ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ከካስቴል ጋንዶልፎ ማረፊያ ሲወጡ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ከካስቴል ጋንዶልፎ ማረፊያ ሲወጡ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል  

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ “ወንጌልን በማወጄ የሚተችኝ ሰው ካለ በእውነት ላይ ተመሥርቶ ይተቸኝ” ሲሉ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከካስቴል ጋንዶልፎ ማረፊያ ሲወጡ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፥ ቤተ ክርስቲያን የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎች የሚያስከትሉን ጥፋት ያለማቋረጥ የምትናገር መሆኗን አረጋግጠው፥ ወንጌልን በማወጃቸው ምክንያት ሊተቻቸው የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በእውነት ላይ ተመሥርቶ ሊተች እንደሚገባው አክለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ማክሰኞ ምሽት ከካስቴል ጋንዶልፎ ወደ ሮም ከመመለሳቸው በፊት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው አጭሩ ቆይታ፥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ራሳቸው ለተናገራቸው የቅርብ ጊዜ ትችቶች ምላሽ ሰጥተዋል።

“የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ወንጌልን ማወጅ እና ሰላምን መስበክ ነው” ያሉት ቅዱነታቸው፥ “ወንጌልን በማወጄን እኔን ሊተቸኝ የሚፈልግ ሰው በእውነት ላይ ተመሥርቶ ያድርግ” ሲሉ ተናግረዋል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ በካስቴል ጋንዶልፎ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ቤተ ክርስቲያን ስለ ኒውክሌር ጦር መሣሪያዎች አስከፊነት ሳታቋርጥ መናገሯን አስታውሰዋል።  

“ቤተ ክርስቲያን ለዓመታት ያህል ስለ ኒውክሌር ጦር መሣሪያዎች ስትናገር ስለመቆየቷ ምንም ጥርጥር የለውም” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ መያዝ ተቀባይነት እንዳለው ይቆጥራሉ፥ በዚህም ሁሉንም ካቶሊኮች አደጋ ላይ ይጥላሉ” በማለት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላቀረቡት ትችት ምላሽ ሰጥተዋል።

“የእግዚአብሔር ቃል ዋጋ ስላለው ብቻ እንደሚሰሙኝ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩት ቅዱስነታቸው፥ ለሐዋርያዊ መንበር ከተመረጡበት የመጀመሪያ ቅጽበት ጀምሮ እንዲሁም የመጀመሪያ ዓመት መታሰብያው እየተቃረበ ባለበት ጊዜ ሁሉ በግልጽ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” በማለት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ሐሙስ ሚያዚያ 29/2018 ዓ. ም. ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር የሚያደርጉትን ውይይት በተመለከተ፥ ጥሩ ውይይት እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸው፥ “ውይይቱ በእምነት እና በግልጽነት ከሆነ እርስ በርስ በሚገባ መግባባት ይቻላል” ብለዋል።

“የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የሚያነሷቸው ነጥቦች የዛሬዎቹ  እንደማይሆኑ አስባለሁ” ብለው፥ አክለውም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰጡትን አስተያየት በድጋሚ ጠቅሰዋል።

 

06 May 2026, 17:05