ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ከዚህ በፊት በተገናኙበት ወቅት ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ከዚህ በፊት በተገናኙበት ወቅት  (@Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር እንደሚገናኙ ተገለጸ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ሐሙስ ሚያዝያ 29/2018 ዓ. ም. ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በቫቲካን እንደሚገናኙ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአንድ ዓመት በፊት የሐዋርያዊ መንበር ስልጣናቸውን በይፋ መጀመራቸውን ተከትሎ ከቀረበው የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት በኋላ ከሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ተገናኝተው እንደ ነበር ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው ሐሙስ ሚያዝያ 29/2018 ዓ. ም. ከረፋዱ አምስት ሰዓት ተኩል ላይ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በቫቲካን የሚገናኙ መሆኑን የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቋል።

የቅድስት መንበር መግለጫ ክፍል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከቅዱስነታቸው ጋር እንደሚገናኙ ያረጋገጠው እሁድ ዕለት የሚዲያ ዘገባዎች ከወጡ በኋላ ሲሆን፥ በዚህም መሠረት አቶ ማርኮ ሩቢዮ ወደ ቫቲካን የሚደርሱት ሐሙስ ዕለት ከረፋዱ አምስት ሰዓት ከሩብ ላይ እንደሚሆን ይጠበቃል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ቀደም ሲል ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ጋር እሑድ ግንቦት 10/2017 ዓ. ም. ከቀረበው የሐዋርያዊ አገልግሎታቸው መጀመሪያ መስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት በኋላ ሲሆን፥ በዚህ ዕለት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስም ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር ሰላምታ ተለዋውጠው እንደ ነበር ይታወሳል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በማግሥቱ ማለትም ሰኞ ግንቦት 11/2017 ዓ. ም. ከምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽ ግንኙነትን በማስመልከት ተወያይተው እንደ ነበር ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው ከፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋርም ይገናኛሉ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐሙስ ሚያዝያ 29/2018 ዓ. ም. ከአሜሪካ የልዑካን ቡድን ጋር በሚገናኙበት ዕለት ከፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ታስክ ጋርም እንደሚገናኙ እና ይህም ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ እንደሚሆን የቅድስት መንበር መግለጫ ክፍል አስታውቋል።

 

05 May 2026, 09:35