ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሊቀ ጳጳስ ክብርት ሣራ ሙላሊ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሊቀ ጳጳስ ክብርት ሣራ ሙላሊ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ   (@Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ አንግሊካውያን እና ካቶሊካዊያን ልዩነታቸውን ለማስወግድ በዘላቂነት እንዲሰሩ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአዲሷ የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ክብርት ሣራ ሙላሊ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝተዋል። ቅዱስነታቸው ሊቀ ጳጳስ ክብርት ሣራን በቫቲካን ተቀብለው ባደረጉት ንግግር፥ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን እና የአንግሊካውያን ኅብረት ምዕመናን አንድ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስን ለዓለም ለማወጅ እና ማንኛውንም ልዩነት እና ተግዳሮቶች ለማሸነፍ አብረው እንዲሠሩ አበረታተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ሰኞ ሚያዝያ 19/2018 ዓ. ም. ከካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ክብርት ሣራ ሙላሊ ጋር በቫቲካን ተገናኝተው፥ በሐዋርያዊ ሕንጻ ውስጥ በሚገኘው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ኡርባኖስ ስምንተኛ ጸሎት ቤት ውስጥ በጋራ ጸልየዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሰላምታ ንግግራቸው፥ በብርሃነ ትንሳኤው ወቅት ሊቀ ጳጳስ ክብርት ሣራ ሙላሊን በቫቲካን ሲቀበሏቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፥ ከ60 ዓመታት በፊት በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ እና በሊቀ ጳጳስ ሚካኤል ራምሴይ መካከል የተከናወነውን ትሪካዊ ግንኙነት አስታውሰዋል።

በሮም ለሚገኘው የአንግሊካውያን ኅብረት የአገልግሎት ማዕከል ምስጋናቸውን አቅርበው፥ በቅድስት መንበር የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ተወካይ ለሆኑት አቡነ አንቶኒ ቦልን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል ወቅት ሰላምታን አቅርበው፥ ይህም ለክርስቲያኖች በሙሉ ግብዣን የሚያቀርብ መሆኑን ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሊቀ ጳጳስ ክብርት ሣራ ሙላሊ ጋር
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሊቀ ጳጳስ ክብርት ሣራ ሙላሊ ጋር   (@Vatican Media)

“የትንሣኤው ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ‘ያለ መሣሪያ ትጥቅ’ መሆኑን ብዙ ጊዜ መናገራቸውን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው፥ “ይህም ለዓመፅ እና ለጠብ ዘወትር ያለ ጦር መሣሪያ ምላሽ መስጠት እንዳለብን ስለሚጋብዘን ነው” ብለዋል።

በክርስቲያኖች መካከል ያለው መከፋፈል የክርስቶስን ሰላም ውጤታማ በሆነ መንገድ ወደ ዓለም የማምጣት አቅማችንን ያዳክማል” ብለው፥ ዓለም ምስክርነታችንን ልብ እንዲለው ከፈለግን፥ በጸሎታችን እና በወንጌል ምስክርነት ላይ እንቅፋት የሚሆኑ መሰናክሎችን ለማስወገድ በምናደርገው ጥረት ጽኑ መሆን አለብን” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና አንግሊካውያን በእምነት እና በቅዱሳት ምስጢራት ውስጥ የተሟላ ኅብረት እንዲኖር ለብዙ አሥርተ ዓመታት ዘላቂ ሥነ-መለኮታዊ ውይይቶችን መደረጋቸውን አስታውሰዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሊቀ ጳጳስ ክብርት ሣራ ሙላሊ ጋር በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ኡርባኖስ ስምንተኛ ጸሎት ቤት
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሊቀ ጳጳስ ክብርት ሣራ ሙላሊ ጋር በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ኡርባኖስ ስምንተኛ ጸሎት ቤት   (@Vatican Media)

ሂደቱ ውስብስብ ቢሆንም የክርስቲያኖች የአንድነት ጉዞ በተለያዩ ታሪካዊ ከፋፋይ ጉዳዮች ላይ ፍሬ ማፍራቱን ገልጸው፥ በአሁኑ ጊዜ አንግሊካውያን ኅብረትን ተመሳሳይ ጥያቄዎች እያጋጠመው እንደሆነ ተናግረው፥ “ሆኖም እነዚህ ቀጣይ ፈተናዎች ኢየሱስ ክርስቶስን ለዓለም በጋራ ለማወጅ የሚያስችል እያንዳንዱን አጋጣሚ ከመጠቀም እንዲያግደን መፍቀድ የለብናል” ብለዋል።

ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በግንቦት 2024 ዓ. ም. ለአንግሊካውያን ኅብረት ሊቀ ጳጳስ የተናገሩትን በማስታወስ፥ “በክፍፍላችን ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስን ለዓለም ለማሳወቅ የተቀበልነውን የጋራ ጥሪ በተግባር ካልፈጸምን ውርደት ይሆናል” ብለዋል።

የስጦታ ልውውጥ
የስጦታ ልውውጥ   (@Vatican Media)

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከዚህም ጋር፥ “ልዩነቶቻችንን ለማሸነፍ መሥራትን ካልቀጠልን ውርደት ይሆንብናል” ብለው፥ የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ፣ ክብርት ሣራ ሙላሊን ለጉብኝታቸው አመስግነው፥ አንግሊካውያን ኅብረት እና ካቶሊካውያን በመንፈስ ቅዱስ በመመራት በወዳጅነት እና በውይይት አብረው እንዲጓዙ በማለት ጸሎታቸውን በማቅረብ ንግግራቸው ደምድመዋል።

28 Apr 2026, 16:59