ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ  በካስተል ጋንዳልፎ የጳጳስ እረፍት ማድረጊያ ሥፍራ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በካስተል ጋንዳልፎ የጳጳስ እረፍት ማድረጊያ ሥፍራ   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ 'የፍቅር ሥልጣኔ' መገንባት ድፍረት እና ትሑት አመራርን ይጠይቃል ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በመጀመሪያው 'የቦርጎ ላውዳቶ ሲ' (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) ስብሰባ ላይ ለተሳታፊዎች አዲስ የሞራል አመራር ሞዴል እንዲያሳድጉ እና እያደገ እያሽቆለቆለ በሚሄደው የሰብአዊነት ዝቅጠት ፊት 'የፍቅር ሥልጣኔ' ("የፍቅር ስልጣኔ" የሚለው ቃል በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ የተፈጠረ እና በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በስፋት የተዘጋጀ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ ፅንሰ-ሀሳብ ነው። ይህ ጽንሰ-ሀሳብ ከራስ ወዳድነት፣ ከቁሳዊነት ወይም ትርፍ ለማግኘት በከፍተኛ ሁኔታ መጓጓት እና ትርፍን እንደ አምላክ ከማምለክ ይልቅ ባልተገደበ የበጎ አድራጎት፣ በፍትህ እና በሰው ልጅ ውስጣዊ ክብር ላይ የተገነባ፣ ባህል እና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብን ይገልጻል) እንዲገነቡ እንዲያግዙ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አርብ ዕለት ሰኔ 12/2018 ዓ.ም በ'ቦርጎ ላውዳቶ ሲ' ውይይቶች የመጀመሪያ ቀን ላይ ተሳታፊዎችን በደስታ ተቀብለዋል። ተሳታፊዎቹ ዛሬ የሰው ልጆች ከሚያጋጥሟቸው በጣም አንገብጋቢ ጉዳዮች መካከል አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (የሰው ሰራሽ አስተውሎት) እና በሰው ልጅ ክብር፣ ጤናማ እርጅና፣ የስፖርት ዲፕሎማሲ እና የአካባቢ ዘላቂ ልማት ጋር የተያያዙ ለሁለት ቀናት ውይይት ለማድረግ በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው ቦርጎ ላውዳቶ ሲ' ተሰብስበው ነበር።

ይህ ተነሳሽነት በሮም ከተማ አከባቢ በሚገኘው በካስቴል ጋንዶልፎ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የእረፍ ማድረጊያ ስፍራ ውስጥ የተቋቋመው የቦርጎ ላውዳቶ ሲ ሰፊ ተልዕኮ አካል ሲሆን ይህም እ.አ.አ በ2015 ዓ.ም በቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ተነሳሽነት እ.አ.አ በ2015 ዓ.ም በላቲን ቋንቋ 'ላውዳቶ ሲ' (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) በሚል አርዕስት ይፋ ካደረጉት ጳጳሳዊ መልእክት ተመስጦ የተቀናጀ የስነ-ምህዳር ማዕከል ሆኖ የተቋቋመው የቦርጎ ላውዳቶ ሲ' ሰፋ ያለ ተልዕኮ አካል ነው። ውይይቶቹ ሥነ ምግባራዊ አመራር ለሥነ-ምህዳር፣ ለማህበራዊ እና ለኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንዴት አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚችል ለመመርመር ከተለያዩ አገሮች እና ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎችን፣ ሊህቃን እና መሪዎችን አሰባስበዋል።

የሞራል አመራርን እንደገና ማሰብ

በስብሰባቸው መደምደሚያ ላይ ለተሳታፊዎች ንግግር ሲያደርጉ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ስብሰባውን “ዛሬ የተሰበረ እና ታሪካዊ ሥር መሰረቶቹን የሚረሳ በሚመስል ዓለም ውስጥ የሞራል አመራርን ለማደስ እና እንደገና ለማሰብ የታለመ የሂደት የመጀመሪያ እርምጃ” ሲሉ ገልጸዋል።

በላቲን ቋንቋ "Magnifica humanitas" (አስደናቂ ሰብዓዊነት)  በተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት መጽሐፋቸው ውስጥ ከተዘጋጁት አንዳንድ ጭብጦች ላይ በማሰላሰል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዘመናዊ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም የውይይት አስፈላጊነትን በድጋሚ ተናግረዋል። “ለጋራ ጥቅም እና ለሁሉም ሰው ክብር ያለው ሕይወት ለማስተዋወቅ አዳዲስ መንገዶችን ለመለየት እንፈልጋለን” ብለዋል፣ “ከዘመናችን ካሉ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጋር ውይይት ለማድረግ፣ እነሱም በሰው ልጅ ክስተቶች፣ ጥያቄዎች እና ምኞቶች ውስጥ የምንካፈልባቸው” ጥሪያቸውን አስታውሰዋል።

ቅዱስ አባታችን ኅብረተሰቡን ከታሪካዊ ትዝታው ጋር ለመለያየት አደጋ ላይ የሚጥል እያደገ የመጣ “መንፈሳዊ እና ባህላዊ ዕውርነት” ብለው የጠሩትን አስጠንቅቀዋል። “ሐሰተኛ ተግባራዊነት” ብለዋል፣ “ከቀደመው ጊዜ የተለየ “አዲስ ፍጥረት” መመስረት የሚቻል ይመስል የታሪካችንን ሥሮች እንድንቆርጥ ያሳስበናል” ያሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም የሞራል መርሆዎችን የሚጠቅሱ እንኳን ወደ "ታሪካዊ ኒሂሊዝም" (ኒሂሊዝም ሕይወት ተጨባጭ ትርጉም፣ ዓላማ ወይም ውስጣዊ እሴት የሌለው እንደ ሆነ የሚገልጽ የፍልስፍና የዓለም እይታ ነው። "ኒሂል" ማለትም "ምንም" ማለት ነው፣ በሚለው የላቲን ቃል ላይ የተመሠረተ ሲሆን ሥነ ምግባር፣ እውነት እና እውቀት በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የተገነቡ እንዳልሆኑ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ የሰው ልጅ ፈጠራዎች ወይም ግንባታዎች እንደሆኑ ይጠቁማል) ወደ እዚህ አይነት አስተሳሰብ ሊወድቁ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፣ ይህም የሃያኛው ክፍለ ዘመን አሳዛኝ ክስተቶች ሊደገሙ እንደማይችሉ ቅዱስነታቸው እንደምያምኑ ገልጸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመቀጠልም ውይይቶቹ የተነሱት በቤተክርስቲያኒቱ የሲኖዶሳዊ ራዕይ ሲሆን የተለያዩ ድምጾችን በማሰባሰብ በጋራ ስጋቶች ዙሪያ አንድነትን በመፈለግ እንደሆነ አስተውለዋል። ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተዳደግ እና የልምድ ዘርፎች ቢኖሯቸውም ሥነ ምህዳራዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድሳትን ለማስፋፋት ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የቴክኖሎጂ ልማት ተግዳሮቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቴክኖሎጂ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ምክንያት የሚፈጠሩትን ሥነ ምግባራዊ ተግዳሮቶች በመመለስ ሁለት ተቃራኒ የኅብረተሰብ ራዕዮችን አነጻጽረዋል። "የባቢሎን ግንብ ለመገንባት በሚደረገው ፈተና ፊት ለፊት፣ ይህም በጣም ተጋላጭ በሆኑ ሰዎች ወጪ ትርፍን የሚያጣምም እና የሰብአዊነትን አደጋ የሚያባብስ ነው" ብለዋል፣ ክርስቲያኖች በምትኩ "ለአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ግንባታ፣ የፍቅር ሥልጣኔ" አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ እንዲጥሩ አሳስበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዲህ ዓይነቱ ሥልጣኔ የሚገነባው በታላላቅ ምልክቶች ሳይሆን በየቀኑ በታማኝነት እና በእንክብካቤ በምናደርጋቸው ተግባራት ነው። “የፍቅር ሥልጣኔ የሚመነጨው ከአንድ ወይም አስደናቂ ምልክት ሳይሆን ከሰብዓዊነት መገለል ለመከላከል እንደ መሸሸጊያ ሆነው ከሚያገለግሉት ጥቃቅን እና ጽኑ የታማኝነት ተግባራት ድምር ውጤት ነው” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ስብሰባውን በቦርጎ ላውዳቶ ሲ በሚገኘው የጳጳሳዊ የአትክልት ስፍራዎች ተፈጥሯዊ አካባቢ ማካሄዱ ያለውን ጠቀሜታ አጉልተው ገልጸዋል፣ ተሳታፊዎች የአካባቢውን ተሞክሮዎች ከዓለም አቀፍ ኃላፊነት ጋር ለማገናኘት ሲፈልጉ “ከፍጥረት ውበት - እና ከፈጣሪ ውበት” መነሳሳትን ማግኘት ችለዋል ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ተሳታፊዎቹ ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን በማቅረብ በካስቴል ጋንዶልፎ የተጀመረው ሂደት ወደፊት በሚደረጉ ግንኙነቶች እና ተነሳሽነቶች እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ በመግለጽ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

19 Jun 2026, 15:44