ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን ከአሜርካ የካቶሊክ ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጅ መሪዎች የልዑካን ብዱን ጋር በተገናኘበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን ከአሜርካ የካቶሊክ ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጅ መሪዎች የልዑካን ብዱን ጋር በተገናኘበት ወቅት  (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ወደ ክርስቶስ መምራት አለባቸው አሉ!

የአሜሪካን የካቶሊክ ኮሌጅ ፕሬዚዳንቶች እና ካህናት በቫቲካን ተቀብለው ሲያነጋግሩ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች የመማር ፍቅርን ብቻ ሳይሆን ለክርስቶስ፣ “እውነት” ጥልቅ ፍቅርን ማዳበር እንዳለባቸው አክለው ገልጸዋል፣ ይህ ከሌለ ተማሪዎች እውነትን ለመለየት እና ህይወታቸውን በዚሁ መሰረት ለመቅረጽ ብዙም ዝግጁ እንደማይሆኑ አሳስበዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ውስጥ ለእውነት እውነተኛ ፍቅርን - እና ምሁራዊ እውነትን ብቻ ሳይሆን ክርስቶስ ራሱ የሆነውን እውነት (ዮሐንስ 14:6) እንድያውቁ - ሰዎች እውነትን ለማወቅ እና ህይወትን በዚሁ መሰረት ለማላመድ የሚያስፈልገውን ጥረት ለማድረግ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ማድረግ ተገቢ ነው" ማለታቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ረቡዕ ጠዋት ግንቦት 26/2018 ዓ.ም በሮም እ.አ.አ የ2026 ዓ.ም ትምህርታዊ ጉባኤ ላይ ከዩናይትድ ስቴትስ የተውጣጡ የካቶሊክ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር ልዑካን ቡድንን ባነጋገሩበት ወቅት ይህንን ነጥብ አንስተው አብራርተዋል።

ቅዱስ አባታችን "የካቶሊክ ተቋማት የተጠሩት የክርስትና ራዕይ እያንዳንዱን ሥነ ሥርዓት እና እያንዳንዱን መስተጋብር የሚሸፍንበት ሕያው አካባቢ እንዲሆኑ ነው" ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲዎቹን ፕሬዚዳንቶችና ዳይሬክተሮችን በማበረታታት፣ “እንደ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የእናንተ እውነተኛነት ሕያው ወንጌልን በማስተላለፍ ረገድ በእርግጥ ይረዳል፣ ይህም በአደራ የተሰጡዋችሁን ሰዎች ጌታን በእውነት እንዲያገኙ እና እውነት ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን አንድነት ያለው ራዕይ በካቶሊክ እምነት ውስጥ እንዲያገኙ እንድትረዱ ያግዝችሁሃል” ብለዋል።

የተገደበ አመለካከት ያላቸው ባለሙያዎች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ልባቸው “በእውነት ውበት እና በእግዚአብሔር በተፈጠረ እና በክርስቶስ በተዋጀው የሰው ልጅ ግርማ የበለጠ እንዲማረክ” ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እ.አ.አ በግንቦት 25 በታተመው “'ማኝፊካ ሂውማኒታስ' የሰውን ልጅ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመን ለመጠበቅ” በሚለው ጳጳሳዊ መልእክት መሠረት በዛሬው ዓለም የካቶሊክ ትምህርት ወሳኝ ጠቀሜታን በተመለከተ ለአስተማሪዎቹ ሐሳብ አካፍለዋል።

በመጀመሪያ፣ የትምህርት ዓለም በአሁኑ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የእውቀት መከፋፈል እየገጠመው መሆኑን አውስተዋል።  

በአንድ የተወሰነ የጥናት መስክ ባለሙያ የሆኑ ሰዎችን ማግኘት ቀላል ቢሆንም፣ ከእነዚህ ግለሰቦች ውስጥ ብዙዎቹ "በሕይወታቸው ውስጥ አቅጣጫ ለማግኘት ይታገላሉ" እና "ብዙውን ጊዜ የተለያዩ የእውቀት ዘርፎችን ብቻ ሳይሆን የሕይወትን የተለያዩ ገጽታዎች እና የሰውን ልብ ውስጣዊ ምኞቶች አንድ ለማድረግ የሚያስችል ዓለም አቀፍ የእውነታ ራዕይ የላቸውም" ብለዋል። የካቶሊክ ትምህርት በዚህ ረገድ የሚጫወተው ሚና ልዩ ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ተማሪዎች እውነት የሆነውን ኢየሱስ እንዲወዱ እርዷቸው

ቅዱስ አባታችን ወጣት ወንዶችና ሴቶች በኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩት የተወሰነ ዲግሪ ለማግኘት እንደሆነ ተገንዝበዋል፣ ብዙውን ጊዜ ወደፊት በሚመጡ የሥራ አመለካከቶች ተነሳስተው ነው፣ ስለዚህ አስተማሪዎች "እውነትን መፈለግና መውደድ፣ የሕይወትን ትርጉም ማሰላሰል እና የእያንዳንዱን ሰው ክብር መገንዘብ እንዲችሉ የእውቀትን ፍላጎት የመምራት ክቡር ተግባራቸውን እንዲቀበሉ" አበረታተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ይህ ቀላል ሥራ አይደለም" ብለው አምነዋል፣ ነገር ግን ተማሪዎች ለክርስቶስ፣ ለትምህርት ግኝቶቻቸው እና ህይወታቸውን ለመኖር ያላቸውን ፍቅር እንዲያገኙ መርዳት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

'ጤናማ አስተምህሮ' ለሕይወታቸው እና ለዩናይትድ ስቴትስ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ቁልፍ ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የቅርብ ጊዜ የቴክኖሎጂ ግስጋሴዎች ለትምህርት ዓለም በርካታ ተግዳሮቶችን እንዴት እንደሚፈጥሩ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በዚህ ረገድ "የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በብዛት መጠቀም የተማሪዎችን ስራ ለመገምገም አስቸጋሪ ያደርገዋል፣ ይህም አስተማሪዎች እንዲከባክቧቸው በአደራ የተሰጧቸውን ሰዎች የተቀናጀ የሰው ልጅ እድገት ለማረጋገጥ ዘዴዎቻቸውን በፈጠራ ተግባራት እንዲያስተካክሉ ይጠይቃል፣ ይህ ለመምህራን የበለጠ ስራ ቢጠይቅም፣ በዚህ መልኩ፣ ለወደፊት ትውልዶች ትምህርት በልግስና መዋለ ነዋይ ፈሰስ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን አለብን" ብለዋል።

"ወጣት ወንዶችና ሴቶች በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች አዎንታዊ በሆነ መልኩ መሳተፍን መማር፣ በተመሳሳይ ጊዜ ያስፈልጋል" ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን "እግዚአብሔር የሰጣቸውን ክህሎቶች እና ችሎታዎች የማመዛዘን፣ በጥልቀት የማሰብ እና እውቀትን በትውስታ ላይ የማዋል ችሎታቸውን በማዳበር፣ በዚህም የሚመጣውን ዓለም በኃላፊነት ስሜት እንዲቀርጹ ያዘጋጃቸዋል" ብለዋል።

ስለዚህ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አክለው እንደ ገለጹት ከሆነ አስተማሪዎቹ የቤተክርስቲያኗን የወንጌላዊነት ተልእኮ መወጣታቸውን ሲቀጥሉ፣ "ተማሪዎች በቤተክርስቲያናችሁ ውስጥ ሁልጊዜ ለቤተክርስቲያኗ በአደራ የተሰጠውን ጤናማ አስተምህሮ ማግኘት እንደሚችሉ፣ ይህም ለህይወታቸው ብቻ ሳይሆን ለአገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እውነተኛ እና ዘላቂ መሠረት ሆኖ ያገለግላል" የሚለውን ተስፋቸውን ከገለጹ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

03 Jun 2026, 15:41