ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለአይስላንድ ፕሬዝዳንት ቶማስዶቲር በቫቲካን አቀባበል ሲያደርጉላቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለአይስላንድ ፕሬዝዳንት ቶማስዶቲር በቫቲካን አቀባበል ሲያደርጉላቸው   (@VATICAN MEDIA)

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአይስላንድ ፕሬዝዳንት ቶማስዶቲር ጋር መገናኘታቸው ተገለጸ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሚያዝያ 26/2018 ዓ. ም. የአይስላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ቶማስዶቲርን በቫቲካን ተቀብለው ተወያይተዋል። ፕሬዝዳንቷ ቀጥለውም ከቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት አባላት ጋርም መወያየታቸውን የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሰኞ ጠዋት የአይስላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ሃላ ቶማስዶቲርን በቫቲካን ተቀብለው የተወያዩ ሲሆን፥ ፕሬዝዳንቷ ቀጥለውም በቫቲካን የመንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግንኙነት ክፍል ዋና ጸሐፊ በሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በመመራት ከቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ጋር መገናኘታቸውን መግለጫው አክሏል።

በቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት በተደረገው ገንቢ ውይይት፥ በመካከላቸው ላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት አድናቆት የተሰጠው ሲሆን ይህም የአገሪቱ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የኅብረተሰቡን የጋራ ጥቅም በተለይም የወጣቶችን ጥቅም ለማስተዋወቅ ያበረከተችው አዎንታዊ አስተዋጽኦ ትኩረት ተጥቶታል።

ውይይቱ በተጨማሪም በክልላዊ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች በተለይም ግጭቶችን ለማስወገድ የጋራ ውይይት በሚጫወተው ሚና እና በሰላም ተስፋዎች ላይ ያተኮረ እንደ ነበር ተገልጿል።

 

05 May 2026, 11:50