የር.ሊ.ጳ ሊዮ በስፔን የምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት፤ ከማድሪድ ወደ ባርሴሎና ተሻግሯል

በስፔን ሐዋርያዊ ጉዞአቸው በአራተኛው ቀን፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በማድሪድ የነበራቸውን ጊዜ አጠናቀው ወደ ሰሜን ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ባርሴሎና አጭር በረራ ከመጀመራቸው በፊት ከበጎ ፈቃደኞች ጋር መገናኘታቸው ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በስፔን ዋና ከተማ ቆይታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ረፋዱ ላይ በማድሪድ ውስጥ እርሳቸው የምያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማገዝ እና ለመርዳት ጊዜያቸውን ከሰጡ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመገናኘት አሳልፈዋል፣ እናም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእርዳታ ጥሪ በቀረበላቸው ጊዜ በፍጥነት ምላሽ በመስጠታቸው የተነሳ ለልግስናቸው ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን “እያንዳንዳችሁ የምትችሉትን ሰጥታችኋል፣ ልባችሁን፣ እጃችሁን፣ ሀሳባችሁን፣ ተሰጥኦአችሁን እና ፈገግታችሁን አቅርባችኋል” ብለዋል። “እግዚአብሔር ልብን ስለምያውቅ እግዚአብሔር ይክሳችኋል!” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሁሉም ክርስቲያኖች “የራስ ወዳድነትን እርሾ” ከውስጣቸው እንዲያስወግዱ ለሁሉም  አሳስበዋል። “ራስን አስልፎ መስጠት እንደ እርሾ ነው፣ ይህም የኅብረተሰቡን ሰብዓዊ፣ ሥነ ምግባራዊ እና መንፈሳዊ ገጽታዎችን ያሳድጋል፣ እና የ‘እግዚአብሔር ከተማ’ ልዩ አካል ነው” ብለዋል።

ክፍል ሁለት ይጀምራል

እኩለ ቀን አካባቢ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ወደ ሁለተኛው የሐዋርያዊ ጉዞ መዳረሻቸው ባርሴሎና ተጉዘዋል፣ በከተማው በቅዱስ መስቀል እና በቅዱስ ኡላሊያ ካቴድራል፣ በጎዳናዎች ላይ ከተሰበሰቡ ሰዎች ጋር ከተገናኙ በኋላ የቀትር ጸሎት ጀምረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ያላቸውን ፍቅር እና እውቀት በመጠቀም ስብከታቸውን በካታላን እና በስፓኒሽ ቋንቋዎች  አድርገው ሁሉም ሰው የሙሽራይቱን እና የአካሉን ምስሎች እንዲያሰላስል ጋብዘዋል። የባርሴሎና የካቶሊክ ማህበረሰብ - በተለያዩ ስጦታዎች፣ ቸርነት እና የግል ታሪኮች የበለፀገ - የሙሽራይቱን ምስል ምሳሌ እንዴት እንደሆነ አጉልተው ገልጸዋል።

ወጣቶች የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በባርሴሎና ያደረጉትን ንግግር ስያዳምጡ
ወጣቶች የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በባርሴሎና ያደረጉትን ንግግር ስያዳምጡ   (@Vatican Media)

ከዚህም በላይ፣ ሁላችንም በክርስቶስ አንድ አካል ነን። ልክ እንደ አካል፣ "ጠንካራ የሆኑ አባላት እና ደካማ የሆኑ አባላት አሉ።" አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ አባላት በስራቸው ይታያሉ፣ ሌሎች ደግሞ የበለጠ ተደብቀዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ ምክንያት፣ ሁሉም ሰው ለአንድነት ቅድሚያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። "ጠንካራዎች ነን ምክንያቱም አንድ ስለሆንን፣ እና አንድ ስለሆንን በአንድ መንፈስ ተንቀሳቅሰናል" ብለዋል።

ዘላለማዊ እንድንሆን ነው የተፈጠርነው

በባርሴሎና ባደረጉት የመጀመሪያ ምሽት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሉዊስ ኩባንያስ ኦሊምፒክ ስታዲየም ከወጣቶች ጋር ተገናኝተው ስለ መለወጥ፣ ስለአእምሮ ጤና፣ ስለ ዓመፅ እና ስለ ስቃይ ጭብጦች የሚያንፀባርቁ ሶስት ምስክርነቶችን አዳምጠዋል።

ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእያንዳንዳቸው ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ወስደው ነበር።

ዓለማዊ ስኬት ቢኖርም ስለ ባዶነት ለተናገረችው ፌራን ለተባለች ወጣት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “ለዘላለማዊነት የተፈጠርን ነን። ለዚህም ነው እያንዳንዱ የተወሰነ አድማስ፣ እያንዳንዱ እርምጃ፣ እያንዳንዱ ስኬት - እኛን እያረካን እያለ - ወደፊት እንድንገፋ የሚያደርገን እና ፍለጋችንን እንድንቀጥል የሚጋብዘን” ሲሉ ቅዱስነታቸው መልስ ሰጥተዋል።

ፌራን እና ሁሉም ወጣቶች “ውስጣቸውን እንዲመለከቱ” እና በህይወት ፈጣን ፍጥነት ከመዋጥ እንዲቆጠቡ ቅዱስነታቸው አሳስበዋል።

ከድብርት ጋር ያጋጠሟትን ትግል ለዘገበችው ካርሚና ለተባለች ወጣት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “ይህ ሰዎች ጤናማ ሚዛንን ለሚያደናቅፉ ጫናዎች፣ ግምቶች እና ውጥረቶች የሚዳርጋቸው የተወሰነ የእድገት ጽንሰ-ሀሳብ በጣም የተሳሳተ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት” እንዴት እንደሆነ አጉልተው ገልጸዋል።” በ“እነዚያ ጨለማ ሰዓታት” የክርስቶስን ሕማማት እንድትመለከት አበረታተዋል።

በመጨረሻም፣ በቤት ውስጥ ጥቃት፣ ሱስ እና ከቤተሰቧ በመለየት የምትኖረውን ወጣት ቼችሊያን በማነጋገር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሐሳባቸው ወደ  ይቅርታ አዙረዋል፣ “ይቅርታን - ውስጣዊ ቁስላችንን የሚፈውስ ኃይለኛ የክፋት መድኃኒት - እንደ ሂደት እና ጉዞ አካል አድርጎ ማየትን መማር አለብን” ብለዋል።

በሐቀኝነት አስቡ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለወጣቶች ከተናገሩ በኋላ ባደረጉት ስብከት፣ ዘመናዊውን ስፔን ተመልክተው ሁሉም ሰው ድህነትን፣ ማህበራዊ ክፍፍልን እና የባህል ለውጥን ጨምሮ በዛሬው ኅብረተሰብ ውስጥ ያሉትን ተግዳሮቶች በሐቀኝነት እንዲያስቡ አሳስበዋል፣ አብረው ምን ዓይነት የወደፊት ሕይወት መፍጠር እንደሚፈልጉ እንዲያስቡ ጠይቀዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ይህች አገር ለሁሉም ሰው የሚስማማ ቦታ ልትሆን ትችላለች፣ የእያንዳንዱ ሰው ሰብዓዊ ክብር የሚከበርበት እና ሁሉም ሰው በማንነቱ የሚወደድበት” ሲሉ አስረድተዋል።

10 Jun 2026, 16:23