ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ “የሃይማኖት ትምህርቶች ወጣቶች ልባቸውን እንዲያዳምጡ ያስተምራሉ” ሲሉ ገለጹ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በጣሊያን የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የሃይማኖት ትምህርቶችን የሚያስተምሩ የካቶሊክ ሃይማኖት መምህራን ብሔራዊ ስብሰባ ተሳታፊዎችን ቅዳሜ ሚያዝያ 17/2018 ዓ. ም. በቫቲካን ተቀብለው ንግግር አድርገውላቸዋል።
ቅዱስነታቸው ለተሳታፊዎቹ ባደረጉት ንግግር፥ “ሥራቸሁ ብዙውን ጊዜ ጸጥታን እና ትኩረትን የሚፈልግ በመሆኑ ለብዙ ልጆች ዕድገት እጅግ አስፈላጊ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ቅዱስ አጎስጢኖስን በመጥቀስ እንደተናገሩት፥ የሰዎች ልብ በዕረፍት እጦት የተሞላ እንደሆ እና ይህም ከእግዚአብሔር፣ ከፍጥረት እና ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያደናቅፉ፥ በመጨረሻም ማለቂያ ወደሌለው ጥማት የሚመራ እንደሆነ አስረድተዋል።
“አገልግሎታቸሁ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለአዲሱ ትውልድ ያላትን እንክብካቤ የሚገልጽ ነው” ብለው፥ “ታዳጊዎች እና ወጣቶች ወደ አስደናቂው ውስጣዊ ውይይት ዘልቀው መግባት የሚችሉበት በመሆኑ ዛሬ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው የትምህርት ዘርፍ አካል ነው” ሲሉ ገልጸውታል።
የካቶሊክ ሃይማኖት ትምህርቶች ጥልቅ የባሕል እሴቶችን እንደሚሰጡ ተናግረው፥ ይህም “እምነት ባሕልን እና ዘመናዊውን ማኅበረሰብ የሚቀርጽ ጠቅላላ እይታ የሚሰጥ ስለሆነ ነው” ብለዋል።
መምህራኑ የሚሰጡት ትምህርት ወጣቶች እራሳቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲያውቁ እና የሌሎችንም እምነት እንዲያከብሩ የሚረዳ፣ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የዳበረ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች የታገዘ እና በሌሎች የሃይማኖት ምርምር ዘርፎች ላይ ያተኮረ መሆኑን አስረድተዋል።
“የእያንዳንዱን ሰው ነፃነት ሙሉ በሙሉ በማክበር፥ አዲሱን ትውልድ ለመረዳት ስትሉ የማይቻል እና ግልጽ ያልሆነውን ነገር ታቀርባላችሁ” ብለው፥ “እውነተኛ ዓለማዊነት ሃይማኖታዊ እውነታን እንደሚያካትት፣ እንደ የትምህርት ግብዓትም እንዴት አድርጎ መያዝ እንዳለበት ያውቃል” ብለዋል።
“ልብ ለልብ ይናገራል” በሚለው የስብሰባቸው ጭብጥ ላይ በማሰላሰል እንደተናገሩትም፥ የካቶሊክ የሃይማኖት መምህራን ወጣቶች በዙሪያቸው ባሉ ጫጫታዎች ሳይረበሹ በውስጣቸው የሚሰማቸውን ማዳመጥን እንዲያውቁ መርዳት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
“ትምህርት ሰዎች ልባቸውን በማዳመጥ ውስጣዊ ነፃነትን ለማግኘት እንደሚረዳ፣ እምነት እና ምክንያታዊነት ወደ እውነት እንዲመሩ ያግዛቸዋል” ብለዋል።
“ሰዎች ያለ እውነት እና ትክክለኛ ትርጉም መኖር አይችሉም” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ “ወጣቶች አንዳንድ ጊዜ ግድየለሾች ቢመስሉም፣ በግድየለሽነት ውስጥ እውነት ከልክ በላይ የሚሰማቸውን ሰዎች ዕረፍት በማጣት እና በስቃይ ውስጥ ይደብቃቸዋል” ብለዋል።
ተማሪዎችን ወደ እውነት በሚወስደው መንገድ ላይ ሲጓዙ፥ የካቶሊክ የሃይማኖት መምህራን የጉዞአቸው አጋር በመሆን የተማሪዎቻቸውን የግል ዕድገት ለማክበር ትዕግስትን እና ፍቅርን እንደሚያገኙ ገልጸው፥ ቤተ ክርስቲያን በተለይም አስገራሚ ፈተናዎች ባሉበት በዚህ ዘመን ትምህርትን ለማስፋፋት ለምታደርገው ጥረት የሚሰጡትን ድጋፍ አድሰዋል።
“እውነት በሰዎች አማካይነት ወደ ሌሎች ይሸጋገራል” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ “እናንተ እግዚአብሔርን በመውደድ ለተማሪዎቻችሁ እውነትን ለማስተላለፍ፣ ታማኝ አስተማሪዎች ለመሆን እና ራሳችሁን ከፍ ሳታደርጉ እሴቶችን ለማስተላለፍ የተጠራችሁ ናችሁ” በማለት ንግግራቸውን ደምድመዋል።
