የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የጳጳሳዊ አካዳሚን ጎብኝት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የጳጳሳዊ አካዳሚን ጎብኝት   (@VATICAN MEDIA)

የቅድስት መንበር ዲፕሎማሲ ሚና ሰላምን፣ እውነትን እና ፍትህን ማገልገል መሆኑ ተነገረ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ በሮም የሚገኘውን ጳጳሳዊ አካዳሚን ጎብኝተው በምሥረታው 325ኛ ዓመት መታሰቢያ ላይም ተገኝተዋል። በአካዳሚው ጽሕፈት ቤት የሚያገለግል ካኅን ተልዕኮ ላይ በማሰላሰል ባደረጉት ንግግር፥ በዚህ አገልግሎት ላይ የተሰማራ ካኅን የሰላም መልዕክተኛ፣ ካቶሊካዊ ማኅበረሰብን ብቻ ሳይሆን መላውን የሰው ልጅ ቤተሰብ ለመንከባከብ የተጠራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ጳጳሳዊ አካዳሚውን ሰኞ ሚያዝያ 19/2018 ዓ. ም. በጎበኙበት ዕለት ባደረጉት ንግግር፥ የዲፕሎማት ካኅን ተልዕኮ የሰላም፣ የእውነት እና የፍትህ አገልግሎት ልዩ ጥሪ እንደሆነ ገልጸው፥ በአካዳሚው ያደረጉት ጉብኝት ከምሥረታው 325ኛ ዓመት መታሰቢያ ጋር የተገጣጠመ ሲሆን፥ ለሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ መንበረ ከመመረጣቸው በፊት አካዳሚውን ጎብኝተው እንደ ነበር ታውቋል።

በክርስቶስ የሚገኝ አንድነት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ አካዳሚው ላበረከተው ታሪካዊ እና ቆራጥ አገልግሎት እንዲሁም ደማቅ የምሥረታው በዓል ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከመላው ዓለም የተውጣጡ ካኅናት በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን አንድነት ለመገንባት ትህትና የሞላው ጥረት ማድረጋቸውን አስታውሰው፥ የመጡበት አካባቢ ሳይገድባቸው በኅብረት ሆነው ያበረከቱት አስተዋጽዖ የቅድስት መንበር ዲፕሎማሲያዊ አካል ባህሪን ልዩ ያደርገዋል” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአካዳሚው ፕሬዝደንት ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአካዳሚው ፕሬዝደንት ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ   (@VATICAN MEDIA)

ከልምምድ የሚገኝ ለውጥ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሊዮ 14ኛ አካዳሚው ላሳያቸው ማሻሻያዎች አፅንዖት ሰጥተው እንደተናገሩት፥ በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውሉ ቋንቋዎች ጥናት ጋር በሕግ፣ በታሪክ፣ በፖለቲካ ሳይንስ እና በምጣኔ ሃብት የጥናት አወቃቀር ለማደስ የተደረገውን ጥረት በማስታወስ፥ የበለጠ ተሃድሶ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ፥ ከትህትና እና ገርነት ጋር ተዳምሮ እርስ በርስ መቀራረብን፣ በትኩረት መደማመጥን፣ ምስክርነትን፣ ወንድማማችነትን እና ውይይትን ማዳበር የማያቋርጥ የለውጥ ልምምዶች መሆናቸውን በመግለጽ፥ እነዚህ በሙሉ መላው የክህነት አገልግሎት ዘልቆ መግባት ያለባቸው መንገዶች መሆናቸውን አስረድተዋል

ታሪክን የሚቀርጹ ድልድዮች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ቅዱሳንን፣ ብፁዓንን እና የአካዳሚውን ታሪክ የቀረጹ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን በማስታወስ፥ የዲፕሎማት ካኅን ልዩ ሚና፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” የሚለው የብርሃነ ትንሳኤው መልካም ዜና አብሳሪ እንደሆነ፣ የውይይት እና የእርቅ ተስፋዎች እየጠፉ የሄዱ ቢመስልም “ሰላምን እተውላችኋለሁ! ሰላሜን እሰጣችኋለሁ!” የሚለውን የተነሣውን ኢየሱስ ቃል ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ መቀጠሉን አስረድተው፥ “የመገናኛ ድልድዮች እና መንገዶች እንድትሆኑ በሚጠይቀው ተልዕኮአችሁ ከሰማይ የሚመጣው ጸጋ ወደ ታሪክ እንዲገባ ማድረግ እንዳለባችሁ ይጠራችኋል” በማለት ካኅናትን አሳስበዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ አካዳሚውን በጎበኙት ወቅት
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ አካዳሚውን በጎበኙት ወቅት   (@VATICAN MEDIA)

የክርስቶስ ፍቅር ምልክት

የጳጳሳዊ ዲፕሎማት ሌላው ተግባር፥ እውነት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ አገራት ማምጣት እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው፥ በመጀመሪያ እንደ ሐዋርያዊ እረኛ እና እንደ ዲፕሎማት ለሚያገለግሏቸው ሕዝቦች የኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅር ምሳሌ መሆን እንደሆነ አስረድተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ቅድስት መንበር እውቅና ለሰጠቻቸው ዲፕሎማሲያዊ አካላት ባደረጉት ንግግር፥ ቃላት ክብደት ኖሮአቸው እውነታዎችን በግልጽ እና በማያሻማ ሁኔታ መግለጽ እንዳለባቸው መናገራቸው በማረጋገጥ፥ ይህም “በእውነተኛ ውይይት ሥጋን ለለበሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በአካዳሚው ጸሎት ቤት ውስጥ ጸሎት ሲጸልዩ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በአካዳሚው ጸሎት ቤት ውስጥ ጸሎት ሲጸልዩ   (@VATICAN MEDIA)

የፍትህ አራማጆች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ መላውን የሰው ልጅ ቤተሰብ ለማካተት ያላቸውን አመለካከትን በማስፋት፥የዲፕሎማቱ አገልግሎት በካቶሊካዊ ማኅበረሰብ ብቻ የተወሰነ አለመሆኑን ገልጸው፥ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ምስል ለመለየት፣ ወደ ነበረበት ለመመለስ እና ለመንከባከብ የሚረዳ የእያንዳንዱ ፍትህ አራማጆች እንዲሆኑ የሚጠራቸው መሆኑን አስረድተዋል።

የሰው ልጅ ክብር አስከባሪዎች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ቀጥለውም፥ በጭንቀት በተሞላ ዓለም ውስጥ አለመግባባት ለመፍታት ብቸኛው መንገድ ጦርነት በሚመስልበት ጊዜ ለውይይት፣ ለመደማመጥ እና ለማስታረቅ የምናደርገው ጥረት በቂ ላይሆን አንዳንዴም ከንቱ ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።

የማበረታቻ ጉብኝት

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳልቫቶሬ ፔናኪዮ የጳጳሳዊ አካዳሚ ፕሬዝዳንት በበ ዓሉ ለተገኙት እንግዶች ባደረጉት የሰላምታ ንግግር፥ የር ዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጉብኝት፥ የቅድስት መንበር ዲፕሎማሲያዊ አገልግሎት ዝግጅት ማበረታቻ መሆኑን ገልጸው፥ በተጨማሪም የክኅነት ማዕረጋቸው 46ኛ ዓመት ላከበሩት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒትሮ ፓሮሊን መልካምን ተመኝተውላቸዋል።

 

 

28 Apr 2026, 16:43