህ ሂደት ውስጥ መመሪያ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል። የአራተኛው ክፍለ ዘመን የሰሜን አፍሪካ ቅዱስ ከሁሉም በላይ የውስጣዊነት ዋጋ እና ቀዳሚነት ሊያስተምረን እንደሚችል በመጠቆም “ከራስህ አትውጣ” የሚለውን የቅዱስ አጎስጢኖስ እውነተኛ ሃይማኖት ጠቅሰው፥ “ወደ ራሳችሁ ተመለሱ፥ እውነት በውስጣዊ ማንነት ውስጥ ትገኛለች” ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በንግግራቸው ማጠቃለያ፥ ይህ መልዕክት ዛሬ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመው፥ ራሳችንን ሳናጣት ወደ ውስጣችን በመመለስ ሕይወታችንን ሊመራ የሚችል ትርጉምን የመፈለግ እና የማግኘት ዓለም አቀፋዊ ፍላጎት መኖሩን አስረድተዋል።

22 Jun 2026, 16:25