“የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የአፍሪካ ጉብኝት ልባችንን እንድናድስ ጥሪ የሚያቀርብ ነው”
“ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በአፍሪካ ውስጥ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓይኖቻችንን እንድንከፍት እና ልባችንን እንድናድስ የሚጋብዝ እና የሰው ልጅ እውነተኛ መልኩን እንዲያሳይ የሚያሳስብ ነው።
በእነዚህ ቀናት ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ፥ በየከተሞች ጎዳናዎች ላይ እንደሚሰበሰቡ፣ ከግድግዳዎች በስተጀርባ ያረጁ የቆርቆሮ ጣሪያዎች እና ደካማ ሕንፃዎች ያሏቸው ቤቶች የሚታዩ ቢሆንም ነገር ግን የሰዎች ዓይን በደስታ የተሞላ እና ፈገግታ የሚታይበት ሰላምታ ሲለዋወጡ ይታያል።
ብዙ ሰዎች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን በዓይን ለማየት ለሰዓታት ሲጠባበቁ፣ ፎቶ በማንሳት የማይረሱ ትዝታዎችን ለማስቀረት ሲጥሩ፣ በመዝሙር እና በጭፈራ ባንዲራዎቻቸውን እና ቅርንጫፎችን ሲያወዛውዙ ታይተዋል።
የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ብዙውን ጊዜ ችላ የተባሉ ሰዎች ቁስሎችን እና ተስፋዎቻቸውን በማካተት፣ ወደ ኋላ ሳይመለከቱ የወንድማማችነት እና የእውነተኛ ግንኙነቶች ትስስርን ለመገንባት የሚጋብዝ ነው።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ወቅት ያገኟት አፍሪካ አስደናቂ ጠቀሜታ እና ከፍተኛ አቅም እንዳላት የሚያሳይ ሲሆን፥ በሌላ በኩል ዓለም አቀፍ ኃይሎች ይህን አቅሟን ለመገደብ እና ለመቆጣጠር ሲፈልጉ የቅኝ ግዛት ተጽዕኖ ዓይነቶችን በግልጽ እንደሚቀጥሉ፥ የተፈጥሮ ሃብቶቿ እና የእርሻ መሬቶቿ በመርዛማ ንጥረ ነገሮች የሚወድሙባቸው፣ ግጭቶች፣ ክፍፍል እና ሙስና የሚስፋፉባቸው ቦታዎችን ጨምሮ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ ኃይሎች የሃብቶች መሰረቅ የትውልድን የአሁን እና የወደፊት ዕጣ ፈንታን የሚያጠፉ ናቸው።
ነገር ግን የሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት በጦርነት እና በዓመፅ በተጎዳ ዓለማችን ውስጥ የእርስ በርስ ግንኙነቶችን በማመቻቸት እርቅን፣ መግባባትን፣ አንድነትን እና ሰላምን የሚያበረታታ እንደሆነ ተመልክቷል።
ቅዱስነታቸው በካሜሩን ጉብኝታቸው ወቅት፥ ከቀሪው የአገሪቱ ክፍል ጋር እንደገና የተገናኘችው የሰሜን ምዕራብ ካሜሩን ከተማ ባሜንዳ፥ ከመገንጠል ቀውስ ጋር ተያይዞ በተከሰተ ሁከት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ ለሞት ተዳርገዋል፤ መንገዶች በአብዛኛው ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፤ አየር ማረፊያው ለስምንት ዓመታት አገልግሎት ሳይሰጥ ቆይቷል። ይህ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሥፍራው መጓዝ አካላዊ ግንባታን ብቻ ሳይሆን አዲስ ተስፋን ለማምጣት አግዟል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአፍሪካ አኅጉር ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የአገራትን ልዩ ልዩ እውነታዎችን በማጉላት፥ አፍሪካ አኅጉር ሳትሆን ነገር ግን አንድ አካል ብቻ አድርጎ የማሰብ ዝንባሌን ተቃርነዋል።
እያንዳንዱ ሰው በልዩነት መካከል ያለውን አንድነት እና የእግዚአብሔር ልጅ የሆነበትን ሰብዓዊ የጋራ ክብርን በማመላከት እና የወንጌልን መልዕክት ለሌሎች ለማድረስ የተጠሩ በርካታ የቤተ ክርስቲያኒቱ ድምጾች መኖራቸውን በመግለጽ፥ ይህን በሚገባ ከተጠቀሙበት ተነሳሽነትን የሚያበረታታ እና የበለጠ ፍትሃዊ፣ የወንድማማችነት እና አጋዥ ማኅበረሰቦችን ለመገንባት እንደሚረዳ ተናግረዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “የጋራ ኃላፊነት እንዲኖር” በማለት በአፍሪካ አኅጉር ሆነው ለመላው ዓለም ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል። እያንዳንዳችን ወደ ሌሎች ዘድን እንድንቀርብ የሚጋብዝ መሠረታዊ ጥያቄን አንስተዋል። እርስ በርስ እንድንገናኝ፣ ይቅር እንድንባባል፣ እንድንደጋገፍ፣ በኅብረት እንድንራመድ እና የወደፊት ሕይወትን ለመገንባት የሚያስችል የጋራ ኃላፊነትን እንድንወስድ ጋብዘውናል። ብዙውን ጊዜ በመከፋፈል፣ በትእቢት እና በማስፈራራት በተገነባ ዓለም ውስጥ እያንዳንዳችን በዕለታዊ ሕይወታችን ውስጥ ቁርጠኝነታችንን በተግባር እንድንገልጽ የሚጋብዘንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥሪ በድጋሚ አቅርበዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው እውነተኛ ሰብዓዊነትን መልሶ ለማገናኘት፣ የሰዎችን ሰብዓዊ ክብር እና ነጻነት በመጠገን፥ ዕድገታቸው እና ብልጽግናቸው የሚረጋግጥበትን መንገድ በመፈለግ፣ የበላይነት እና የቁጥጥር ፍላጎቶችን ለማስቀረት ከፍተኛ ድጋፍ አድርገዋል” ሲል ርዕሠ አንቀጹ ሃተታውን ደምድሟል።
