ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ተገናኙ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በቫቲካን በሚገኘው ሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤታቸው ተገናኝተዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሐሙስ ሚያዝያ 29/2018 ዕለት ወደ ጣሊያን ከደረሱ በኋላ ወደ ቫቲካን በማምራት ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ጋር በሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤታቸው ተገናኝተዋል።
የቅድስት መንበር መግለጫ ክፍል እንደገለጸው፥ በወዳጅነት የተሞላው ውይይት መካሄዱን ገልጾ፥ ሁለቱም አገሮች ማለትም በቅድስት መንበር እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ማደሳቸውን አስታውቋል።
ውይይታቸው በክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ሁኔታ ላይ የሃሳብ ልውውጥ ማድረግ እንደ ነበር ያስታወቀው መግለጫው፥ በተለይም በጦርነት፣ በፖለቲካዊ ውጥረት እና በአስቸጋሪ የሰብዓዊ ሁኔታዎች ውስጥ ስለሚገኙ አገራት እና ለሰላም ያለመታከት የመሥራት አስፈላጊነት በሚለው ላይ መሆኑን ገልጿል።
07 May 2026, 17:31
