ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በስፔን ሕዝብ እምነትና ደስታ ተጽናንቻለሁ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ዘወት ረቡዕ እለት ከቫቲካን ሆነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደምያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በሰኔ 10/2018 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከሳምንት በፊት ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 06/2018 ዓ.ም በእስፔን "ቀና ብላችሁ ተመልከቱ" በሚል መሪ ቃል የጵጵስና ዘመንቻቸው 4ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት የተመለከተ አስተምህሮ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን "በስቴን ሕዝብ እምነትና ደስታ ተጽናንቻለሁ" ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእለቱ የተነበበው የእግዚአብሔር ቃል

"'እናንተም ገና አራት ወር ቀርቶታ፣ ከዚያም በኋላ መከር ይሆናል' ትሉ የለምን? እኔ ግን ቀና በሉና እርሻዎች ለመከር እንደደረሱ ተመልከቱ' እላችኋለሁ። እኔም ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክሁአችሁ፣ ሌሎች በሥራ ደከሙ፣ እናንተ ግን በድካማቸው ፍሬ ተጠቀማችሁ" (ዮሐንስ 4፡35፣ 38)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በወቅቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

ውድ ወንድሞችና እህቶች፣ እንደምን አረፈዳችሁ፣ እንኳን ደህና መጣችሁ!

ባለፈው ሳምንት ወደ ስፔን ባደረግኩት ሐዋርያዊ ጉብኝት ላይ አንዳንድ አስተያየቶችን ዛሬ ማካፈል እፈልጋለሁ፣ ማድሪድን፣ ባርሴሎናን፣ የሞንሴራትን ገዳም እና የካናሪ ደሴቶችን ጎብኝቻለሁ።

በአራት የአፍሪካ አገሮች ረጅም ጉዞ ካደረኩኝ በኋላ፣ በዚህ ጊዜ ጥንታዊ እና በጣም የበለፀገ የካቶሊክ ባህል ባለባት የአውሮፓ አገር ውስጥ ተገኘው። እናም ዛሬ በስፔን፣ ጉልህ የሆኑ ማህበራዊ እና ባህላዊ ለውጦችን ባሳየችው ሥፍራ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን በሁሉም ቦታ በጉጉት እና ለማዳመጥ ዝግጁ ሆነው እንደተቀበሉ ግልጽ ሆነ። ለዚህም፣ ለእግዚአብሔር እና ለመላው የስፔን ሕዝብ፣ ለንጉሡ እና ለሲቪል ባለሥልጣናት፣ ለጳጳሳት እና ለቤተክርስቲያን ማህበረሰቦች ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

የእግዚአብሔር ሕዝብ እምነታቸውን እና ፍቅራቸውን በደስታ በመግለጻቸው ትልቅ መጽናኛ ሰጥተውኛል። እኔ በበኩሌ፣ የሮም ጳጳስ እንደመሆኔ መጠን ሁልጊዜ ኅብረትን፣ ውይይትን እና በልዩነት አንድነትን በማበረታታት እያንዳንዱን የመከፋፈል እና የግጭት አይነት እንዲያሸንፉ ምእመናንን አበረታታኋቸው። ይህ የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ አገልግሎት ነው፣ ይህም በሐዋርያዊ ጉዞዎች ውስጥ የተወሰነ አገላለጽ የሚያገኝ አገልግሎት ነው፣ እያንዳንዱ ጊዜ ከጎበኘዋቸው አገሮች የቤተክርስቲያን እና ማህበራዊ ሁኔታዎች ጋር የሚስማማ ነው።

በስፔን ሁኔታ፣ በእያንዳንዱ ዕድሜና ሁኔታ ያሉ ሰዎች የሊቀ ጳጳሱን ጉብኝት ምን ያህል በጉጉት እንደሚጠባበቁ በደስታ ማየት ችያለሁ፤ በየትኛውም ቦታ በታላቅ ሞቅ ያለ አቀባበል የሚያደርጉልኝን ብዙ ሰዎች አግኝቻለሁ። ይህ እውነታ ቀላል ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው አልነበረም፣ እናም ሊታሰብበት የሚገባ ነው። በተፈጥሮው እንዲህ ዓይነቱ ተሳትፎ የስፔንን ሕዝብ እምነት ይገልጻል፤ በተመሳሳይ ጊዜ፣ እኔ እንደተናገርኩት፣ በእውነተኛና ጥልቅ መሠረት ላይ አንድነት የማግኘት ሰፊ ፍላጎትን እንደሚገልጽ አምናለሁ፣ ይህም በርዕዮተ ዓለምም ሆነ ከፊል ፍላጎቶች ላይ የተመሠረተ አይደለም። በመጨረሻው ትንተና፣ ክርስቶስ ብቻ ሊያረጋግጥ የሚችለው እና ወንጌል በሚያስፈልገው መንገድ “በባሕል ውስጥ በማካተት” በዚህ አማካኝነት በሰዎች ሕይወት ውስጥ ሊያስተላልፈው የሚችለው መሠረታዊ ሐሳብ መግለጽ ነው። መልእክቱ ለእነዚህ ፍላጎቶች ሙሉ በሙሉ መልስ እንዲመልስ ሊያደርገው ይችላል፤ ምክንያቱም የእውነት ፍለጋ እና የፍትህ ጥማት ስላለ ነው።

በማድሪድ እና በባርሴሎና፣ በታላቁ ካቴድራል እንዲሁም በዘመናዊ ስታዲየሞች ተሰብስበን ነበር። በሞንሴራት ገዳም የመቁጸሪያ ጸሎት ጸልየን ነበር። በሳግራዳ ፋሚሊያ (ቅዱስ ቤተሰብ)፣ ግርማ ሞገስ ያለው ምልክት፣ የድንጋይ እና የብርሃን ሲምፎኒ (የብርሃን እና የቀለማት ስብጥር) ለሁሉም ሰው የክርስቲያን ምስጢር የሚናገር ክብረ በዓልን አክብረናል። ይህ የጥንታዊ እና ዘመናዊ፣ የካቶሊክ ባህል እና የዘመናዊ ባህል መጋጠም የአውሮፓን ባህሪ፣ የማይገመተውን ሀብቷን፣ ያለፈ ታሪክ ሳይሆን ሕያው እውነታ እንደሆነ በገዛ ዐይኔ እንድገነዘብ አስችሎኛል። ዛሬ ባለው ዓለም አቀፍ ዓለም ውስጥ ወሳኝ ተግዳሮቶቹ ባሉበት ዓለም ውስጥ ኢንቨስት እንዲደረግ በጥንቃቄ መጠበቅ ያለበት ቅርስ ነው፣ ሰላም፣ የተቀናጀ ሥነ-ምህዳር፣ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ልማት እና ለሰው ልጅ ክብር አክብሮት መስጠትን ባካተተ መልኩ ማለት ነው። እነዚህ ፈተናዎች ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በግልጽ የተገነዘባቸው እና የሚቀጥለው የቤተክርስቲያን አስተምህሮ የመለሳቸው ናቸው፣ ይህም በቅርቡ በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ ዘመን የሰውን ልጅ ለመጠበቅ ያለመ በላቲን ቋንቋ  "ማኝፊካ ሂውማኒታስ" (አስደናቂ ሰብዓዊነት) የተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት ነው።

በተለያዩ ስብሰባዎች፣ የሊቀ ጳጳሱን ድምፅ፣ የዛሬውን የሰው ልጅ የተስፋ ወንጌልን ማዳመጥ አስፈላጊ መሆኑን፣ በማታለል የእድገት ሞዴል አሉታዊ ውጤቶች በጣም የተፈተነ መሆኑን ገልጫለሁ። ይህ ፍላጎት፣ ማዳመጥ በቻልኳቸው ብዙ ምስክርነቶች ውስጥ - አንዳንድ ጊዜ የሚንቀሳቀሱ፣ አንዳንድ ጊዜ የሚያንጹ ምስክርነቶች - ከሁሉም በላይ ደግሞ በትናንሽ ልጆች እና በድሆች ፊት ላይ ተገንዝቤያለሁ፤ በቁምስና ውስጥ የጻፈልኝን ደብዳቤ ያነበበ አንድ ልጅ፤ አንዳንድ የጥቃት ሰለባዎች፣ እንዲሰሙ የሚጠይቁ፤ በእስር ቤት ውስጥ ይጠብቁኝ የነበሩት የሕግ ታራሚዎች፤ በጭንቀት እና በምኞት የተሞሉ ወጣቶች፤ በካናሪ ደሴቶች ውስጥ በሚገኙ የመቀበያ ማዕከላት ውስጥ ያሉ ስደተኞች ጭምር ጎብኝቻለሁ።

በካናሪ ደሴቶች - በጉዟችን የመጨረሻ መዳረሻ- አጠቃላይ ግንዛቤ የተሰጠኝ እዚያ ነበር። በአንድ በኩል፣ በዚያ ደሴት ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ እና በሌላ በኩል ደግሞ፣ በአብዛኛው ከአፍሪካ የሚመጡ ብዙ ቁጥር ያላቸውን ከቀያቸው ተገደው የተሰደዱትን ስደተኞች የምትቀበል የአካባቢ ቤተክርስቲያን እውነታ ነው። የስደት ክስተት ውስብስብ እና ተፈጥሮአዊ እና የተቀናጁ የድርጊት እቅዶችን እንደሚፈልግ እናውቃለን። ነገር ግን ይህ ትርጓሜ የተለየና ሰፊ እይታን ይከፍታል፤ በዛሬው ዓለም ወንጌልን እንደገና እንድናነብ እንዴት እንደተጠራን እንድንረዳ ያስችለናል፣ የየባህሎቻችንን ስጦታዎች እርስ በርስ እንድንለዋወጥ፣ በተለይም የክርስቶስ መልእክት ፍሬያማነት ያስገኛቸውን ውጤቶች ማለት ነው። ከእነዚህ ፍሬዎች አንዱ በሰዎችና በሰዎች መካከል የሚደረግ ውይይት፣ በወንድማማችነት መንፈስ ውስጥ መገናኘት ሲሆን ይህም የእርስ በርስ እሴቶችን እንድናገኝና እንድናደንቅ ያስችለናል። ይህ መንገድ ቀላል አይደለም፤ በጎ ፈቃድንና የእግዚአብሔርን እርዳታ ይጠይቃል፣ ነገር ግን ወደ ፍቅር ስልጣኔ የሚመራው መንገድ ነው።

ውድ ወንድሞችና እህቶች፣ የዚህ ሐዋርያዊ ጉዞ መሪ ቃል በእስፓንሽ ቋንቋ “አልዛድ ላ ሚራዳ”፣ (ቀና ብላችሁ ተመልከቱ!) (ዮሐንስ 4፡35) የተሰኘው ነበር። እነዚህ የኢየሱስ ቃላት ለመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት የተነገሩት በሰዎችና በሕዝቡ መካከል የሕይወትን፣ የእውነትንና የሙላትን ፍላጎት እንዲያዩ ለማስተማር ነው። ጌታ እነዚህን ቃላት በመጀመሪያ ደግሞ ይነግረኛል፣ እናም በጸጋው በዚህ ጉዞ ውስጥም አጋጥሞኛል። ዛሬ ይህንን ግብዣ ከእናንተ ጋር ልጋራ እፈልጋለሁ፡ ዓይኖቻችንን እናንሳ! ጎረቤታችንን፣ ሰዎችን፣ ዓለምን “በእግዚአብሔር ዓይን” ማለትም በፍቅር፣ በአክብሮትና በርኅራኄ መመልከትን ከኢየሱስ እንማር።

በመጨረሻም፣ ለዚህ ​​ሐዋርያዊ ጉብኝት ስኬት የጸለዩትን ሁሉ፣ በተለይም በስፔን፣ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እጅግ ብዙ ለሆኑት አስተዋይ መነኮሳትን ማመስገን እፈልጋለሁ። በድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የበተንኳቸው ዘሮች ብዙ ፍሬ እንዲያፈሩ መጸለያችሁን ቀጥሉ። አመሰግናለሁ!

17 Jun 2026, 15:58