2026.06.19 FOTO LEV 2026.06.19 FOTO LEV 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከመላው ዓለም ከሚመጡ ደራሲያን ጋር እንደሚገናኙ ተገለጸ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የቫቲካን አሳታሚ ድርጅት ምሥረታ 100ኛ ዓመት ለማክበር ከመላው ዓለም የሚመጡ ደራሲያንን ሰኔ 17/2018 ዓ. ም. በቫቲካን እንደሚቀበሉ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ የቫቲካን አሳታሚ ድርጅት የተመሠረተበት 100ኛ ዓመት ለማክበር ከመላው ዓለም የሚመጣ የደራሲያን ቡድንን ሰኔ 17/2018 ዓ. ም. በቫቲካን ለመቀበል ቀጠሮ ተይዟል።

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሚገናኙ ደራሲያን

ከቅዱስነታቸው ጋር ለመገናኘት ቀጥሮ ከተያዘላቸው ታዋቂ ደራሲያን መካከል ጆን ፎሴ፣ ማሪሊን ሮቢንሰን፣ ኤልዛቤት ስትሮውት፣ ኤሪክ-ኢማኑኤል ሽሚት፣ ቪቶሪዮ ሊንጃርዲ፣ ጁሊያ ናቫራ፣ ጆናታን ሳፍራን ፎየር፣ ኤንሪኮ ብሪዚ፣ ሶርጅ ቻላንዶን፣ ኮለም ሚካን፣ ዳኒኤል ሜንካሬሊ እና ሚርሴአ ካርትታሬስኩ ይገኙበታል።

እንዲሁም ከቫቲካን አሳታሚ ድርጅት የተወጣጡ አድሪያን ካንዲርድ፣ ኤራልዶ አፍኒቲ እና ፓውሎ ማላጉቲ እንደሚገኙ ታውቋል።

 

20 Jun 2026, 15:08